” ኢህአዴግ ዶክተር መረራን ማሰሩ ራሱን ይጎዳዋል። ኢህአዴግ እንደ መረራ አይነት ፖለቲከኞችን በማሰሩ አያተርፍም። ከሳሪውና ተጎጂው ራሱ ነው። ይህ ከእነሱም የተሰወረ አይመስለኝም። ከልተረዱት ተሞኝተዋል። ትግሉን ለጽንፈኞች አቀብለውት ያርፉታል እኛም እናርፋለን  ” በማለት ነዋሪነታቸው ምዕራብ ሸዋ የሆነና በህክምና ስራ የተሰማሩ ባለሙያ አስተያየት ሰጡ። እኚህ ለዝግጅት ክፍሉ ቅርብ የሆኑ የህክምና ባለሙያ በኢትዮጵያ አንድነትና በግለሰቦች መብት መከበር የሚያምኑ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው።

ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት አጭር መልዕክት እንደገለጽት  የዶክተር መረራ መታሰር  ካንገበገባቸው ዜጎች መካከል አንዱ ናቸው። ሃዘናቸው ደግሞ በተራ የኦሮሞነት ቁርኝት አይደለም። ” እኔ ” አሉ እኚሁ የህክምና ባለሙያ ” እኔ ሰዎችን በዘራቸውና በጎሳቸው አልተምንም። መረራን የማከብራቸው ኢትዮጵያ ላይ ባላቸው አቋምና የኦሮሞ ጉዳይ በመላው ኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ የሚታይ፣ መፍትሄ የሚፈለግለት እንደሆነ የተቀበሉና ከሁለት አስርተ ዓመት በላይ በዚሁ አቋማቸው የጸኑ በመሆናቸው ነው”

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

” መረራ የሃይል አማራጭን የማይቀበሉ እንደሆኑ አምናለሁ። ማስረጃም አለኝ” የሚሉት ባለሙያው ፣ የዶክተር መረራ እስር ስርዓቱን የሚጎዳው ስለመሆኑ ምክንያታቸውን ሲያቀርቡ ” እንደ መረራ አይነቱን ሰው ከፖለቲካው ማገድና ማሰር ጽንፈኛ ፖለቲከኞች እንዲያቆጠቁጡ፣ ብቅ ብቅ ያሉትም ስር እንዲሰዱ ያደርጋል”

በመነጋገር የሚያምኑና፣ ጽንፈኛ አቋም የላይዙ ፖለቲከኞች እየተገለሉ በመትካቸው ” ኢትዮጵያ ትበታተን” የሚሉ አካላት በሚሰሙበት በአሁኑ ወቅት እንደ መረራ አይነት ተሰሚነት፣ ታማኝነት፣ እንዲሁም ክህሎትና ልምድ ያላውን ፖለቲከኛ ማሰር ኢህአዴግን ዋጋ እንደሚያስከፍለው በማስታወሻቸው  ጠቁመዋል።

በኦሮሞ ትግል ዙሪያ አሁን አሁን የሚደመጡት ጽንፍ የለቀቁ አስተሳሰቦች እየደረጁ እንዲሄዱ ራሱ ኢህአዴግ እያመቻቸ እንደሆነ በማስታወሻው ተመልከቷል። ቀደም ሲል ጀምሮና ለአንድ ዓመት ያህል መልኩንና ቅርጹን ቀይሮ በመላው አገሪቱ የተካሄደውንና እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ ለማስታገስ የተኬደበት መንገድ መሻከርን እንደፈጠረ ለሁሉም ወገኖች ግልጽ መሆኑንን የሚያስታውሱት የህክምና ባለሙያ ፣ ” ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ትግል አክትሞለታል ” ለሚባለው አስተሳሰብ መንግስት ይሁንታውን እየገለጸ ነው ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞችን የመሳሳት መበትን ጨምሮ በመስጠት ሊያነቃንቃቸው ሲገባ እንዲህ ባለ መልኩ ቋንቋን እስርና ሃይል ላይ ማድረጉ እንደ እኔ ያሉትን ሰዎች ጭምር ያሸፍታል” ሲሉ ስሜታቸውን ያመላከቱት የህክምና ባለሙያ ” መንግስት አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ነገሮች እንዴት እየሄዱ እንደሆነ በርጋታ እንዲያይ እመክራለሁ። አሳስባለሁ። እማጸናለሁ። አስጠነቅቃለሁ” በማለት መልዕታቸውን ሲያጠቃልሉ ” ለሁሉም ቁልፉ በእነሱ እጅ ነው” ብለዋል

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

የኮማንድ ፓስቱ ሴክሬታር ” የፈረሰ አገር መምራት አይቻልም” በማለት የአስቸኳይ ጊዜ መውጣቱንና ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ማስቻል የመንግስት ሃላፊነት ነው በማለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸው አይዘነጋም። አቶ ሲራጅ አያይዘውም ይህ በመሆኑ አንጻራዊ ሰላም መገኝቱና አዋጁ ከታሰበበት ቀን ቀድሞ ሊነሳ እንደሚችል ጥቆማ ሰጥተው ነበር። መረራ የታሰሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፋቸው ነው መባሉን የመንግስት ሚዲያዎችን ዋቢ አድርገን መዘገባችን ይታወሳል።

አሁን አገሪቱን የገጠማትን ፈተና አስመልክቶ ግልጽና ነጻ የፖለቲከኞች ውይይት፣ እንዲሁም ርጋታ የተሞላበት አካሄድ እንደሚያስፈልግ፣ ኢህአዴግ ለሰላማዊ ድርድር ሰጥቶ በመቀበል መርህ በሩን በመክፈት ወደ እርቅ ማምራት ብቸኛ መንገድ እንደሆነ የሚጠቁሙ ገለልተኛ ወገኖች አብዛኛውን ቁጥር እንደሚይዙ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገለጽ መሰንበቱ ይታወሳል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *