“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ብርሃኑና ጁሃር ይህን እንቅስቃሴ ባልመሩት ነበር”አባይ ጸሃዬ

 ” የእኛ ምስል፣ የእኛ ገደል ማሚቱ” ሲሉ ተቋማትን ሰየሙ

አቶ አባይ ጸሃዬ ማህበራትን፣ ፍርድ ቤቶችን፣ መገናኛ በዙሃናትን ነጻነታቸውን ጠብቀው በድፍረት ለሚወከሉት ሕዝብ መስራት እንዳይችሉ መደረጋቸው ስህተት እንደነበር ተናገሩ። የግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር ለንጽጽር ቀረቡ።

juhar-mohamed

የተጠቀሱት ተቋማት በተሟላ ሁኔታ ባለመቋቋማቸው ስራቸውን ነጻ ሆነው መስራት ባለመቻላቸው ” የእኛ ገደል ማሚቱዎች፣ የእኛ ምስሎች ሆነዋል” ሲሉ ነው አቶ አባይ ጸሃዬ የገለጿቸው። አንዳንዴ ተቋማቱ በድፍረት ለመስራት ሲሞክሩ ከተለያየ አቅጣጫ ጫና እንደሚፈጠርባቸው አቶ አባይ ምስክር ሆነዋል። ቀደም ሲል ኢህአዴግ በራሱ አባላት አስጠንቶ ባቀረበው ሪፖርት በተመሳሳይ ችግር መኖሩን ባደባባይ ቢያምንም ለውጥ አልታየም ነበር።

“የኢትዮጵያ የዴሞክራሲና የፌደራል ስርዓት ግንባታ ከየት ወዴት” በሚል ርዕስ የገዢው ፓርቲ ንብረት የሆነው ፋና በሮድካስቲንግ ባዘጋጀውና በድረ ገጽ በተለቀቀው ክፍል ሁለት ውይይት ላይ አቶ አባይ ጸሃዬ እንደተናገሩት ነጻ ተቋማት አለመገንባቱ ጥፋት ነው። ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የነጻ ተቋማት አለመኖር በአገሪቱ የወደፊት ጉዞና የዴሞክራሲ ግንባታ ላይ አደጋ እንደሚያስከትል በተደጋጋሚ ሲገለጽ ኢህአዴግ ለመስማት ፈቃደኛ አልነበረም። በዚሁም ሳቢያ የተደማመሩ ችግሮች ህዝብን ወደ አመጽ እንደከተተው በዙዎች የሚናገሩት ነው።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

brhanu-nega

አቶ አባይ ጥፋተኛ ነን ካሉ በሁዋላ መልሰው ” ኢህአዴግ ዴሞክራሲያዊ ባይሆን ኖሮ” ሲሉ ሌላ ተናጋሪ ለሰጡት አስተያየት ሲመልሱ፣ ” በ1983 ዓ.ም ሁሉንም ነገር በጠመንጃ ያስቀጥል ነበር”በማለት የነበረውን የወቅቱን ሂደት አስረድተዋል። አያይዘውም ” አሁን ኢህአዴግ በጥልቅ ከታደሰ በቂ ነው” በማለት በርካታ ስራዎችን የሰራ ፓርቲ ይፍረስ ማለት አግባብ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

እርስ በእርሱ የሚማታው የአቶ አባይ ንግግር አንዴ ” ነጻ ተቋማትን አልገነባንም” በሚል ለተፈጠረው ቀውስ ሃላፊነቱን እንደሚወሰዱ ይጠቁሙና፣ መልሰው ” ዴሞክራሲያዊ ባንሆን ኖሮ ከጅምሩ በጠመንጃ…”በማለት አሁን ጨርሶውኑ ብረት እንደማያነሱ ይናገራሉ።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

እንደሁሉም የኢህአዴግ ነባር አመራሮች በተደጋጋሚ “አቶ ለደቱ አያሌው ትክክል ነው”ያሉት አቶ አባይ፣ አሁን በአግሪቱ የተንሳውን ተቃውሞ ሳያነሱ አላለፉም። አቶ አባይ እንደሚሉት አሁን የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞና አመጽ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ሊመሩትና ኢህአዴግን አንገቱን አንቀው ሊይዙበት በተገባ ነበር። እዚህ ላይ በዙዎች እንደሚሉት ኢህአዴግ የፖለቲካውን ምህዳር ቀርቅሮ ሳለ እንዴት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህዝብ ዘንድ ባደባባይ ይቀርባሉ። ስብሰባ ማካሄድ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ መደራጀትና መቃወም በወጉ ባልተፈቀደበት አገር እንዴት ተብሎ ይህን ማድረግ ይታሰባል?

ተቃዋሚዎች ስራቸውን ባግባቡ አለመስራታቸውን ለማመላከት ” ይህ ሁሉ በጥብጥ ውስጥ የገባውን ወጣት መናምኑ… ይዘው ኢህአዴግን በወጠሩት ነበር”ያሉት አቶ አባይ ” ይህን አመጽ ጁሃርና ብርሃኑ ማንቀሳቀስ አልነበረባቸውም” ሲሉ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎችን ተችተዋል። ለ” አርበኛ” ፕሮፌሰር ብርሃኑና አቶ ጁሃር መሃመድ እውቅና ሰጥተዋል። እሳቸው ይህን የበሉ እንጂ ዲያስፖራው ዘንድ የአመጹ ባለቤት ራሱ ህዝብ እንጂ ሌላ አካላት አይደሉም። በማብቂያቸው መተጋገዝና አብሮ መስራት አግባብ እንደሆነ ጠቁመዋል። አቶ አብይ ጸሃዬ በአገሪቱ ከፍተኛ መዋል ንዋይ ፈሶበት ከከሽፈው የስኳር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደነበር የሚታወስ ነው።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

ኢንጂነር ጸደቀ ይሁኔ በተመሳሳይ ውይይት ላይ ሃብትን አስመልክቶ የተናገሩት የሁሉንም ተሰብሳቢዎች ትኩረት የሳበና የተለየ ምልከታ ያገኘ ስለመሆኑ ካሜራ ያመላከታቸው ሰዎች ገጽ ይናገራል። ኢንጂነሩ እንዳሉት ሃብት ከመሬ በላይ ነው። ሃብት ከሞት በሁዋል ምን አልባትም የሚገዛው የብረት አስከሬን ሳጥን ብቻ እንደሆን አመልክተው፣ ለተሰብሳቢዎቹ የማያልፍ ነገር መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0