ኢህአዴግ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ የ”ጥልቅ” ተሃድሶ ማሳያ የሚሆነውን ሹም ሽር እንደሚያካሂድ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ይፋ አድርገዋል። የ
ተለያዩ ሚዲያዎች ሹም ሽሩ እሳቸውንም እንደሚነካ በመጠቆም ጉዳዩን አብይ ርዕስ አድርገውት ሰንብተዋል። በተቀናቃኝ ፓርቲዎች ዘንድ ግን ለውጥ እንጂ ሹም ሽር ለውጥ እንደማያመጣ እየተጠቆመ ነው። ተቃዋሚዎች ይህንን ቢሉም ኢህአዲግ ግን “ጥልቅ ተሃድሶ” ላይ መሆኑን ደጋግሞ በማስታወቅ ላይ ይገኛል።
በጥልቀት የመታደሱ ጉዳይ የሚያስገኘው ውጤት ወደፊት የሚለካ ቢሆንም መታደሱን ተስታኮ የምርጫ ህግን የማስተካከል እቅድ ስለመያዙ በይፋ ተሰምቷል። ገዚው ፓርቲ የምርጫ ህጉን ለማሻሻል የገባውን ቃል የሚታወቁ ይተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች አጣጥለውታል። በሌላ በኩል አቶ ልደቱን ጨምሮ ስልጣን ለመጋራት ፍላጎት ያላቸውና ከኢህአዴግ ጋር ተስማምተው ለመጓዝ የወሰኑ ድርጅቶች አሉ። በሊላ በኩል ደግሞ የሽግግር ቻርተር በማርቀቅና በማዘጋጀት የተጠመዱ አሉ። ለሁሉም የጅርምን ሬዲዮ ይህንን ዝግቧል።
ፍትሀዊ ምርጫ እንደ አማራጭ
በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች፣ በተለይም በኦሮሚያ፣ በአማራ እንዲሁም በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን፣ የተካሄደዉ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለብዙ ሰዎች መሞት፤ መጎዳት፤ መታሰር እና አገር ጥሎ መሰደድ ትልቅ ምክንያት ሆኗል።
ፍትሀዊ ምርጫ
ተቃዉሞዉን ለማብረድም አንዳንድ ማሻሻያዎች አደርጋለሁ ያለዉ መንግሥት ሹምሽር ለማካሄድ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ረዳ ሰሞኑን ተናግረዋል። የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ግን ይህ ሕዝቡ ለጠየቀዉ ጥያቄ መልስ አይሆንም ይላሉ። ሥር ነቀል ለዉጥ እንደሚያስፈልግ በማሳሰብም፤ ምርጫ መካሄድ እንደሚኖሩበት ይናገራሉ። በመድረክ ፓርቲ ዉስጥ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከታወጀ በዋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ ጦላይና ዲዴሳ የወታደሮች ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ይገልጻሉ። ሹም ሽሩም ቢሆን «የግለሰብ መለዋወጥ ምንም ፋይዳ የለዉም፣ አገር መሠረታዊ ለዉጥ ትፈልጋለች» ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። የሚፈለገዉ የፖሊሲ ለዉጥ መሆኑንም ያመለክታሉ።
ዶክተር መረራ አገሪቱን ወደ ተረጋጋ መልክ ለማምጣት የሽግግር መንግሥት ወይም ባለ አደራ መንግሥት አቋቁሞ ምርጫ መካሄድ እንዳለበት ያሳስባሉ። ይሁን እንጅ መንግሥት ይህን አይቀበልም። አቶ ጌታቸዉ ረዳ ምርጫ የሚካሄደዉ በመደበኛዉ ጊዜ ከአራት ዓመታት በኋላ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ የፌስቡክ ከተከታዮቻችንን አወያይተን ነበር። አንዳንዶቹ ገዢዉ ፓርቲ «በምርጫ እንደማይለቅ፣ አስመራጩ ራሱ፣ ቆጣሪው ራሱ፣ ፈራጁ፣ ዳኛው፣ ምስክሩ ራሱ፣ የሚያዋጣው ትግሉን መቀጠል ብቻ እና ብቻነው» ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ «በኔ እምነት አሁን ምርጫ ይደረግ ቢባል „የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ ነው» የሚሆነው ምርጫ ሲባል መምረጥና መመረጡ ብቻ ሳይሆን አመራረጡና የምርጫው አፈጻጸም ሂደት ነው ወሳኙ» የሚሉ አስተያየታቸዉን ሰንዝረዋል።
መርጋ ዮና ሸዋዬ ለገሠ ጀርመን ድምጽ