” ዶክተር መረራ የጣሱት ህግ የለም ” ሲል በሊቀመንበርነት የሚመሩት ድርጅት ኦፌዴን መግለጫ አሰራጨ። በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አንጋፋ አባል ሴናተር ቤን ካርዲን የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። አዲሱ የምንግስት አፈ ቀላጤ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ  “ህግ ተጥሷል” ሲሉ የመንግስትን አቋም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ና የኦፌኮ መሪ የታሠሩት “የሚመሩት የሰላማዊ ትግል በመንግሥት ላይ ሥጋት ስለፈጠረ ነው” በማለት መግለጫ ያሰራጨው ኦፌኮ መሪው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ የትኛውንም የኢትዮጵያ ህግ አለመጣሳቸውን በማስታወቅ እስሩ አግባብ አለመሆኑንን አመልክቷል።

Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

“መላ ህይወቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰጠ” ሲል አገልግሎታቸውን ያወሳው መግለጫ መረራ አሸባሪዎች ከሚባሉ ክፍሎች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ዓለም፣ ህዝብና ራሱ መንግስት እንደሚያውቅ ባልደረባቸው ተናገረዋል። ባልተለመደ ሁኔታ 10 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን፣ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸውን ተመልከቷል።

መንግሥት በበኩሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሠሩት በሽብርተኝነት ከተፈረጁ አካላት ጋር በመገኘታቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰዋል በማለት በኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮና በኮማንድ ፖስቱ ማካይነት አስታውቀዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አንጋፋ አባል ሴናተር ቤን ካርዲን ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ጋዜጣዊ መግለጫ ያወጡት  ቤን ካርዲን  ዶ/ር መረራ የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በጠራውና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ላይ ትኩረት ያደረገ ሥነ ሥርዓት የምስክርነት ቃል ከሰጡ በኋላ ባለፈው ሳምንት ወደ አገራቸው ሲመለሱ መታሰራቸውን በመግለጫቸው አውስተዋል።

Related stories   “ወያኔ እየሠራው ባለው ግፍና በደል ትግራይ ከፍላ የማትጨርሰው ዕዳ እየተቆለለባት ነው!”ሲሉ ሰምቼ…

ሴናተሩ አያይዘውም ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን፥ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና የሲቪል ማኅበረሰብ ታጋዮችን እንዲፈታ፣ የፖለቲካ ምሕዳሩን ለማስፋት የሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድና እንዲሁም በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎትና አቅርቦቶች ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ፤  ጠይቀዋል።

“የዶ/ር መረራ ጉዲና እስር በመንግስቱ ላይ የሰላ ትችት የሚሰነዝሩ የፖሊቲካ ተቃዋሚ በመሆናቸው ብቻ ነው። በመሆኑም በአስቸኳይ መለቀቅ አለባቸው” ሲሉ ጠይቀዋል። የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች፣ የአውሮፓ ፓርላማና አሜሪካ ቀደም በለው ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። ከተለየዩ አካላት ጫናና ጉትጎታ ቢኖርም መረራ አሁንም እስር ላይ ናቸው። ዛጎል ያናገራቸው  ጡረተኛ የኢህአዴግ አድናቂና ደጋፊ፣ በአስቸኳይ አዋጁ መመሪያ “…አዋጁን ተላልፎ የተገኘን ተገቢ የተሃድሶ ትምህርት በመስጠት መልቀቅ ” የሚል ሃርግ በመጥቀስ መረራ ይለቀቃሉ ሲሉ  ተንብየዋል።

Related stories   “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?

ቪኦኤ ያዘጋጀው ዝርዝር ዘገባ እነሆ

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *