ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

በርግጥ ብር የለም?ባንኮች ብር የለም እያሉ ነው!! ችግሩ አልታወቅም

የግል ባንኮች “ ብር የለም ይላሉ ” ንግድ ባንክ ቀጠሮ ይሰጣል
ነጋዴዎች ገንዘባቸውን ከባንክ ለማውጣት ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ አመለከቱ። የግል ባንኮች “ ገንዘብ የለንም” ሲሉ ንግድ ባንክ ቀጠሮ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። የንግድ ስራ ቀጠሮ የማይሰጥ በመሆኑ ስራቸው መስተጓጎሉ በርካቶችን ከባንኮች ጋር እያነታረከ ነው። ለዛጎል መረጃውን የሰጡ እንዳሉት “ ብር የለም ማለት ምን ማለት ነው” ሲሉ ይጠይቃሉ። በመንግስት በኩል ችግሩ ሰለመኖሩ በይፋ የተባለ ነገር የለም። የውጭ ምንዛሪ ግብይት ዋጋ መናርን አስመልከቶ ማስተባበያ ተሰጥቷል።
“ቀድሞውንም አንድ ሰው ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከባን ሲያወጣ ለምን ምክንያት እንደሆነ ይጠየቃል” ሲሉ የሚናገሩት በንግድ ስራ የተሰማሩ የመሳለሚያ አካባቢ ነዋሪ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት በር ላማውጣት ደንበኛ የሆኑበት የግል ባንክ ያመራሉ። የመጀመሪያው ቅርንጫፍ ባንክ የጠየቁት ያህል ብር እንደሌለው ይነግራቸውና ወደ ሌላ ቅርንጫፍ እንዲሄዱ ይመክራቸዋል። በተመሳሳይ ሁለተኛውም ቅርንጫፍ “ ብር የለም” ይላቸዋል። ሶሰተኛ ቅርንጫፍ ሄደው ተመሳሳይ መልስ ሲሰጣቸው ይናደዱና ከሃላፊዎች ጋር ሙግት ይገባሉ።
ቅሬታቸውን የሚገልጹት እኚሁ ሰው “ የባንክ ደንበኝነቴን አቋርጣለሁ” ሲሉ ለሃላፊው ያስረዳሉ። በመጨረሻም ሃላፊው “ ከገንዘብ ቤት ጋር ልነጋገር” ይሉና ቢሮ አስቀምጠዋቸው ይወጣሉ። ሲመለሱ ባለጉዳይ/ ደንበኛ የጠየቁት ያህል ብር እንደሌላ ነገር ግን የተወሰነ ብር መውሰድ እንደሚችሉ ይግለጹላቸዋል። ደንበኛው ሰው የተሰጣቸውን ተቀብለው ሌላውን ከሌላ ባንክ በማከል የፈለጉትን ያከናውናሉ። እሳቸውን መሰል በርካታ ሰዎች በተመሳሳይ እንደሚጉላሉ ያመለከቱት ቅሬታ አቅራቢ፣ “ገንዘብ የለም” የሚለው የባንኮች ምላሽ ግራ የ88393cacfdca4c6436eb458eed62bb18ሚያጋባ እንደሆነና የሚመለከታቸው ክፍሎች ከወዲሁ ምላሽ ሊሰጡበት የሚገባ እንደሆነ ያሳስባሉ። አለበለዚያ የራስን ብር ለማውጣት እንዲህ ያለ መጉላላት ካለ ሁሉም በሂደት ቤቱን ባንክ ቤት ሊያደርገው እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
በተመሳሳይ ንግድ ባንክ ሄደው ገንዘብ ሲጠይቁ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው የሚናገሩ የባንኩ ደንበኛ በበኩላቸው “ የንግድ ባንክን ለዩ የሚያደርገው ቀጠሮ መስጠቱ ነው” ሲሉ ያጋጠማቸውንና ከንግድ ባልንጀሮቻቸው የሰሙትን ያስረዳሉ። እሳቸው እንደሚሉት ብር ለመውሰድ አልተመላለሱም። ችግሩን ተከትሎ የተፈጠረውን ዘዴ ተጠቅመዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ ገንዘቡን አነስ አነስ በማድርግ ከተለያዩ ባንኮች ማውጣት ወይም ለተለያዩ ሰዎች ቼክ በመስጠት የሚፈልጉትን ገንዘብ ያገኛሉ።
የገንዘብ እጥረት ወይስ ሌላ ችግር? በሚል ከዛጎል ለተጠየቁት እነዚሁ ሰዎች አስተያየታቸውን ሲሰጡ “ ችግሩ ሊገባን አልቻለም። ግን ግርግሩ ተካሮ በነበረበት ወቅት በርካታ ሰዎች ገንዘባቸውን አውጥተዋል። ምን አልባት ይህ ችግር ሊሆን ይችላል” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል። ችግሩን አስመልክቶ የመንግስት አካል በጉዳዩ ዙሩሪያ በየትኛውም የመንግስት ሚዲያ ያለው ነገር ባለመኖሩ ከመንግስት ወገን ያለውን ምላሽ ማካተት አልተቻለም።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት እየናረ ያለውን የዶላር ገበያ አስመልከቶ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ዮሐንስ አያሌው ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ኖቬምበር 6 / 2016 ይህንን ብለዋል። ዶላር በጥቁር ገበያ ከ25- 26 ባለው የምንዛሪ ጣሪያ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ የሚያሳየው በርካታ ሰዎች ዶላር በመግዛት መጠመዳቸውን ያሳያል። በውጭ አገር በተለይም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩበት ዋሺንግቶን ዲሲ ዶላር በመሰብሰብ የሚታወቅ አንድ ሰው ከ25 እሰከ 26 ብር እየከፈለ አዲስ አበባ ባሉ ወዳጆቹ አማካይነት በሩን ለሚፈልጉት ሰዎች እንደሚያደርስ የዛጎል የዲሲ ተባባሪ አመልክቷል። አዲስ አድማስ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ያተመው ዜና ከዚህ የሚከተለው ነው።
የዶላር ምንዛሬ በከፍተኛ መጠን እያሻቀበ ሲሆን 1 ዶላር በጥቁር ገበያ ከ26 ብር በላይ እየተመነዘረ ነው ተብሏል፡፡ ለዶላር ምንዛሬ መናር ዋነኛው ምክንያት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና በኢትዮጵያ የዶላር የምንዛሬ መጠን አለመሻሻል መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፤ ዓለም ባንክና አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፤ የዶላር ምንዛሬ እንዲሻሻል የሰጡትን ምክር መንግስት አለመስማቱ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል፡፡
የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው፤ የዶላር ምንዛሬ መናር በአንዳንድ ወቅቶች በሚናፈሱ ወሬዎች ተከስቶ ወዲያው የመጥፋት ባህርይ እንዳለው ጠቁመው፤ ይህ የተለመደና አዲስ ነገር እንዳልሆነ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስለመኖሩ የተጠየቁት ምክትል ገዢው አቶ ዮሃንስ አያሌው፤ እስካሁን ምንም አይነት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳላጋጠመና ባንኮችም በጥሩ ሁኔታ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰው፣ የምንዛሬ ዋጋ ማሻቀቡ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ባለመሆኑ ብዙ እንደማያሳስብ ገልፀዋል፡፡
‹‹የትኛውም አካል ኢትዮጵያ የዶላር ምንዛሬ እንድትጨምር ወይም እንድታስተካክል ምክርም ሆነ አስተያየት አልሰጠም›› ያሉት ምክትል ገዢው፣ በጥቁር ገበያ 1 ዶላር፤ ከ26 ብር በላይ እየተመነዘረ መሆኑን እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ መንግስት ከዶላር ምንዛሬ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም በአግባቡ ለማግኘት ጥረት እያደረገ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ገዢው፤ ህጋዊ ያልሆነ እንቅስቃሴን ለመገደብ የተቀመጠ ህግ መኖሩን አስታውሰው፤ እስካሁንም ብዙ እንቅስቃሴ መደረጉንና እንቅስቃሴው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል አንድ ዶላር በባንክ በ22.6 ብር እየተመነዘረ ይገኛል።

Related stories   የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዲስ የአደረጃጀት ሰነድ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀረበ