” ጥልቁ ተሃድሶ” ጌታቸው ረዳን ገፋ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም አዲሱን ካቢኔ ይፋ አደረጉ ዶ/ር ቲዎድሮስ አድሃኖም በቀድሞው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ተተኩ። ሹመቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ለኦሮሞ ወይም ለኦህዴድ የማስተላለፍ እንደሆነ ተጠቁሟል። ውሳኔው ህወሃት ቁልፍ ስልጣን ጠቅልሎ ይዟል ለሚለው ምላሽ ለመስጠትና ሰፊ የሀዝብ ውክልና ያለውን የኦሮሞ ህዝብ ውክልና ከፍ በማድረግ በኦሮሚያ ያለውን ተቃውሞ ለማርገብ እንደሆነ ሹመቱን ተከትሎ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ዘጠኝ ሚኒስትሮች በቦታቸው እንዲቀጥሉ ሲደረግ የተቀሩት ተነስተው ባብዛኛው የዶክተርነት ማዕርግ ያላቸው አዳዲስ ሰዎች ተሹመዋል። በሚሰጡት መግለጫ የከፋ ሃረግ በመጠቀማቸው በስፋት የተወገዙት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከተሰናባቾቹ አንዱ ሆነዋል። በሌላ አነጋገር “ጥልቅ ተሃድሶው ገፍቷቸዋል”

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

ፋና በዝርዝር ያቀረበው የሹመት ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው።

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የካቢኒያቸውን አዳዲስ እጩ አባላት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያቀረቡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሉበት ይቀጥላሉ ያሏቸው የካቢኒ አባላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ናቸው።

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

አዲስ የቀረቡት እጩ የካቢኒ አባላት፦

1. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርdownload (1)

2. አቶ ታገሰ ጫፎ፦ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር

3. ዶክተር አብረሃም ተከስተ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር

4. ዶክተር በቀለ ጉላዶ፦ የንግድ ሚኒስትር

5. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፦ የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር

6. ዶክተር ኢያሱ አብረሃ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር

7. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

8. አቶ አህመድ ሺዴ፦ የትራንስፖርት ሚኒስትር

9. ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር

10. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፦ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር

11. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦ የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

12. አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር

13. ዶክተር ገመዶ ዳሌ፦ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር

14. ዶክተራው ሽፈራው ተክለማርያም፦ የትምህርት ሚኒስትር

15. ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ፦ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር

16. ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር

17. ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

18. ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቤሳ – የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር

19. አቶ ርስቱ ይርዳው፦ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር

20. አቶ ከበደ ጫኔ፦ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚኒስትር

21. ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፦ የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ናቸው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *