በኢትዮጵያ የተከሰተዉ ድርቅ 10,2 ሚልዮን ሰዎችን ጎድቶ እንደበር የሚታወስ ነው። ይኸው ቁጥር በወቅቱ ቢቀንስም፣ የ9,7 ሚልዮን ሰዎች ህይወት አሁንም አደጋ ዉስጥ መሆኑን የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ መስሪያ ቤት፣ በምህፃሩ «ኦቻ» ትንንት ባወጣዉ ዘገባ አመልክተዋል።

መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶች ይኸው አሳሳቢ ሁኔታ ወደከፋ የሰብዓዊ ቀውስ እንዳይቀየር ምን እየሰሩ ነዉ? መርጋ ዮናስ ዘገባ አለዉ።

በኢትዮጵያ በሃምሳ ዓመት ዉስጥ የመጀመርያ የተባለዉ አስከፊ ድርቅ በመከሰቱ ከ10 ሚልዮን ሰዎች በላይ መጠቃታቸዉ ይታወሳል። በዚያም ላይ ተደርቦ በግንቦትና በሰኔ ወሮች ዉስጥ ሃይለኛ ጎርፍ ባስከተለዉ አደጋ 600,000 በላይ ሰዎች ከቄያቸው መፈናቀላቸው የተመድ የሰባዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ «OCHA» በግዜዉ ዘግቦት ነበር። ተቋሙ ትላንትና ባወጣዉ ዘገባ ከድርቁና ከጎርፉ ጋር ተዳምሮ የተከሰቱት የጤና ችግሮችና ሌሎች መሰረታዊ የማኅበረሰብ አገልግሎቶች መናወጡ አሁንም የ9,7 ሚልዮን ሰዎች ሕይወት ላይ አሉታዊ ተፅኖ ማስቀጠሉን አመልክተዋል።

Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

10,2 ሚልዮን የነበረዉ የተረጅዎች ቁጥር ወደ 9,7 መዉረዱን የሚናገሩት በኢትዮጵያ በብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘዉዴ አሁን ያሉት የተረጅዎች ቁጥር በመንግስትና በ«OCHA» ተከፋፍለዉ ርዳታ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በሚገኘዉ ከሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ኢየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ ባቀርብነዉ ጥያቄ፣ የሃገሪቱን የሰብዓዊ ጉዳይ የሚከታተለዉ ቡድን የመርህ ግዜ ግምገማ እያደረጉ እንደሚገኙና ቡድኑ ሲመለስ መረጃ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነ በላኩልን የኢሜል መልክት ገልፀዉልናል። ይሁን እንጅ ይሄ  የመኸር ግምገማ ምን እንደሆነ አቶ ደበበ አብራርተዋል።

Related stories   ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

በኢትዮጵያ አዲስ ድርቅ ሊከሰት እንደሆነ ባላፈዉ ሳምንት «OCHA» መግለፁም ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶች በዚህ ላይ ምን እየሰሩ ነዉ ለሚለዉ ጥያቄ አቶ ደበበ መልስ ሰጥተዋል።

በሶማሌ ክልል የምገኙ 60 ቀበሌዎችን ጨምሮ አፋር፣በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከፍተኛ የዉኃ እጥረት መከሰቱን «OCHA» በዘገባዉ አመልክተዋል። የሃገሪቱ የሜትርዮሎጂ ኤጀንሲም የሰብዓዊ ችግሩ አስከፊነት እንዳይባባስ ለማድረግ ገበሬዎች የመኽር ግዜ ሰብል ቶሎ ብሎ መሰብሰብ እንዲጀምሩ አሳስበዋል።

Related stories   ሱዳን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደምታነሳ አስጠነቀቀች፤ "ብሄራዊ የጀግንነት ጥሪ ያፈልጋል"

መርጋ ዮናስ – አዜብ  ታደሰ http://www.dw.com/am

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *