“… thank you for serving your beloved country Ethiopia. You will never be forgotten.May God bless your soul ” እናመሰግናለን!ውድ አገርህ ኢትዮጵያን በማገልገልህ እናመሰግናለን። በፍጹም የምትረሳ ሰው አይደለህም፤ እግዚአብሔር ነብስህን ይባርክ” ከክቡር ተስፋዬ ዲንቃ ህልፈት በሁዋላ ከተሰጡ አስተያየቶች የተወሰደ
ተስፋዬ ዲንቃ እጅግ አስተዋይ እንደነበሩ በርካቶች በህይወት እያሉ መስክረውላቸዋል። በቀለም ባገኙት እውቀት ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮ የረጉና ውብ ስብዕና እንደነበራቸው የሚያውቋቸው በአደባባይ ይናገሩላቸዋል። አገራቸውን የሚወዱና ለተሰጣቸው ሃላፊነት የተጉ እንደነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ያስታውሳሉ። በተሟጠጠ ሰዓት ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሲሾሙዋቸው፣ ቁጭትን የፈጠረ አስተያየት እንዲሰነዘር ምክንያት የነበሩ ሰው ነበሩ!!
ደርግ ከመውደቁ ሁለት ዓመት ግድም የቅይጥ ኢኮኖሚን ሲያውጅ ተስፋዬ ዲንቃን ወደ ሃላፊነት ቢያመጣና እሳቸውን ቢሰማ ኖሮ ሁኔታዎች ሊቀየሩ እንደሚችሉ በጊዜው ተነግሮ ነበር። የተዋጣላቸው ዲፕሎማትና ባለእውቀት ሰው ስለነበሩ አገሪቱን እንደሚጠቀሙ በበርካቶች ዘንድ እምነት ነበር።
Tesfaye Dinka funeral Services Church Service December 10th at 11:30 AM – 1:00 PM Ethiopian Orthodox Tewahedo Debre Meheret St. Michael Cathedral 3010 Earl Place NE Washington, DC 20018 Burial Service will follow at 2 PM Fair-fax Memorial Park 9900 Braddock Road Fair fax, VA 22032 Family will receive guests and family Friday December 9th at 12 PM – 8 PM Saturday December 10th for Lunch following Burial Service at 4 PM-8 PM Sunday December 11th at 11 AM – 5 PM Dama Ethiopian Restaurant Pastry and Cafe 6669 Little River Turnpike Annandale, VA 22003
ተስፋዬ ዲንቃ ን አስመለከቶ ኢትዮጵያ ዛሬ ስለ እሳቸው የጻፈው ገላጭ ሆኖ ስላገኘነው ከዚህ በታች እንዳለ አትመነዋል።