ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

መከላከያና ማዕከላዊ ዕዝ አገራዊ ግዳጃቸውን በጽናት እንደሚወጡ አስታወቁ

የአገር መከላከያ ሚኒስትር ህገመንግስቱን፣ አገርናና ህዝብን በታማኝነት እንደሚያገለግል አስታወቀ። የአቶ መለስን ዜና ህልፈት አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ይፋ የሆነው የመከላከያ ሚኒስትር የሃዘን መግለጫ የአቶ መለስን ማለፍ ታላቅ ሃዘን ብሎታል።

አቶ መለስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውንም ግዳጅ በጭር ጊዜና በብቃት መመከት የሚችል እንዲሆን አድርገው ማዋቀራቸውን ያተተው መግለጫ፤ አገሪቱ የምትመራበትና የቆመችበት ህገመንግስት ከማስጠበቅ አንጻር “የማያወላዳ” አቋም እንዳለው መልክቷል። የአገር መከላከያ ሰራዊት አገራዊ ግዳጁን ያለማዋላዳት እንደሚወጣ ባበሰረበት መግለጫው እንደተመለከተው አቶ መለስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ግዳጃዊ ብቃቱና አቅሙ ከፍተኛ እንዲሆን ያበረከቱት ተግባር የማይረሳ መሆኑን አመልክቷል። አቶ መለስ የገነቡት ጠንካራ ድርጅት፣ መንግስትና፣ ስትራቴጂ በቀጣይነት አገሪቱን በጀመረችው የልማት ጎዳና እንደሚመራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይፋ አድርጓል።

በተመሳሳይ የማዕከላዊ እዝ ባወጣው መግለጫ በጠ/ሚ መለስ ሞት የተሰማውን ሃዝን አውስቶ በኢትዮጵያ ልዕልናና ህልውና ላይ ለሚቃጣ ማናቸውም አይነት ሙከራ አጻፋውን የመመለስ፣ የማያዳግም ምት የመምታትና ሙሉ በሙሉ አገራዊ ሃላፊነቱን በቁርጠኛነት እንደሚወጣ አስታውቋል። የ17ኛው ክፍለ ጦርም አደራውን በመጠበቅ አገራዊ ሃላፊነቱናና ህዝባዊ አደራውን እንደሚወጣ አመልክቷል።

በተያያዘ ዜና በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  ሃላፊአቶ በረከት ስምዖን ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ህጋዊ ስርዓቱ ተሟልቶ መንበረ ሹመታቸውን በፓርላማ የሚጸድቅበት ሁኔታ እንዳለ ሆኖ፣ አሁን የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መሆናቸውን በይፋ ተናግረዋል። በዚሁ መሰረት አቶ መለስ ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሰራዊት አዛዥ በመሆን የነበራቸውን ሃላፊነት መረከባቸውን አረጋግጠዋል። ዛሬ ማለዳ አቶ በረከት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ” ጦሩን ማን ይመራል ” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ አቶ ሃይለማርያም አቶ መለስ የሚሰሩዋቸው የነበሩትን ስራዎች ሁሉ ይሰራሉ ብለዋል።   አቶ በረከት በመግለጫቸው አቶ መለስ ተሽሏቸው ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ በድንገት ትናንት 5፡40 ህይወታቸው ማለፉን አስታውቀዋል። “የት ነበር ሲታከሙ የቆዩት?” ለተባለው ለደህንነታቸው ሲባል አስቀድመን ስንናገር እንደነበረው ውጭ አገር ነበሩ ከማለት ውጪ ያለሉት የለም።