ኮማንድ ፖስቱ “ለአርሶ አደሩ ሲባል”የጸጥታ ሃይሎችን ዩኒፎርም ቤት ማስቀመጥንና በእጅ መያዝን ብቻ ፈቀደ፤

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድርገ ዝርፊያ መፈጸሙ ተረጋገጠ። ዲፕሎማቶች ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ተነሳ። በጸትታ ሃይሎች ዩኒፎርም ላይ የተጣለው ገደብ ትርጉም በሌለው ማሻሻያ ተተካ። አዋጁ እንዲሻሻል የተደረገው የተሻለ ሰላም በመፈጠሩ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ብርበራዎችና አካላት በህግ አሰከባሪ ስምና ፣ አንዳንድ የህግ አስከባሪዎች ራሳቸው በዝርፊያ መሰማራታቸውን የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ናቸው ያመኑት። በዚህም መነሻ ህጉ ሲሻሻል የብርበራና የፍተሻ ድንጋጌውን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኗል። በተሻሻለው ህግ መሰረት ብርበራና ፍተሻ በግልጽና ራስን በመግለጽ ይሆናል። ዛሬ ሚኒስትሩ ይህንን ጉዳይ በይፋ ማመናቸው አዲስ ካልሆነ በቀር የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክና ኢሳት በተደጋጋሚ ሲዘግቡ ነበር። አቶ ሲራጅ አንዳንድ ያሉዋቸው የጸጥታ ሃይሎች ላይ ስለተወሰደው ርምጃና የተዘረፋው ንብረት ስለመመለሱ አለተናገሩም። ጥያቄም አልቀረበላቸውም።
ዲፕሎማቶች ከኮማንድ ፓስቱ እውቅና ውጪ ከአዲስ አበባ ክልል 40 ኪሎሜትር አልፈው እንዳይንቀሳቀሱ የሚከለክለው ህግ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል። እገዳውን አስመልክቶ አሜሪካ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማውጣቷን ተከትሎ ቅሬታ መነሳቱ አይዘነጋም። በወቀቱ የአሜሪካን አቁዋም በርካታ አገሮች ስለሚከተሉት በጠቀላላ የቱሪስት ፈሰቱ አደጋ ያጋጥመዋል ተብሎ ነበር። ለዚህም ይመስላል አሜሪካ ውሳኔዋን እንድታሻሽል ተጠይቃ ነበር። የአሜሪካ ውሳኔ ግን ” አንደርገውም” የሚል ሲሆን ጥልቅ ተሃድሶው የገፋቸው አቶ ጌታቸው ረዳ ” ይህ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የሚሰሩ ግልሰቦች ውሳኔ ነው” በለው ነበር። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቱሪዝም ኢንደስትሪው ክፉኛ አደጋ ላይ መውደቁ፣ በርካታ ጎብኚዎች ጉዞ መሰረዛቸውና ሙሉ የጎብኚዎች ፍስት መንጠፉን የተላያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ሚዲያዎች ሲዘግቡ ስንብተዋል።

Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

የህግ አስከባሪዎችን ልብስ መልበስ፣ መሸጥ፣ ለሌላ ወገን አሳልፎ መስጠት ክልክል ሲሆን በቤት ውስጥ ማስቀመጣና ይዞ መገኘት ይቻላል ተብሏል። ድንቡ እንዲሻሻል የተደረገው አብዛኛው አርሶ አደር እንደ መደበኛ ልብስ ስለሚጠቀምበት እንደሆነ አቶ ሲራጅ አስረድተዋል። አብዛኛው አርሶ አደር መደበኛ ልብሱ የጸጥታ ሃይሎች ዩኒፎርም ከሆነ ቤት ማስቀመጥና በእጅ መያዝ ለአርሶ አደሩ ምን ጥቅም እንዳለው አላብራሩም። ጥያቄም አልቀረበላቸውም።

Related stories   “ወያኔ እየሠራው ባለው ግፍና በደል ትግራይ ከፍላ የማትጨርሰው ዕዳ እየተቆለለባት ነው!”ሲሉ ሰምቼ…

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተባለው የስድስት ወር ጊዜ ዘምቻውን እንደሚያሳካ የተጠየቁት ሚኒስትሩ አሁን ላይ ሆኖ መናገር እንደማይቻል በመግለጽ መግለጫቸውን አጠናቀዋል። በተለያዩ ሚዲያዎችና ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ጦርነት ስለመኖሩ በተከታታይ እየዘገቡ ነው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *