በውስጥ ችግር የሚናጠው ሰማያዊ ፓርቲ አባላቱና አመራሩ ላይ እስር ተጠናከሮ መቀጠሉን ፕሬዚዳንቱ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ገለጹ። ኢንጂነሩ ለጀርመን ሬዲዮ እንዳስታወቁት በባህር ዳርና በደቡብ ወሎ ሀይቅ ከዚህ ቀደም ከታሰሩት በተጨማሪ ሰባት የፓርቲው አመርስሮች ህዳር 27 እና 28 ታስረዋል።የታሰሩት አባሎቻቸውና አመራሮቻቸው የታሰሩበት ምክንያት እስካሁን አይታወቅም።
የደረሳቸውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ስም ጠቀሰው የተናገሩት የፓረቲው መሪ ” ህግ አለ ብለው ለማህበረሰባቸው የሚታገሉ ዜጎች ህይወት አሳዛኝ እየሆነ ነው” ሲሉ በተቆራረጠ ድምጽ ተናገረዋል። ታሳሪዎቹን ” ህይወታቸው ተሰናክሏል። ቤተሰባቸውም ተበትኗል። በእንዲህ ሁኔታ ነው ያሉት” በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነትና እስሩ በማህበራዊ ኑሮ ላይ እያስከተለ ያለውን ሰንካ አሳይተዋል።
በተለያዩ የጦር ካምፖች፣ ብር ሸለቆ፣ ጦላይ፣ አዋሽ አርባ፣ እና የተለያዩ ማከማቻዎች ውስጥ አሉ ከመባሉ ውጪ ፓርቲያቸውም ሆነ ቤተሰቦቻቸው በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ መርጃ እንደሌለው አኢንጂነር ይልቃል አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ መስከረም ማብቂያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲሕ ብቻ ከአንድ መቶ ሐምሳ በላይ የፓርቲዉ መሪዎችና አባላት መታሰራቸውን ይፋ አድርገዋል። በዜናው የምንግስት ምላሽ አልተካተተም። ይሁን እንጂ ሰሞኑን በቪኦኤ ቀርበው ሰፊ ምላሽ ሲሰጡ የነበሩት የመንግስት አፈ ቀላጤ ነገሪ ሌንጮ ታስረው ከነበሩት ውስጥ የተለቀቁ መኖራቸውን አመልክተው፣ አሁን ለጊዜው አሃዙ በእጃቸው እንደሌለ በመግለጽ ወደፊት በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ እንደሚሰጡ ማመልከታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው ” የአስቸኳይ አዋጁ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተግባር ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይፈጥርም” በለው መናገራቸው አይዘነጋም።
በተመሳሳይ ዜና አብዛኞች ቤተሰቦች ለጆቻቸውን ወይም የቤተሰባቸውን አባል ለመጠየቅ መቸገራቸውን፣ በዚህም የተነሳ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን በተለያዩ ሚዲያዎች በመናገር ላይ ናቸው።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *