ምድብ ሰባትን በመሪነት ያጠናቀቀው ሌስተርስ ሲቲ ፣ ፖርቶን መቋቋም ተስኖት አምስት ግብ ማስተናገድ ግድ ሆኖበታል። ባለፈው ሳምንት በሰንደርላንደ  የተሸነፈው ሌስተርስ አያያዙ እንደ ካሮት ሆኗል። የእንግሊዝ ሻምፒዮና ክብር ባገኘ ማግስት ክፉኛ እየተሸነፈ ያለው ሌስተርስ ሲቲ በፕሪሚያር ሊጉ ወራጅ ቀጠና ሊገባ  በቋፍ ነው።

አሰለጣኝ ራይነሪ ” ሁሉም ነገር በሌስተር ተበላሽቷል” በማለት በተናገሩ የቀናት ለዩነት ውስጥ አምስት ጎል ጠጥተዋል። አብሮ በመከላከልና አድብቶ በካውንተር በማጥቃት እዚህ ግባ በማይባል እንቅስቃሴ ዋንጫ የወሰደው ሌስተርስ ሲቲ በአዲሱ ዘመን እንደማይሳካለት ኳስ የሚአውቁ አስቀድመው ተናገረው ነበር።

የጎል ናዳ ቢወረድበትም ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፉ Leicester can get PSG, Benfica, Bayern Munich, Bayer Leverkusen, Real Madrid or Sevilla  አንዳቸውን ይገጥማል። የውድድሩ ቃል አቀባይና አስተናባሪ ” ሌስተርስ እውነትም ቀውስ ውስጥ ነው” እያለ  ጉዟቸው የሚያበቃበት ሁኔታ መቃረቡን ሲያመላክት ነበር። አሁን የሚፈራው በሊጉ ወደ ወራጅ ቀጣና ገብተው በዓመት ለዩነት የመንከባለል ገድል እንዳያስመዘግቡ ነው።

ሁሌም ኳስ የሚጫወት ቡድን እንጂ መከላክልን መሰረት ያደረጉ ቡድኖች በውጤት ደረጃ ቀጥይነት የላቸውም። ዶርትመንድ ቁልፍ ተጫዋቾቹ እየወጡበት ተንኮታኮተ ሲባል ይነሳል። የዘንድሮው ቡድን አዳዲስና ዝና የሌላቸው ቢሆኑም የሚጫወቱት ኳስ ለባላጋራ የሚጨበጥ አይደለም። ማድሪድን በሜዳው አስቸግረውት ነጥብ ወስደዋል። የጣሊያኑ ተወላጅ ሌስተርስ ሲቲን የመሰረቱብተ ዘዴ ገና ብዙ ያስከፈላቸዋል የሚል ግምት እየበዛ ነው።

Related stories   አምስት ቀናትን በመፀዳጃ ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *