“Our true nationality is mankind.”H.G.

ተመስገን ተከቦ ለ3 ደቂቃ ወንድሙን አየ፤ታሟል

ላለፉት 10 ቀናት ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዳገኙት ቤተሰቦቹ አስታወቁ፡፡ ቤተሰቦቹ “ተመስገን ዝዋይ የለንም ተብለናል” ሲሉ አቤቱቻቸውን ለተለያዩ አካላት ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡ ዛሬ ለጥቂት ደቂቃዎች ተመስገንን መመልከት እንደቻሉና ጤንነቱ መቃወሱን ተናግረዋል፡፡

ጤንነቱ መቃወሱን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል

በጻፋቸው እና ባሳተማቸው ጽሁፎች ክስ ቀርቦበት እና ተፈርዶበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት እስሩን እየገፋ ይገኝ የነበረው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደብዛ መጥፋት የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ፡፡ ከሰብዓዊ መብት ተቋማት እስከ ጋዜጠኛ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ለጉዳዩ አጽንኦት ሰጥተው መግለጫ እስከ ማውጣት እና በማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ እስከመክፈት ደርሰዋል፡

የተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች በዝዋይ ማረሚያ ቤት “ተመስገን እዚህ የለም” ተብለናል ካሉበት ቀን አንስቶ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ባሉ የተለያዩ እስር ቤቶች ጋዜጠኛውን ሲያፈላልጉ ቆይተዋል፡፡ ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤትም በየቀኑ በመሄድ ጥያቄቸውን በተደጋጋሚ አቅርበዋል፡፡ እስከዛሬ ረፋድ ድረስ ግን ያገኙት የነበረው ተመሳሳይ ምላሽ “የለም” እንደነበር ሲገልጹ ነበር፡፡

ዛሬ ዓርብ ታሕሳስ 7 ከአዲስ አበባ ወደ ዝዋይ ተጉዞ የነበረው ወንድሙ አላምረው ደሳለኝ ግን አምስት ደቂቃ ላልሞላ ጊዜ ተመስገንን አግኝቶት እንደነበር ለዶይቸ ቨለ ገልጿል፡፡ ወንድሙን እንዴት ለማየት እንደተፈቀደለት በዝርዝር ያስረዳል፡፡

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

“ከበር ላይ ጠብቅ ቆይ ተባልኩኝ፡፡ ከዚያ ተደዋወሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ይዘውኝ ሄድን፡፡ በፊት በምንጠይቅበት አይደለም፡፡ በሌላ ቦታ ነው፡፡ ገባን፣ አስጠሩት፣ ጠየቅን፡፡ ከሶስት ደቂቃ እንኳ ያልበለጠ ነው፡፡ ምንም ነገር ያወራነው የለም፡፡ ሰባት ስምንት ፖሊሶች አጠገባችን አሉ፡፡ ስንቅ አልያዝንም፡፡ ሰላምታ [ተለዋወጥን]፡፡ ‘ጤንነትህን ስለው?’ ‘ጨጓራዬን በጣም እያመመኝ ነው’ ያለው፡፡ ሌላው በሽታም እንዳለ ነው- ወገቡም፣ ጆሮውም፡፡ ‘ሌላውን ምን ትጠይቀኛለህ?’ ነው ያለኝ፡፡ ‘ጆሮዬንም ያመኛል፤ ህክምና የለም፤ ግን ጨጓራዬን አሁን በጣም እያመመኝ ነው’ አለ፡፡ አሁን ካልኩህ ውጭ ምንም ነገር ማውራት አትችልም፡፡ ተከብቦ ነበር፡፡ ” ሲል የነበረውን ሁኔታ ገልጿል፡፡

የተመስገን ቤተሰቦች ከዚህ ቀደም “መጎብኘት አትችሉም” በሚል ተከልክለው እንደሚያውቁ እንጂ እንዲህ እንዳሁኑ “ጭራሹኑ በዝዋይ ማረሚያ ቤት የለም” የሚል ምላሽ አጋጥሟቸው እንደማያውቅ ይገልጻሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በተለይ የ70 አመት አዛውንት የሆኑትን የተመስገንን እናት ለከፍተኛ ጭንቀት እና ህመም ዳርጓቸው እንደነበር አላምረው ይናገራል፡፡ ተመስገንን በኋላም በቀጥታ የደወለው ወደ እርሳቸው ነበር፡፡

“መጀመሪያ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ ሰልኬን ስቀበል ወደ እናቴ ጋር ነው የደውልኩት፡፡ ‘አገኘሁት’ ብቻ ስላት ለረጅም ጊዜ ነው እልል ያለችው፡፡ ጠዋት ስወጣ እንደውም ‘ልጁ ቅዱስ ሚካኤል አባቱ ነው፤ ለእርሱ ሰጥቼያለሁ ከዚህ በኋላ እኔ አቅም የለኝም’ ብላ ነበር፡፡ እናቴ ስለሆነች አይደለም፡፡ ማውራት ሁሉ የለ፡፡ በጣም ተጎሳቁላለች፡፡ በጣም ትጨነቃለች፡፡ እንቅልፍ የለም፣ ጭንቀት ነው፡፡ አሟት ሁሉ ነበር፡፡ ከሦስት ቀን በፊት ሀኪም ቤት ሁሉ ወስደናታል፡፡ ዶክተሩ ‘ምንም ነገር የለም፤ አትጨነቁ’ ነው ያለው ግን የእርሷ ሁኔታ በጣም ይከብድ ነበር” ሲል እናቱ ያሳለፉትን አስጨናቂ ቀናት መለስ ብሎ ያስታውሳል፡፡

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ተመስገን ደሳለኝ መገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር ፈጽሟል በሚል ሦስት ዓመት እስራት የተበየነበት በጥቅምት 2007 ነበር፡፡ ሁለት ዓመት ከአንድ ወር በእስር ያሳለፈው ተመስገን አመክሮ ቢጠበቅለት ኖሮ ከእስር ተፈቺ እንደነበር ቤተሰቦቹ ይናገራሉ፡፡ ዓለም አቀፉን የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት (ሲፒጄን) ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተቋማት ጋዜጠኛው ሀሳቡን በነጻነት በመግለጹ ምክንያት መታሰር እንደሌለበት ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡  ቀደም ሲል ይህንን መዘገባችን ይታወሳል።

9ኛ ቀን ተመስገን የለም- እናት ” ልጄ ሞቶም ከሆነ ንገሩኝ እርሜን ላውጣ”- የማረሚያ ቤት አስተዳዳሪው ” ያለበትን አላውቀም” ይላሉ

……የጋዜጠኛ ተመስገን እናት ” ልጄ ሞቶም ከሆነ ንገሩኝ እርሜን ላውጣ” ማለታቸውና ቤትሰብ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መውደቁ ተገለጸ። የማረሚያ ቤቶች አስተዳድሪ አቶ ግዛቴ መንግስቱ ” የማውቀው ነገር የለም ” ሲሉ ለወጭ መገናኛዎች መልስ ሰጡ። ዛሬ ዘጠኝ ቀን ሞልቶታል። የምስራቅ አፍሪቃ የሰብአዊ መብት ተከራካሪው ደርጅት ” በጣም እያሳሰበን ነው” ሲል ስጋቱን ገልጿል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለቪኦኤ እንደተናገረው ዛሬ በዘጠነኛው ቀን ወደ ዘዋይ ሰው ልከው ነብር። በተመሳሳይ ” የለም” ተብለዋል። ” እኛን ከጠሉን ብለን ሰው ላክን” ያለው ወንድምየው ተመስገንን ፍለጋ ያለገቡበት ቦታ የለም። የጠቅላይ አቃቤ ህግ የሆኑትን አቶ ጌታቸው አምባዬን ቢጠይቁ ተመስገን ያለበትንና የሚገንበትን ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም።

ላለፉት ሁለት ዓመት ከሁለት ወራት ዝዋይ የተመላለሱት ቤተሰቦች ፍጹም ሃዘን ላይ እንደሆኑ ነው ታሪኩ የተናገረው። ተመስገን የጤናው ሁኔታ የተበላሸና ከጊዜ ወደ ጊዜ የባሰበት ቢሆንም ህክምና አለማግኘቱ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል። በማህበራዊ ገጾች ሰፊ ሽፋን ያገኘው ተመስገን የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቅ በዕረኛ ጋዜጠኛ መሆኑ ይታወሳል።

በተያያዘ ዜና ከአስቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው  ከመኖሪያ አካባቢያቸው ርቀው ስለሚታሰሩ ቤተሰብ ሊያገኛቸው አይችልም። በዚህም የተነሳ ቀላል የማይባል ቀውስ መፈጠሩ እየተሰማ ነው። ተመስገንን አስመልክቶ ላለፉት 9 ቀናት መንግስት በኦፊሳል የሰጠው የተለየ ምክንያት ወይም ማብራሪያ  የለም።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0