ከፍተኛ የሳላ መንጋ የሚንጋጋበት፣ የተለያዩ የዱር እንስሳት የሚፈነጩበት የአዋሽ ፓርክ መጨረሻ የተቃረበ ይመስላል። በተደጋጋሚ ሃላፊዎች ፓረኩ አደጋ ላይ እንደሆነ ቢገለጹም ሰሚ የተገኘ አይመስልም። ዛሬ 182 ሳላዎች ብቻ እንደቀሩ፣ የተቀሩት እንደተሰደዱ ወይም አካባቢውን ለቀው እንደሄዱ ሪፖርተር በውስጥ ገጹ ሃላፊ አነጋግሮ ዘግቧል።

ችግሩን ለመንግስት ሲያቀርቡ “በሽምግልና ፍቱት” ከማለት የዘለለ መልስ እንደማይሰጣቸው የገለጹት ሃላፊው የአዋሽ ፓርክ ጉዳይ ” ድህና ሰንብት” ወደ ሚባልበት ደረጃ መዳረሱን ፍንጭ ሰጥተዋል። በኢትዮጰያ ሃይቆች እየደረቁ ነው። ደን እያለቀ ነው። ያለውም እየተጨፈጨፈ ነው። ዘገባው እንሆ…

awash-park-ostrichአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ አገልግሎት ወደማይሰጥበት ደረጃ እየሄደ መሆኑ ተጠቆመ
Aየተመሠረበትን 50ኛ ዓመት ከሁለት ዓመት በኋላ የሚያከብረው አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጋጠመው ያለው ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ተግዳሮቶች መቋቋም እያቃተው መሆኑና በዚሁ ከቀጠለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚቸገር አስታወቀ፡፡
በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ቺፍ ዋርደን ተወካይና የጥበቃና ቁጥጥር የጥናትና ምርምር ዋርደን አቶ ሺፈራው መንግሥቱ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአካባቢው የሚኖሩት የአርብቶ አደር ማኅበረሰቦች የፓርኩ ይዞታ ለእንስሶቻቸው የግጦሽ መሬት እያደረጉት በመሆኑ የዱር እንስሳቱ በተለይም ሳላዎች ፓርኩን እየለቀቁ ነው፡፡
የፓርኩ መለያ የሆነው ሳላ ከዓመት ዓመት ቁጥሩ እየቀነሰ መምጣቱ አምና በተደረገው ቆጠራ 182 ሳላዎች መቅረታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያና በአፋር ክልሎች የሚኖሩና ከፓርኩ ጋር የሚጎራበቱትና አርብቶ አደሮች በፓርኩ ይዞታ ውስጥ የሚያሰማሯቸው የቤት እንስሳዎች በሚጥሉት እዳሪ የሚመጣ ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ የሚባለው አረም ፓርኩን እየወረረ መሆኑን አቶ ሺፈራው አስረድተዋል፡፡
በሌላ በኩል የፓርኩ ተግዳሮት የሆነው በተደጋጋሚ ለሁለት ዓመታት የተከሰተው ድርቅ የዱር እንስሳቱ የሚግጡትን ሳር በከፊል አሳጥቷቸው በድርቁ ምክንያት ተገንድሰው የወደቁት የግራር ዘፎች የከሰል አክሳዮች ሲሳይ ሆነው መውደማቸውን የገለጹት አቶ ሺፈራው፣ የጠባቂዎች (ዋርዳኖች) ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ፓርኩን ለመከላከል አልተቻለም ብለዋል፡፡ እንደ ተወካዩ አነጋገር፣ ፓርኩ እያጋጠመው ላለው ችግር በተደጋጋሚ ለበላይ አካል አቤቱታ ቢቀርብም ‹‹በሽምግልና ፍቱት›› ከማለት የዘለለ መፍትሔ ሊመጣ አልቻለም፡፡
‹‹እዚህ ያለነው ዋርደኖች በቁጥር ትንሽ ነን፤ መገናኛ ሬዲዮ የለንም፤ በቅርቡ ሁለት ባልደረቦቻችን ተገለውብን እስካሁን ገዳዩ ማን እንደሆነ የሚጠይቅ አካል የለንም፤›› በማለትም ሥጋታቸውን አልሸሸጉም፡፡ ‹‹አሁን ትልቁ ሥጋታችን በአካባቢ ይሠራል የተባለው ፈጣን መንገድ በፓርኩ ውስጥ እንዲያልፍ መደረጉ ነው›› የሚሉት አቶ ሺፈራው የፍጥነት መንገዱ ፓርኩን በማይነካ መልኩ እንዲገነባ መደረግ አለበት ይላሉ፡፡

Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

awash_pic2ብሔራዊ ፓርኩን ወደ ቀድሞ ይዞታው እንዲመለስ ለማድረግ መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት ይገባዋል ሲሉም አክለዋል፡፡ የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክና የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በአገሪቱ የመጀመሪያዎቹ ፓርኮች ሆነው በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በነጋሪት ጋዜጣ ደንብ በ1961 ዓ.ም. መቋቋማቸው ይታወቃል፡፡
02 Nov, 2016 By ታምራት ጌታቸው Reporter Amharic

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *