ማመልከቻ……. ለአለም አቀፉ የስሜት ሀይል ኤጀንሲና የወንዱ ፀጥታ ምክርቤት…….

ሴቶች በተፈጥሯቸው ውብናቸው ፡፡ወብ ሆነው ሲያበቁ የበለጠ ውብ ለመሆን ይጥራሉ፣ሁልግዜም ውበታቸውን በማጉላት አምሮ መታየትን ይሻሉ፡፡ሁሉም ሴቶች ማለቴነው ፡፡አሁን አሁን ግን ቁንጅና በሁለት የተከፈለ ይመስላል፣ካንገት በላይና ካንገት በታች ተብሎ ፡፡ይህ ክፍፍል ስር ሰዶ፣ በሁለት ጎራ አሰልፎ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡የውጊያ አሰላለፉን ባዲስ መስመር…….

ባብዛኛው የፊት ቅርፃቸው የሚያምር እንሰቶች ካንገት በታች እምብዛም ናቸው በተቃራኒው ካንገት በታች የሚያምሩ ሴቶች ፊታቸው አይስብም፡፡ውጊያው ታድያ የሚመራው ማዘዣ ጣብያቸውን ካንገት በላይ ባደረጉት እና ጦራቸውን ስንደዶ አፍንጫ፣ዘንፋላ ፀጉር፣አመልማሎ ከንፈር በሚባሉ ክፍለጦሮች አደራጅተው በተጨማሪም ልቃቂት አይን የሚባል ልዩ ኮማንድ እዝ የጠላት ቀጠና ውስጥ ድንገት በመግባት ልብ ስልም ማድረጉን ስራ የሚሰራል ለዋናዎቹ ሀይል ድጋፍ የሚሰጥ ሀይል አላቸው፡፡
naked_art-402x251
እነኝህ ክፍለጦሮች እና የኮማንዶ ልዩ እዙ ቻፒስቲክ፣መነፅር፣ኩል እና ሌሎች መሰል ዘመናዊ መሳርያዎችን የታጠቁ ሲሆን ያለረፍት ለረጅም ሰአታት በፅናት ይዋጋሉ፡፡ማዘዣ ጣብያቸውን ካንገት በታች አርገው ሰፊ የጦር ግንባር በመፍጠር የጀግና ትግል እያረጉ ያሉት አማፅያን ጉችጉች ያለ ጡት፣እንደ እንዝርት የሚሾር ቀጭን ወገብ፣የሚውረገረግ ሽንጥና ዳሌ በሚባል ሜካናይዝድ ክፍለጦሮች የተደራጁናቸው፡፡ይሄ ግንባር ከጠላት የጦር አሰፋፈር ጋር ሲነፃፀር ጦሩ የሰፈረበት ስፍራ ለሜካናይዝድ ክፍለጦር በጣም አመቺ ነው፡፡ ሲኪኒ፣ታይት ፣ፓንት የሚባሉ ተሸከርካሪዎች ክፍለጦሩን በፍጥነት በማንቀሳቀስ የጠላትን የውጊያ አቅም በማንኮታኮት ረገድ አጀብ የሚያሰኝ ድሎችን ተጎናፅፈዋል፡፡

ከመደበኛው የምሽግ ውጊያ በተጨማሪ ሁለቱም አማፅያን እጠላት ጦር ቀጠና ተመሳስሎ ዘልቆ በመግባት ድንገተኛ ውጊያ ያካሂዳሉ፡፡ካንገት በታች የመሸገው ሀይል የጨሌ ብስ አይኖችን ቅንድብ በመላጨት እና ጎራዳ አፍንጫን በሎቲ አስታጥቆ ተመሳስሎ በመግባት የጠላትን የሎጀስቲክ አቅም በማንኮታኮት ጦሩ የፈለገ ቆራጥ ቢሆን የታጠቀው መሳርያ ይበልጥ ጀግንነቱን እንደሚያጎላ በማሳየት በተቀራኒ የቆመውን ጦር ሞራል በመስበር የውጊያ የበላይነትን ለመጎናፀፍ ይሰራል፡፡

በሌላ በኩል ካንገት በላይ መሽጎ ጠባብ ግንባር በመፍጠር የሚወጋው መቺ ሀይል ደላጎ ጡትን በጡት ማስያዣ በመወጠርና በመቀሰር ጉች ጉች ያሉትን ጡቶች ለመመከት ድንገት እጠላት ጦር ሰፈር ሰርጎ በመግባት በተጨማሪም እንደንዝርት የቀጠነውን ወገብ በሚመክት መልኩ በሎቲ የተደራጀው እምብርት፤መሰል አፅፋዊ እርምጃ እንዲወስድና የጠላትን የውጊያ አቅም የማንኮታኮት ተልኮ ይፈፅማል፡፡

አሁን አሁን ግን በውለቱም ግንባሮች የተሰለፉት ሀይሎ የሚያደርጉት ውጊያ ከልክ ያለፈና ደም አፋሳሽ እየሆኑ መምጣቱ አሳስቦናል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የታጠቁትን መሳርያዎች በመተው እና ሀፍረተስጋቸውን ጉኝር በሚየዳርግ ታይት በሚባል ሳንጃ ብቻ ተከፍነው የጨበጣ ውግያቸውን አጧጡፈውታል፡፡ “መኳኳልን” ታጥቀው ሲዋጉ የነበሩት ቡድኖች በቀጣይ ባለማቀፍ ህግ የተወገዘውን “መገላለጥ” የሚባል አቶሚክ ቦንብ ወደመጠቀሙ እያዘነበሉ በመሆኑ የአለም አቀፉ የስሜት ሀይል ኤጀንሲ ጉዳዩን ቢያየው እና የወንዶች ፀጥታ ምክርቤት ውጥረቱን የማርገብ ዲፐሎማሲያዊም ሆነ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንዲያረግ ስል አሳስባለሁ ፡፡

ይላችኋል…………በልክ ሲሆን ይሻላል! አለማቀፍ ተቋም ካንትሪ ዳይሬክተር

ኮ/ው ፀደቀ ድጋፌ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *