“Our true nationality is mankind.”H.G.

‘ኢትዮጵያዊው’ ምሩጽ ይፍጠር አረፈ

“ኢትዮጵያዊ” ሲሉ ያደንቁታል። አገር ወዳድና የዋህ እንደሆነም በአብዛኞች ይመሰክሩለታል።  በቅርቡ “ሞተ” ተብሎ ያልተጣራ መረጃ መተላለፉን ተከትሎ “ለቤተሰቦችህ ምን እንበልልህ?” ተብሎ ሲጥየቅ ” መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቤተሰቤ ነው”  ማለቱ አይዘነጋም። ምሩጽ ማረፉን ልጁ ቢኒያም ማረጋገጡን ጌጡ ተመስገን የሚባለው የፌስቡክ እንደምተኛ አስነብቧል።

ምሩጽ የጅግና አሸኛኘት ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል። አዲሱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሃይሌ ገብረስላሴም ለታሪኩን ዋጋ መልኩና ለመጪው ትውልድ መማሪያ የሚሆን “ኢትዮጵያዊ” መታሰቢያ እንዲዘጋጅለት ከወዲሁ ሊሰራ ይገባል። ኦሊምፒክ ኮሚቴም ቢሆን የምሩጽን ጀግነነትና አገር ወዳድነት ለዘላቂው ሊዘክር የሚችል መታስቢያ እንዲዘጋጅለት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መሪ ሆኖ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ የብዙዎች እምነት ነው።

Related stories   መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

ጀግናው ምሩፅ ይፍጠር  በ1982 እ አ አ ሞስኮ ላይ በተካሄደው ኦሎምፒክ በ10,000 እና 5000 ሜትር ተወዳድሮ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ያስመዘገበ ባለገድል ነው። አትሌቱ በአጨራረስ ብቃቱ የተነሳ “ማርሽ ቀያሪው” የሚል ቅፅል ስምም ተሰጥቶታል። ምሩፅ በ1972 እ አ አ በተካሄደው የሙኒክ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

ምሩጽ በ1965ቱ የመላ አፍሪካ ጨዋታ በ10,000 የወርቅ ፤ በ5000 ሜትር ደግሞ የነሃስ ሜዳልያ ለሀገሩ ማስገኘቱም የሚታወስ ነው። በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታም በ5000 እና በ10,000 ሜትር ሁለት ወርቅ ማስመዝገቡ አይዘነጋም። አትሌት ምሩፅ በአትሌቲክስ በአጠቃላይ ከ410 በላይ ውድድሮች የተሳተፈ ሲሆን፥ በ210 ውድድሮች በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል። አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ጤናው በመታወኩ በውጭ ሀገር ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል።

Related stories   መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

አትሌቱ በ73 ዓመቱ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው። ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ  መጽናናትን እንመኛለን።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0