የዛሬው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ውጤት በጎል የታጀበ ነው። አርሰናል የቼልሲን ውጤት እየጠበቀ መሪ ለመሆን በቅቷል። አጅሬው ሳንቼዝ ባያገባም እንደወትሮው ሲያስጭንቅ ነው የዋለው። ማክሰኞ ከኤቨርተን ጋር ላለው ጨዋታ ቁጠባ ይመስላል 16 ደቂቃ ሲቀር ተቀይሯል። ኦዚል ከሰሞኑ ሁሉ ዛሬ የተሸረጠለት ይመስላል። የፈረንሳዩ ዓለም ዋንጫ ላይ ቫንፐርሲ ያገባትን ጎል ያስታወሰች ጎል አስቆጥሯል። ሲመሩ ነበር። ከሁዋላ ተነሰተው 3 በማግባት  በስቶክ ሲቲ ላይ 15ኛውን ተከታታይ ድል ተቀዳጅቷል። በድምሩ 42 ጎል ስቶክ ላይ አስቆጥሯል። የስቶክ አሰልጥኝ 10ኛውን የእንግድነት ሽንፈታቸውን ቀምሰዋል።eboy

ለዚህም ይምስላል ዌንገር ” ለዋንጫ እንጫውታለን” ሲሉ ከድላቸው በሁዋል ተናግረዋል። ሲመራ የነበረው ቡድናቸው አሸንፎ ለመውጣት ያሳየውን ትኩረትና ስሜት በማድነቅ ይኽው ስሜት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። የተሰጠችውን ፍጹም ቅጣት ምት ” ፋወል እምኳን አልነበረም” ሲሉ ለሳቸው አዲስ በሆነ መልኩ አልቢትሩንተቃውመዋል። አርሰናል ማክሰኞ ኤቨርተንን፣ እሁድ ደግሞ ዛሬ 4 የገባበትን ሲቲን በሜዳው ይገጥሙታል።

58871fdc-12e3-46fb-a720-7b62ff6c3f14

በፖርቶ 5 የገባበት ሌስተር ገና በጠዋቱ 3 በማግባት የጋርዲዮላን ጢቢ ጢቢ ጨዋታ ወሃ አፍሠውበታል። ሲቲ እንደ ቡድን የተዘባተለ ነው። የጫወታው ኮሜንታተር ሲተቻቸው ነበር። ለዋንጫ የሚጫውት፣ ክፍተኛ ግንዘብ የከሰከሰ ቡድን፣ በ20 ደቂቃ ውስጥ ጎሎችን ማስተናገዱ ሳይሆን ሲሰሩት የንበረው ስህተት መሪ አልባ ነበር ያስመሰላቸው። ቀደሞውኑ 6 ለውጥ እንደሚያደርግ ያስታወቀው ጋርዲዮላ ጎሎቹ የምጥ ያህል ስላጣደፉት ያሰበውንም ማድረግ አልተቻለውም። ባለፈው ሳምነት ቼለሲን ኳስ ከመግጠም ይልቅ ቦክስ የመረጡት ሲቲዎች የሚጠቀሟቸን ተጨዋቾች ዝም ብለው የለቀቁ ይመስላሉ።3a175e38-f245-47d0-b2a8-db3a61ef1b12

” ሁሉም ነገር ትክክል አይደለም” ያሉት የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ዛሬ ከጠበቁት በላይ ጣፋጭ ድል ተጎናጽፈው ነጣባቸውን 15 በማድረግ ከወራጅ መስመር ትንሽ ፈቀቅ ለማለት ችለዋል። ሰንደር ላንድና ሞይስ አንዴ 3 ቀምሰው እዛው ወራጅ ሳሎን ውስጥ ለመጋደም ተገደዋል። ስዋንሲ ሲቲ ዛሬ ቢያሸንፍም ከወራጅ ጠርዝ መራቅ አልቻለም።

ግብ ግብ ይመሥል የነበረው የሁል ሲቲና የክሪስታል ፓላስ ጨዋታ 3-3  ተጠናቋል። በሁሉም ጨዋታ ማግባት የማይከብደው ፓላስ ጎሉን መጠበቅ ስለማይችል በዘንድሮው ዓመት ሲንገዳገድ ታይቷል። አላን ይህንን ችግራቸውን ከጨዋታ ጨዋታ ማስተካከል አልቻሉም። ባለፈው ሳምን ሊቨር ፑልን ከሁዋላ ተነስቶ 4 በማግባት አብዶ የነበረው ቦርንማውዝ በበርልኔ 3-2 ተሸንፏል። በዛሬው ጨዋታ 29 ጎል የተቆጠረ ሲሆን ቫርዲ ሃትሪክ ሰርቷል።

ሳውዝአምተንን ተለይተው ኤቨርተንን የተቀላቀሉት አሰልጣኝ ኮመን ” ኤቨርተንን ለማሻሻል ጊዜ እፈልጋለሁ” ሲሉ ነበር አስተያየታቸውን የሰጡት። በዋትፎርድ 3-2 ተሸንፈዋል። ኤቨርተንን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ያደርጋሉ የተባሉት አስልጣኝ የትጨነቁ ይመስላሉ። ኤቨርተን የጨለመበት ቡድን ነው የሚመስለው።  ነገ እሁድ ቶተን ሃም ከዩናይትድ የሚያደረጉት ጨዋታ የሚጠበቅ ሲሆን ሊቨርፑል ከዌስት ሃም፣ ቼልሲ ካልባን….

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *