ዛሬ ድረስ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረውና የዘመናችን የፖለቲካ ትኩሳት እምብርት የሆነው የፍልስጤምና የእስራኤል ፍጥጫ ከባጡ ወደ ቆጡ ሆኖ ቅርቃር ውስጥ ገብቶ የቀረው እንዲህ ነው። ከስድስቱ ቀን ጦርነት በፊት አንጻራዊ የመሬት ይዞታ የነበራቸው ፍልስጤማውያን ቀስ በቀስ እያደገ የመጣውን የእስራኤላውያን የመሬት ፍላጎት ለመግታት አለመቻላቸው እና ለዚህም የሚያበቃ ብሄራዊ ቁጭት ማጣታቸው ያበሳጫቸው እንደ ጃዋር ሳይሞቁ የፈሉ የፍልስጤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች አዲስ አይነት የውሽት የፕሮፓጋንዳ ስልት ለመጠቀም ይወስናሉ። ይኸውም “የእስራኤል መንግስት የሚያሳየውን የወረራ ፍላጎት ካሁኑ መገታተር ከልተጀመረና ዝም ከተባለ ወታደሩ ፍልስጤማውያንን ከእርስታቸው ጠራርጎ ለማጥፋት የሚያስችል የኬሚካል እና ባዮሎጅካል ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ መታጠቁን የሚያሳይ ጥብቅ መረጃ እንደደረሳቸው” በሬዲዮው ቀን ከሌት በመለፈፍ የፍልስጤማውያንን ቀልብ ለመግዛትና ለተሻለ ተጋድሎ ለማዘጋጀት ፕሮፓጋንዳውን መለፈፍ ይጅመራሉ። ለጽድቅ ያሉት ነገር ለጥፋት ሆነና ጭራሽ ይህን ዜና የሰሙ ፍልስጤማውያን እልህ ውስጥ መግባቱ ቀርቶ “ማምሻም እድሜ ነው” በሚል ዘር ማንዘራቸውን እየያዙና ሻንጣቸውን እየሸከፉ እርስታቸውን ለጭርሱ ለቀው ወደ ዮርዳኖስ ደማስቆና ወደ መሳሰሉት አገሮች እግር አውጭኝ ብለው ወጥተው ሄዱ። ያን ግዜ ሲወጡ ሰባት መቶ ሺህ ያህል ነበሩ። ወደ ግማሽ ምእተ አመት ያህል በስደት አገር ኑሮ ሲገፉ ተመልሶ መግባቱም የማይቻል ሆኖ እርስት አልባ አገር አልባ ሆነው እንደወጡ ቀርተዋል። አሁን ወደ አስር ሚሊዮን ይጠጋሉ ይባላል።ባጣም የሚያሳዝነው የእርጥብ አቃጣይ የሆነው የፖለቲካ ትርፍ ለመዛቅ ሲገፉ የነበሩት የፓን አረቢያን አራማጆች ከሁከቱ ማትረፍ ቢሳናቸው አንድም የአረብ ሊግ አባል የሆነ አገር ለአንድም ፍልስጠማዊ የዜግነት ፓስፖርት እንዳይሰጥ ቃል በቃል ተማምለው በደረቀ መሬት ላይ ከኪስ የተበተነ ቆሎ አድርገዋቸው ሲኖሩ ግማሽ ምእተ አመት ሆኖዋቸውል።

እነጃዋር ይዘውት የተነሱት የኦሮሞ ንቅናቄ በሜጫና ቱለማ ተጀምሮ ለግማሽ ምእተ አመት ሲቀነቀን ከኖረው የኦነግ ጥያቄ በመሰረታዊ ባህሪውም ሆነ በመፍትሄ አሰጣጡ ዙሪያ ይለያያል።ከስነ መሰረቱ በወለጋ ጴንጤ ቆስጤዎች የተጀመረው የኦሮሚያ ምስረታ ጽንሰ ሃሳብ ሁለት ትውልድ ያህል ዋጋ አስከፍሎ አንድ መንደር ሳይቆጣጠር መጨረሻ ላይ እንታደጋለን የሚሉትን ህዝብ ለአንድ አንሳ ቡድን መጫዎቻ ይሆን ዘንድ ያለ ደረሰኝ ሸጠው የያኔው መሪዎቹ ዛሬ አያቶች ሆነው በምእራብ አገር አደባባዮች እንደ ዞምቢ በከዘራ ይጎተታሉ።”ጦር ሰንቄ ዘገር እነቀንቃለሁ” ብሎ ወደ ኤርትራ የወረደው አቦ ዳውድም ቢሆን የሃማሴን ሴት አግብቶና ዳቦ ቤት ከፍቶ የሽቢያ ጀነራሎች የማይነዱትን ውድ ላንድሮበር እየነዳ አስመራ ኮኛክ እየጠጣ መኖር ከጀመረ አስራዎቹን አመታት አስቆጥሯል።

በአዲሶቹ የኦነግ አልጋ ወራሾች ግምገማ የኦሮሚያ ነጻነት ህልው መሆን ያልቻለው በቀድሞዎቹ ልሂቃን ነን ባዮች የፖለቲካ ትንታኔ ድክመት ነው ብለው አያምኑም። ይልቁንም ሰፊ መሬትና ትልቅ ቀጥር ያለው ህዝብ ይዘው የትም ያልደረሱት ዘራቸውን ብቻ ማእከል ተደርጎ የተዘረጋው ትግል መስመር ትግሉ የሚጠይቀውን ቀንበር ለመሸከም የሚያስችል የብሄርተኝነት ስሜት ለመፍጠር በቂ አይደለም ባዮች ናቸው። በነርሱ እምነት ይኽ ትግል የሚጠይቀውን የመስዋእትነት ዋጋ ለመክፈል ኦሮሞ መሆን ብቻ በቂ ግብዓት ሊሆን ካልቻለ ይህንን የብሄርተኝነት ቁጭቱን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እስልምናንም ጭምር ማእከል ማድረግ ግድ ይለናል ባዮች ናቸው። ለዚህም ዋነኛው ማረጋገጫ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው እስላም የሚኖረው በኦሮሞያ ውስጥ መሆኑን ነው። ስለሆነም ኦሮሚያን ህልው ማድረግ የሚቻለው በእላማይዜሽን ውስጥ (through Islamization ) ብቻ ነው ብለው ከልባቸው አምነው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ውለው አድረዋል።ለዚህም ከጅማ ባሌ አሩሲና ጅቡቲ ብሎም የመን ድረስ የተዘረጋው መስመር ምን ሲስራ እንደ ከረመና ዛሬ የመን ውስጥ በተፈጠረው ቀውስ የገባበትን አጣብቂኝ እናውቀዋለን። በቅርቡ አትላንታ ላይ በተደረገው የነጃዋር ኮንፈረንስ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስትገለል እና ከእስልምና ጽንፈኝነት ጋር እንዳይያያዝባቸው የፕሮቴስታንት ተወካይ ለይስሙላ እንዲወከል ማድረጋቸው ሌላ ትርጉም የለውም። በጥቅሉ የአጭር ግዜ ስኬትን ብቻ በማስላት የሚፈጠሩ የፖለቲካ መስመሮች በአግባቡ አለመያዛቸው ምን እንደሚያስከትል ደቂቀ ጃዋርያን ከፍልስጤሞች ኪሳራ ቢማሩ እዳው ገብስ ይሆንላቸው ነበር። በኤደን ባህረ ሰላጤ ራዲካላይዝድ ለማድረግ በቀን ሁለት ሽህ ያህል የየመን ሪያል ወይንም (ሁለት መቶ ብር) ጫትና ምግብ ጨምሮ የኪስ ገንዘብ እየተከፈላቸው ለአመታት የሰለጠኑት በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ከባሌ ከጅማና ከ አሩሲ የተወሰዱት እስላም አክራሪ ኦሮሞዎች ለታቀደላቸው አለማ ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት የመን ውስጥ በተነሳው እሳት ተቀርቅረው መቅረታቸውን እናውቃለን ። ነገ የነጃዋራ ሙሃመድ ቅዠታቸው ሰምሮ “Islamic Republic of Oromia” ተግብራዊ ብትሆን በዋናነት ከፍተኛ የዘር ማጽዳት ዘመቻ የሚከሰትባቸው እስላም ያልሆኑት ኦሮሞዎችና ኦሮሞ ያልሆኑት እስላሞች መሆናቸውን ለማወቅ ነገን መድረስ አይጠይቅም።

የሌለ እውነት በመፍጠር ርካሽ ለሆነና የትም ለማይደርስ ቅዠት እንደቀላል የሚለኮስ የፖለቲካ ቁማር ምን ያህል ዋጋ እንደ እንደሚያስከፍል ከፍልስጤም ተሞክሮ መማር አዋቂነት ነው። እንኩዋን ዛሬ ድፍን መካከለኛውን ምስራቅ እንደሰደድ እሳት የሚበላው የሺያት ሱኒ ካርድ ባለበት በዚህ የብላ ተባላ ዘመን ወትሮም ቀይ ባህርን ካባ አባይን መቀነት አድርገን የምንገኝ እንደመሆናችን እንዲህ ባለው ኩነት ከረባት እያሰሩ “ድምጻችን ይሰማ” በሚያዘጋጀው መድረክ ላይ ሁሉ እየተገኙ “ኦሮሚያ ስሩ እስላማይዜሽን” የሚል የላም አለኝ በሰማይ ተረት መተረት የልጆች ጨዋታ አለመሆኑን ማወቅ ካለመቻል የባሰ ድንቁርና የለም።
ደቂቀ ጃዋርያን:- በክፋት ህሊና ለምትራመዱት መንገድ ቀርቶ በተቃጠለ ብሄራዊ ስሜት ፋኖ ተሰማራ ያሉት የያ ትውልድ አካላት እንኩዋን ይህችን አገር በመልካቸው መቅረጽ እንዳልቻሉ የትናንት ታሪካችን ምስክር ነው። ይኽ ዘመን የመረጃ ዘመን ነው። ይኽ ዘመን አለም አንድ ትራስ ተጋርቶ የሚተኛበት ባንድ ጃንጥላ የተጠለለበት ዘመን ነው። ዛሬ ኩታ ገጠም ሆነን በየትኛውም የአለም ዳርቻ የምንኖር ህዝቦች እጣ ፋንታችን አንድ ነው። የነጃዋር አገሪቱን የማስለም እስትራቴጂ ዛሬ ቀርቶ ጨለማውን ዘመን ተገን አድርጎ በመጣው አህመድ ግራኝ ሳይቀር ተሞክሮ ሳይወለድ የጨነገፈ ኪሳራ እንደነበር ልብ ይሉዋል።

(መስቀሉ አየለ)  ከልጅ ግሩም ፌስ ቡከ የተወሰደ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *