ያራ ኢንተርናሽናል ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት መስክ እንዲሳተፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠየቁ
Prime Minister Hailemariam Dessalegn urged the globally respected and widely recognized fertilizer company Yara International to invest in Ethiopia.

The premier held talks today with CEO of Yara International, Svein Tore Holsether, on the possibility for Yara to engage in areas of investment the Norwegian company has been working.

During the discussion, Hailemariam said Yara International CompanYara int’l eying "very large potash mining project" in Ethiopiay will get better benefits if it invests in the production of fertilizer.

The prime minister assured the CEO that his country is ready to provide all the necessary support for the company to facilitate its investments in Ethiopia.

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

He further informed Holsether about the raw material it could obtain from the potash reserve in Afar Regional State.

CEO Holsether said on his part his company is looking potentially for very large potash mining project in Afar region in Ethiopia.

“We had very good discussion with the Prime Minister about the project; and we found out that to be a very productive meeting and a very responsive prime minister”, he added.

Yara has organizations in 50 countries and sales products to more than 150 countries.

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ያራ ኢንተርናሽናል ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት መስክ እንዲሳተፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኩባንያውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ስቬን ቶር ሆልስተርን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እንደተናገሩት ያራ በሚሰራባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች በኢትዮጵያ ቢሰማራ ውጤታማ ይሆናል።

በተለይ ለማዳበሪያ ግብዓትነት የሚያስፈልገው የፖታሽ ማዕድን በአፋር ክልል በስፋት መገኘቱ ለኢንቨስትመንቱ መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል።

ኩባንያው በኢንቨስትመንት ሥራዎች እንዲሳተፍ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸው ውይይቱን የተከታተሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ካሳ ገብረዮሃንስ ገልጸዋል።

የያራ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ስቬን ቶር ሆልስተር በበኩላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጋር በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን በስፋት መኖር ኩባንያው ለሚሰራባቸው ሥራዎች ከፍተኛ ጠቃሜታ ያለው በመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት እንደሚሰጠው አመልክተዋል።

ያራ ከአሞኒያ፣ ናይትሬትስ እንዲሁም ከናይትሮጂን፣ ከፎስፎረስና ከፓታሲየም የተለያዩ የማዳበሪያ ዓይነቶችን በማምረት የሚታወቅ ኩባንያ ነው።

ዋና መቀመጫውን ኖርዌይ መዲና ኦስሎ ያደረገው ያራ ኢንተርናሽናል የናይትሮጂን ማዳበሪያን በማምረት በዓለም ቀዳሚ ኩባንያ ያደርገዋል።

በ50 ሀገራት ማዳበሪያ የሚያመርተው ይኸው ኩባንያ ኖርስክ ሀይድሮ በሚል ስያሜ ነበር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1905 የተመሰረተው።

Source: Fana ,Addis Ababa, November 14, 2016 (FBC)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *