ላለፉት ሁለት አስር አመታት ለሚጠጋ ጊዚያት ሚድሮክ አጥሮ የያዘውን ቦታ ወደ ግንባታ ለመቀየር መወሰኑን አስታወቀ። የሜድሮክ ኢትዮጵያ ዋና ሰራ አሰፈፃሚ አቶ አብነት ገብረመስቀል ይህንኑ አስመልክተው “በአሁኑ ወቅት ቁርጠኛ ነን” ማለታቸው ተጠቁሟል። ሜድሮክ በተመሳሳይ ግንባታ እጀምራለሁ በማለት መግለጫ የሰጠው ለበርካታ ጊዚያት ሲሆን አፈጻጸም ላይ ግን አይታይም።
የበርካታ መንገድ ፕሮጀክቶችን ተረከቦ በውሉ መሰረት ጨርሶ ባለማስረከቡ መነጠቁ አይዘነጋም። ድርጅቱ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ መሬት አጥሮ ማስቀመጥ ልዩ ባህሪው በመሆኑ ሌሎች ባለሃብቶች መሬት ሲቀሙ ለማነጻሰሪያ ይጠቀሙበታል። እንደ ፋና ዘገባ ግን የአሁኑ የመጨረሻ ነው።
“ከእዚህ በኋላ ያለፈው ዓይነት ችግር አይታሰብም” በማለት ለግንባታ የተወሰደን መሬት ማልማት ግዴታ መሆኑንን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው መናገራቸውን ያወሳው ፋና፣ የከተማ አሰተዳደሩና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በኩል ይህን የሚከታተል ቡድን መቋቋሙንም አመልክቷል። ተከታዩ የፋና ዘገባ ነው
ሜድሮክ ኢትዮጵያ በመዲናዋ ለረጅም ጊዜ አጥሮ የያዛቸው ቦታዎች ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ወደ ሰራ መግባታቸውን አስታወቀ
አዲሰ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሜድሮክ ኢትዮጵያ በበአዲስ አበባ ከተማ የተየያዩ አካባቢዎች የሚገኙትና ለረጅም ጊዜ አጥሮ የያዛቸው ቦታዎች ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ችግሮቻቸውን በመፍታቱ ወደ ሰራ እንደሚገቡ ማድረጉን አስታውቋል።
ሜድሮክ ኢትዮጵያ በከተማዋ ቁልፍ ቦታዎች ማለትም ፒያሳ፣ ሜክሲኮና ቦሌ የሚገኙትን እና ለረጅም ጊዜ አጥሮ ያያዛቸውን 350 ሺ ካሬ ሜትር በላይ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ናቸው ወደ ስራ የገቡት ብሏል። በከተማዋ 17 ፕሮጀክቶች ያሉት ሜድሮክ ኢትዮጵያ፥ ከ23 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጿል።
ሜድሮክ ኢትዮጵያ በመዲናዋ ለረጅም ጊዜ አጥሮ ያስቀመጣቸው ቦተታዎች ወደ ግንባታ መግባታቸው አስምልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አለማየው ተገኑ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው በዛሬው እለት ጉብኝት አካሂደዋል።
በዚሁ ጊዜም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥረው ወደ ልማት ሳይገቡ የቆዩ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ስራ የማይገቡ ከሆነ ህጋዊ እርምጃዎች የሚወስድ መሆኑን ምክትል ከንቲባው አስጠንቅቀዋል ምክትል ከንቲባው በግል ባለሃብቶች፣ በምንግስት ተቋማት እና በልማት ድርጅቶች ታጥረው ለመንግስትና ለህዝብ ጥቅም ሳይሰጡ ለአመታት የተቀመጡ ቦታዎች መሬቱን የወሰደ አካል በፍጥነት ማልማት አለበት ብለዋል።
ይህ ከልሆነ ግን አስተዳደሩ ህግና ስርዓቱን ጠብቆ በአሰራር መሰረት ህጋዊ እርምጃዎች የሚወስድ ይሆናል ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ከእዚህ በኋላ ያለፈው ዓይነት ችግር አይታሰብም ያሉት አቶ አባተ ስጦታው፤ የከተማ አሰተዳደሩና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በኩል ይህን የሚከታተል ቡድን መቋቋሙንም ገልፀዋል።
በፕሮጀክቶቹ ባለቤቶች በኩልም የጋራ ጉበኝት እየተደረገ ችግሮቹ እየተለዩ የሚፈቱበት አቅጣጫም መቀመጡን ገልፀዋል። በከተማው መሬት ወስደው ወደ ሰራ የማይገቡ ፕሮጀክቶች ለመጓተት ምክኒያት የነበሩ ችግሮች በመንግስት በኩል ሙሉ ለሙሉ የተፈቱ በመሆናቸው፤ ከአሁን በኋላ መሬት ወስደው ወደ ልማት ያልገቡ አካላት በሙሉ አቅም ወደ ሰራ መግባት ይጠበቅባቸዋልም ሲሉም አሳስበዋል።
በሚድሮክ ኢትዮጵያ በኩል የነበረው ችግርም በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተቀርፎ ወደ ስራ መገባቱን ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታው ገልጸዋል። የሜድሮክ ኢትዮጵያ ዋና ሰራ አሰፈፃሚ አቶ አብነት ገብረመስቀል በበኩላቸው፥ ለፕሮጀክቶቹ መዘግየት የዲዛይን ለውጥ፣ የመብራትና ውሃ መስመሮች በጊዜው አለመነሳት፣ የተሻሻለ ፕላን አለመኖር እንዲሁም የድርጅቱ የውስጥ ችግሮችና ለችግሮቹ ፈጥኖ መልስ አለምስጠት የሚሉትን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ ይላሉአቶ አብነት፥ አሁን ድርጅቱ በከተማዋ በወሰዳቸው ቁልፍ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ፕሮጄክቶቹ ወደ ሰራ ገብቷል ብለዋል። ለፕሮጅክቶቹ መዘግየት ኩባንያውንም ይሁን መንግስትን ኪሰራ ላይ ጥሏል የሚሉት አቶ አብነት፥ እንደ አጋር ድርጅት በፍጥነት ወደ ሰራ ግብተን የሚጠበቅብንን ሃላፊነት ለመወጣት ተዘጋጅተናል፤ በአሁኑ ወቅትም ቁርጠኛ ነን ብለዋል።
በደመቀ ጌታቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *