ሕዝቡ “ከሁለት ገዳይ ካንሰሮች አንዱን መርጧል”

ለሁለት ዓመታት ያህል ሲካሄድ የቆየው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሪፓብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የምርጫው ውጤት ለሒላሪ ክሊንተን ድምጻቸውን የሰጡ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፡፡ ምርጫው ለአንዳንዶች እንደ ኤርትራው ሕዝበ ውሳኔ “ነጻነት” ወይም “ባርነት” የመምረጥ ያህል ተሰምቷቸዋል፡፡ ይህ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተሻለ አማራጭ የጠፋበትና ከሁለት ገዳይ ካንሰሮች አንዱን የመምረጥ ያህል ነው ተብሏል፡፡

ገና ከጅምሩ በሚሰጡት ከፋፋይ መልዕክት የመመረጥ ዕድል እንደሌላቸው ሲገመቱ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ለዚህ መድረሳቸው በርካታ የሚዲያ ሰዎችንና የፖለቲካ ተንታኞችን ያስደመመ ነው፡፡ ትራምፕ ፓርቲቸውን ወክለው ለመወዳደር ዕድል ካገኙ በኋላ እንኳን በታዋቂ ሪፓብሊካን ድጋፍ ተነፍጓቸው ቆይተዋል፡፡ ከዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ሒላሪ ክሊንተን ጋር በምርጫ ዘመቻ በነበሩበት ጊዜ አብዛኛው ትራምፕ ያደረጓቸው ንግግሮችና ያለፈው ታሪካቸው ያለመመረጥ ዕድላቸውን ያሰፋ መስሎ ታይቶ ነበር፡፡2016-11-09 (9).png

ለሴቶች ያላቸው አመለካከት እስከ ማባለግ የደረሰ መሆኑ፤ በአብዛኛው በምርጫ ዘመቻና በፕሬዚዳንታዊ ክርክሩ ወቅት ከፖሊሲ ንግግሮች ይልቅ የዘለፋና የነቀፋ ንግግሮችን ማድረጋቸው፤ “አሜሪካንን እንደገና ታላቅ እናድርግ” ከሚለው የምርጫ መፈክር በስተቀር ይህ ነው የሚባል የአገር ውስጥና የውጪ ፖሊሲ አቋማቸውን ያላሳዩ መሆናቸው፤ አንዲት ቀን እንኳን በመንግሥት ተቋም ውስጥ ለሕዝብ አገልግሎት ሰጥተው የማያውቁ መሆናቸው፤ ወደ አሜሪካ ለገቡ እና ወደፊት ለሚገቡ ስደተኞች የሚናገሯቸው ጽንፈኛ አመለካከቶች፤ ወዘተ ትራምፕ የመመረጥ ዕድላቸው ያነሰ መሆኑን በተለይ በሚዲያው ሲስተጋባ ቆይቷል፡፡

ከዚህ በተጻጻሪ ደግሞ በአብዛኛው የሚዲያው ድጋፍ የተቸራቸው፣ የባራክ ኦባማና የትዳር ጓደኛቸው እንዲሁም የባላቸው ቢል ክሊንተን ድጋፍና የምርጫ ዘመቻ የተደረገላቸው፤ በሌሎች ታላላቅ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አመራሮች ከፍተኛ ድጋፍ የነበራቸው፤ በሴትነታቸው የበርካታ ሴቶችን ድምጽ የማግኘት ዕድል እንዳላቸው የተነገረላቸው፤ እጅግ በርካታ ለሆኑ ዓመታት በመንግሥት ሥራ ላይ እንዲሁም የሕዝብ ተመራጭ በመሆን መሥራታቸው በሰፊው የተወራላቸው፤ ለዓመታት ያካበቱትን የአገር ውስጥና የዓለምአቀፍ ልምድ በፕሬዚዳንትነት ለከፍተኛ ጥቅም ያውሉታል ተብለው የተጠበቁት፤ በወንዶች ተይዞ የነበረውን የመስታወት የሥልጣን ጣሪያ በርቅሰው በመውጣት ለወደፊት ሴቶች ተስፋ ይሆናሉ ተብለው የተጠበቁት ሒላሪ ክሊንተን በፍጹም ያልጠበቁትን የሽንፈት ጽዋ ተጎናጽፈው ደጋፊዎቻቸውንም እጅግ አስለቅሰዋል፡፡

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

ዶናልድ ትራምፕ ለመራጮቻቸው ምሥጢራዊ መልዕክት አስተላልፈዋል በማለት አስተያየታቸውን የሚሰጡ ፈርጀ ብዙ የሆነው “አሜሪካንን እንደገና ታላቅ ማድረግ” የሚለው የምርጫ መፈክራቸው ለደጋፊዎቻቸው ተገቢውን መልዕክት አስተላልፏል ይላሉ፡፡ ይህ አሜሪካንን እንደገና ታላቅ የማድረግ ዘመቻ በሥራ ማጣት፣ በኢሚግሬሽን፣ በኢኮኖሚ ድቀት፣ ሥራቸው ወደ ኢሲያ አገራት በመሄዱ በስቃይ ለሚገኙ፣ በኦባማ ጥላቻ ባደረባቸው፣ … ላይ ተስፋን የጫረ ብቻ ሳይሆን ክብርንም የሚመልስ ተደርጎ ታይቷል፡፡

እስከ ምርጫው ቀን በተካሄደው የሕዝብ አስተያየት በአብዛኛው ክሊንተን ሲመሩ ቆይተው ትራምፕ ማሸነፋቸው በተለይ የሚዲያ ሰዎችን ያነጋገረ ሆኗል፡፡ ከተሰጡት በርካታ ምክንያቶች መካከል አንዱ መራጮች ለሕዝብ አስተያየት (ፖል) ሲጠየቁ ትክክለኛ ምርጫቸውን አለመናገራቸው ነው ተብሏል፡፡ ምክንያቱም እንደ ትራምፕ ዓይነቱን ዕጩ በግልጽ እደግፋለሁ ብሎ መናገር ለብዙዎች በተለይም ክሊንተንን ለመምረጥ ላልወሰኑ መራጮች የሚያኮራ ባለመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ለወራት ሲወሰዱ የነበሩት የሕዝብ አስተያየቶች ትክክለኛ የሕዝቡን የምርጫ ፍላጎት ጠቋሚ እንዳልነበሩ ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል ከቢል ክሊንተን የአርካንሳስ አገረ ገዢነት ጀምሮ እስከ ኋይትሃውስ ከዚያም በውጭ ጉዳይ ሚ/ርነት ዘመን ድረስ ከባላቸው ጋር በመሆን ፈጸሟቸው የሚባሉ እስከ ነፍስ ማጥፋት የዘለቁ ሕገወጥ ተግባራት፤ በሊቢያ የነበሩት የአሜሪካ ዲፕሎማት መገደል፤ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር የሥልጣን ዘመናቸው ጠፉ ወይም ተሰረዙ የተባሉት የኢሜይል መልዕክቶች እና ከዚያ ጋር ተያይዞ የተናገሩት ውሸት እንዲሁም ለመራጮቻቸው በተለይም እርሳቸውን ለመምረጥ ላልወሰኑቱ ከዶናልድ ትራምፕ የተሻሉ ዕጩ መሆናቸውን በበቂ መረጃ ያለማቅረባቸው የመራጮቻቸውን በተለይ ትራምፕን ለመምረጥ ፍላጎት ያልነበራቸውን ድምጽ እንዳያገኙ ካደረጓቸው ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

trump-and-clinton-e1478752176860-948x474እንደ ቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ከቀድሞዎቹ አውሮጳ ነገሥታት ጋር ቀጥተኛ የደም ትስስር እንዳላቸው የተነገረላቸው ትራምፕና ክሊንተን ለዚህ የአሜሪካ ምርጫ የቀረቡበት ሁኔታ “ነጻነት” ወይም “ባርነት” ይል እንደነበረው የኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ታይቷል፡፡ በሌላ አነጋገር የአሜሪካ ሕዝብ ከሁለት ገዳይ የካንሰር በሽታዎች አንዱን እንዲመርጥ የተገደደበት ሁኔታ በሚል ይህንን ምርጫ የሚተቹ ይናገራሉ፡፡ ሁለቱም ብዙ የሚያስወቅሷቸው ተግባራት መኖራቸውና በተለይ ዶናልድ ትራምፕን ለመምረጥ ፍላጎት የሌላቸው ሒላሪ ክሊንተንን አሳማኝ ዕጩ ሆኖ አለማግኘታቸው ክሊንተንን የጎዳ ቢሆንም ከሁለቱም አንዱ ያነሰ ክፉ (lesser evil) እንዳልሆኑላቸው አስተያየት ሲሰጡ ተሰምተዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ሥልጣን ከያዘ በኋላ እንደ መለስ ዓይነቱን የለየለት ኮሙኒስታዊ አምባገነን “የአፍሪካ የሕዳሴ መሪ” በማለት የሰየሙት የቢል ክሊንተን ባለቤትና ከባላቸው እምብዛም ያልተለየ ፖሊሲ እንደሚኖራቸው የተጠበቁትን ሒላሪ ክሊንተንን በርካታ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵውያን መደገፋቸው ለአንዳንዶች ያልተዋጠ ተግባር ሆኗል፡፡ በተለይ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዴሞክራቱ ኦባማ የህወሃትን ምርጫ “ዴሞክራሲያዊ” በማለት በህዝብ ላይ መቀለዳቸው እየታወቀ ኢትዮጵውያኑ ሒላሪን መደገፋቸውና መምረጣቸው ግራ ጋባ ሆኗል፡፡ አሁንም የዚህ ምክንያት እንደ ኤርትራው ሕዝበ ውሳኔ ጉዳዩ የ“ነጻነት” ወይም የ“ባርነት” ዓይነት ስለሆነባቸው ነው የሚል አስተያየት ይሰጣል፡፡

የትራምፕ በፕሬዚዳንታዊ መንበሩ ላይ መቀመጥ የአሜሪካንን የውጪ ፖሊሲ በተለይ በአፍሪካ ላይ የሚኖረውን እምብዛም እንደማይቀይር ይነገራል፡፡ “አዲስ የዓለም ሥርዓት” በሚል የፖለቲካ አመለካከት ህወሃትን በሥልጣን ላይ እንዲቀመጥ ካደረጉት ሪፓብሊካኑ 41ኛው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ጀምሮ ቀጥሎም በነሱዛን ራይስ አማካሪነት ህወሃትን ሲያቀማጥሉ የነበሩት ቢል ክሊንተን በኋላም ጆርጅ ደብሊው ቡሽ አሁን ደግሞ ህወሃትን “ዴሞክራሲያዊ” እስካሉት ኦባማ ድረስ የአሜሪካ የውጪ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ላይ ሲለወጥ አልታየም፡፡ በትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ዘመንም ይለወጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ነገር ግን ህወሃትን ልክ እንደ አድዋ ልጅ የሚደግፉት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አመራሮች፣ እንደነ ሱዛን ራይስ ዓይነት ባለሥልጣናትና ሌሎች የህወሃት አቀማጣዮች ከኦባማ ጋር አብረው ጥር ወር ላይ መውጣታቸውና በትራምፕ ሠራተኞች መተካታቸው ለህወሃት አሁን አገር ውስጥ ካለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር ተዳምሮ የማገገሚያውን ጊዜ ያስረዝምበታል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ህወሃትን በማንገሳቸው ቁጭት ላይ የሚገኙ የቀድሞ ባለሥልጣናት ጋር በመተባበር የውትወታ (የሎቢ) ሥራ የማከናወኑ ጉዳይ ካሁኑ መጀመር እንዳለበት አንዳንድ ወገኖች ሃሳባቸውን ይሰጣሉ፡፡

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ሕዝብ የፈለገውን መርጧል፤ ትራምፕ መራጮቻቸውን ለማስደሰት ይሁን ከልባቸው ለሕዝብ እጅግ በርካታ ተስፋዎችን ገብተዋል፡፡ በሥልጣን መንበሩ ላይ ከተቀመጡ ከ100 ቀናት በኋላ ያደረጓቸው ወይም ለማድረግ የሚያቅዷቸው ነገሮች የቀጣዩ አራት ዓመታት ጉዟቸውን የሚተነብዩ ይሆናሉ፡፡ ከዚያ በፊት ግን ባራክ ኦባማ አሜሪካዊ ዜግነታቸውን ለተጠራጠሩትና በይፋ በዚህ ጉዳይ ላይ ሲናገሩ ለነበሩት ለዶናልድ ጄ. ትራምፕ ሥልጣናቸውን በይፋ ያስረክባሉ፡፡ ከኦባማ የማንነት ጥያቄ ጀምሮ እስከ “አሜሪካንን እንደገና ታላቅ ማድረግ” ድረስ ታላቅ ተስፋ የገባው የትራምፕ አመራር ጥር 12፤ 2009 ሥራውን ይጀምራል፡፡ ከዚያ በፊት ግን በትራምፕ ዩኒቨርሲቲና በሌሎች ጉዳዮች ዶናልድ ትራምፕ ፍርድቤት ይቀርባሉ፡፡trumpweddingyayclintons-300x194

አሜሪካ እጅግ በርካታ የፖለቲካ ድራማ የሚካሄድባት አገር ናት፡፡ ዴሞክራሲ፣ ምርጫ፣ የሕዝብ ድምጽ፣ … የሚባሉት ነገሮች እንዳሉ ሆነው 32ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ስለ ፖለቲካ ያሉትን ማስታወሱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቨልት እንዲህ ነበር ያሉት፤ “በፖለቲካ ዓለም በድንገት የሚከሰት ነገር የለም፤ ካለም የተከሰተው እንደዚያ እንዲሆን ታቅዶ ስለመሆኑ መወራረድ ይቻላል”፡፡

Credit – http://www.goolgule.com/the-usa-election-like-the-eritrean-referendum/

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *