– የእስረኞች ቁጥር በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩትን እስረኞች አያካትትም

ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል 11 ሺህ 607 ተጠርጣሪዎች ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አስታውቋል። ኢዜአ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ወርዶፋን ጠቅሶ እንደዘገበው

ለእስሩ ዋነኛ ምክንያት ሆነው የቀረቡት ሁከት መፍጠር፣ ሁከት ማስነሳት፣ ሽብር መንዛትና አለመረጋጋትን መፍጠር፣ የግለሰቦችንና ህዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማቃጠል፣ ኢንቨስትመንትን ማውደም፣ የመንግስት፣ የህዝብና የግለሰቦችን ንብረት መዝረፍና ማቃጠል፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ማድረግ፣ መንገድ መዝጋትና ተሽከርካሪዎችን ማውደም፣ በቦምብና በጦር መሳሪያዎች በጸጥታ ሀይሎች ላይ ጥቃት ማድረስና መግደል በሚሉት ከሶች ተጠርጥረው ነው።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ብሄራዊ ሰንደቅ አላማን በመቅደድ እና በማቃጠል፣ የአሸባሪ ድርጅቶችን ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ፣ የአሸባሪ ሀይሎችን የሽብር ቅስቀሳ መዕልክቶችን በማሰራጨት፣ ህገወጥ የጦር መሳሪያ መነገድና በማዘዋወር፣ ለፀረ ሰላም ድርጊት እንዲውል በማድረግ፣ አጥፊዎችን በመደበቅ እና በመተባበር እና ነውጡን በግንባር ቀደምትነት በመምራት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ እንደሚገኙበትም የዜና አግልግሎቱ ጠቁሟል። 2013_ethiopia_maekelawi

ፎቶ የሂይውማን ራይትስ ዎች ሲሆን፣ ቦታው ማዕከላዊን በሳተላይት የሚያሳይ ነው

1. በአዋሽ ማዕከል፦ ከፊንፊኔ ዙሪያ፣ ከሰሜን ሸዋ፣ ከምስራቅ ሸዋ ዞኖች / ወንድ – 1 ሺህ 172 ሴት 2 ድምር 1 ሺህ 174
2. በጦላይ ማዕከል፦ ከቄለም ወለጋ፣ ከአርሲ፣ ከምዕራብ አርሲ፣ ከምስራቅ ሸዋ ዞኖች / ወንድ 4 ሺህ 193 ሴት 136 ድምር 4 ሺህ 329
3. በዝዋይ አላጌ ማዕከል፦ ከጉጂ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ምስራቅ ሀረርጌ፣ ከጉጂ ዞኖች /ወንድ 2 ሺህ 957 ሴት 91 ድምር 3 ሺህ 048
4. በዲላና ይርጋለም፦ ከጌዲኦ አካባቢ / ወንድ 2 ሺህ 104 ሴት 10 ድምር 2 ሺህ 114
5. በባህር ዳር ማዕከል፦ ከሰሜን ጎንደር፣ ከደቡብ ጎንደር፣ ከምስራቅ ጎጃም፣ ከአዊ ዞኖች/ ወንድ 441 ሴት 91 ድምር 532
6. በአዲስ አበባ ማዕከል፦ ከአዲስ አበባ የተያዙ/ ወንድ 393 ሴት 17 ድምር 410

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

የታሳሪዎች ስም ዝርዝራቸው በየክልሉ መስተዳደር አማካኝነት ለዞኖች እና ለወረዳዎች ተልኮ የሚለጠፍ መሆኑ ተመልክቷል:: በሌላ በኩል መቼና እንዴት የፍርድ ሂደቱ እንደሚታይ አልተገለጸም። የተቀናቃኝ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አካሄዱ በአገሪቱ ሰላም እንደማያመጣ በተደጋጋሚ እየወተወቱ ነው። አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አገራትና የአውሮፓ ህብረት አገሪቱን እየመራ ያለው ኢህአዴግ አሁን ከያዘው አገባብ ይልቅ ለሕዝብ ጥያቄ መልስ ሊሰጥ እንደሚገባ ማሳሰብና መምከራቸው አይዘነጋም።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

አሁን ይፋ የሆነው የታሳሪዎች ቁጥር ቀደም ሲል በአገሪቱ ያሉትን ታሳሪዎች አያካትትም። በዚህም መልኩ ሲታይ ኢትዮጰያ በእስረኞች ብዝት የምትይዘው ደርጃ ከፊት ሊያስቀምጣት ይችላል ተብሎ ይገመታል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *