በጎንደር ዩኒቨርስቲ መጪው ህይወታቸው ያሳሰባቸውና ጥያቄ ያነሱ ተማሪዎች ታሰሩ። ተማሪዎቹ ላነሱት ጥያቄ በውይይት መፍትሄ መፈለግ ያልተቻለበት ምክንያት አልታወቀም። አሜሪካ ሬዲዮ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዚዳንት ለማናገር በእጅ ስልካቸው በተደጋጋሚ ቢሞክርም ስልኩ ባለመነሳቱ አልተሳካም።

ለደህንነቱ የፈራና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ተማሪ ለቪኦኤ እንደገለጸው የእንሳት ፈርማሲ ትምህርት የስራ እድል አያስገኝም። እንደ እሱ ገለጻ ከዚህ ቀደም በዘረፉ የተመረቁ ተማሪዎች 50 ሲሆኑ ስራ ያገኙት አራት ብቻ ናቸው። አባባሉ ተምረው ስራ በማያገኙበት ዘርፍ ዲግሪ ይዘው ሸክም ከሚሆኑ ከወዲሁ መላ እንዲፈለግ የማሳሰብ ነው።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

ሃሳቡ ይህ ሆኖ ሳለ “የሥራ ዕድሉ በጣም ጠባብ ስለሆነ ዲፓርትመንት ይቀየርልን” በማለታቸው 102 ተማሪዎች በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ታስረዋል። የጎንደር ዩኒቨርስቲ የእንሳት ፈርማሲ ተማሪዎች ከትናንት በስቲያ አርብ መታሰራቸው ሲገለጽ ፎቶ ማንሳት፣ ምግብ መውሰድ፣ ቆሞ ማየት ተከልክሎ ነበር።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ዓመት ያሉ የእንስሳት ሕክምና ፈርማሲ ትምሕርት ክፍል ተማሪዎች ከእነርሱ ቀድመው የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ማግኘት ስላልቻሉ የትምህርት ክፍላቸው እንዲቀየር መጠየቅ ከጀመሩ ሦስት ሳምንት እንዳለፋቸው ለአሜሪካ ድምጽ የገለጸው ይህ ስሙን መናገር ያልፈለገ ተማሪ፣ በሁለት መኪና የተጫኑ የፌደራል ፖሊሶች፣ የክልሉ አድማ በታኞችና የኮማንድ ፖስት አዛዦች ዩኒቨርስቲውን ዘልቀው በመግባት ተማሪዎቹን ሃይል በመጠቀም ወደ እስር ቤት ውስደዋቸዋል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

በዩኒቨርስቲው ውስጥ ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተል እንደነበር የገለፀው ይኸው ተማሪ ተማሪዎቹ መማር ካልፈለጉ ክሊራንስ ሞልተው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስታወቂያ መለጠፉንና በዚህ መሰረት ክሊራንስ ሊሞሉ ሲሄዱ ተሰብስበው ሳለ መታሰራቸውን ነው ያብራራው።

የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የእጅ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምላጫቸው ሊካተት አልቻለም። ይህ የስራ እድል የማያስገኘው የትምህርት ክፍል ከተቋቋመ አምስት ዓመት የሞላው ሲሆን ሲቪል ሰርቪስና ትምህርት ሚኒስቴር በወጉ የማያውቁት እንደሆነ ተመልክቷል። ተማሪው እንዳለው ተመሳሳይ ኮርስ ባለው የፋርማሲ ትምህርት ክፍል እንዲዛወሩ ይፈቀደላቸው ዘንድ አማራጭም አቅርበዋል። ጉዳዩን በጥሞና ከመመርመርና ችግሩን በተቆርቋሪነት ከመመልከት ይልቅ በደፈናው ለእስር መዳረጋቸው ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ያለታሰሩት ሁለት ተማሪዎች አስተያየት ምን እነደሆነ ቪኦኤ አላካተተም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *