ፍርዱ ተመጣጣኝ ይሆን?

ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ቪዛ አስገኛለሁ በማለት በቲቪ፣ በሬዲዮና በጋዜጣ በይፋ ማስታወቂያ አስነግሮ፣ ቀበና በገሃድ ቢሮ ከፍቶ በሰልፍ ገንዘብ ሲሰበስብ የነበረው የአስካሉካ ባለቤት መቀጣቱ ታውቋል። የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እንዳስታወቀው ፍርድ ቤት የቅጣት ርምጃ የወሰደው በተባባሪዎቹም ላይ ስለመሆኑ ያለው ነገር የለም ። ተበዳዮች ቢሮውን ከበው ጩኸታቸውን ሲያሰሙ በፖሊስ እንዲባረሩ ይደረግ እንደነበር በወቅቱ የተዘገበበት ይህ ከፍተኛ የወንጀል ተግባር የበርካታ ምስኪኖችን ህይወት አደጋ ላይ የታለም ነበር።

ተበዳዮቹ ለተለያዩ ሚዲያዎች በወቅቱ ሲናገሩ ፍትህ አጥተው፣ የድርጅቱን ባለቤት ለመክሰስ አቅም አንሷቸው ቢሮው አካባቢ ወፍጮ ቤቶችና በረናዳ እያደሩ ሲሰቃዩ ነበር። በብስጭትራሱንም ያጠፋ ተበዳይ ነበር። ሁኔታው እየተካረረና የህዝብ መነጋገሪያ ሲሆን አዲስ አበባ ፖሊስ በዳይን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ። የአስካሉካ ባለቤት መጥፋታቸውንና አብረዋቸው ሲሰሩ የነበሩትን ሰዎች በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ አወጀ። የደርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተያዙ ተሽከርካሪዎችና በባንክ ያለ ገንዘብ መያዙን ተነገረ።

ፖሊስ በተናገረው መሰረት ተከሳሹ በኢንተርፖል አማካይነት ከጀርመን አገር ተይዘው ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ተደረገና የፍርድ ሂደቱ ቀጠለ። ዛሬ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባሰራቸው ዜና ግለሰቡ በእስርና በገንዘብ መቀጣታቸውን አስታውቋል። አብረዋቸው በተባባሪነት ሲሰሩ ስለነበሩት ሰዎች ግን ያለው ነገር የለም። ኢቴሬድ የዘገበው ዜና እንዲህ ይነበባል። ፍርዱ ተመጣጣኝ ይሆን?

ደቡብአፍሪካ  ባዘጋጀችው የአለም ዋንጫን ለማየት ወደ አገሪቱ ለመጓዝ የሚያስችል ቪዛ አለኝ በማለት በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያጭበረበረው ግለሰብ ተቀጣ፡፡

ከሶስት አመታት  በፊት በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት የተካሄደውን የአለም ዋንጫን ለመመልከት ወደ ደቡብአፍሪካ መሄድ የሚያስችል ቪዛ አሰጣለሁ በሚል  ከተለያዩ ዜጎች ከ25 ሺህ  እስከ 35 ሺህ ብር የተቀበለውተከሳሽ የአስካሉ ካን ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ግርማይ ገብረሚካኤል  ተቀጣ፡፡

ተከሳሹ ገንዘቡን የሰበሰበው በ2002 ዓ/ም ከህዳር እስከ ግንቦት ወር  ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በጊዜውም ገንዘባቸውን ለሰጡት ግለሰቦች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚሄዱ ይነግራቸዋል፡፡ ነገር ግን አቶ ግርማይ የሰበሰቡትን ገንዘብ ይዘው ከአገር በመውጣታቸው በአለም አቀፉ ፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል አማካኝነትተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ችለዋል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት አምስተኛ ወንጀል ችሎትም የሰነድና የሰው ማስረጃዎችንካጣራበኋላ  ግለሰቡ ከተከሰሱባቸው ስምንት የክስ መዝገቦች መካከል በሰባቱ ጥፋተኛ  ብሏቸዋል፡፡ በዚህምፍርድቤቱ ተካሳሹን በስድስት አመት ከስድስት ወራት እስራትና በስምንት ሺህ ብር ቀጥቷቸዋል፡፡ ከዚህምበተጨማሪ ግለ ሰቡ ለሁለት አመታት ያህልም  ከህዝባዊ መብቶቻቸው እንዲታገዱ ፍርድቤቱ ውሳኔአስተላልፏል  ፋና እንደዘገበው፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *