የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የመለሰው የህዝብ ጥያቄ አልመለሰም። ነገር ግን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም በመጠቀም ወደ ፓለቲካዊ መፍትሄ ባስቸኳይ መሄድ ይገባል ሲል ኢዴፓ አስጠነቀቀ። የአስጨኳይ ጊዜው ሲነሳ አገሪቱ ተመልሳ ወደነበረችበት ሁኔታ ትመለሳለች በማለት የተናገሩት አቶ ልደቱ አያሌው ሕዝብ ላቀረበው ጥያቄ መላሽ መስጠት ግድ እንደሆነ አመልክተዋል።
“ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ያገባናል ከሚሉ አካላት ጋር ካልተደራደረ አገሪቱ ትፈርሳለች ይህ ጥንቆላ አይደለም” ያሉት አቶ ልደቱ ” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲታወጅ ኢህአዴግ ችግሩን ተረድቷል ብለን ነበር” ሲሉ እየተደረገ ያለው ሁሉ ወደፊት አገሪቱን መከራ ውስጥ እንደሚከታት አመልክተዋል።
አንዳንዶቹ ባለስልጣናት ምንም ነገር እነደተፈጠረ እንኳን ማሰብ አለመቻላቸውን ለቪኦኤ ያስረዱት አቶ ልደቱ ” እንጮሃለን” ሲሉ ጊዜው ዝም የሚባልበት እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ከቅንጀት መክሰም ጋር በተያያዘ ስማቸው የጎደፈው አቶ ለደቱ አያሌው አሁን አሁን ተመልሰው ግንባር እየሆኑ ነው። ፓርቲያቸው ኢዴፓ አንድ ጠንካራ ፓርቲ እንዲመሰረት ጥሪ ማቅረቡም በዜና ተዝግቧል። ኢዴፓ ከሁሉም ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ለመስራትና እስከመዋሃድ ሊደርስ የሚችል ውሳኔ ላይ መድረሱንም ይፋ አድርጓል። የቪኦኤን ዘገባ ያድምጡ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *