– ፖለቲካ ከፊዚክስ የበለጠ አስቸጋሪ ነው፡፡
አልበርት አንስታይን
– ፖለቲኞች የትም ቦታ አንድ ናቸው፡፡ ወንዝ በሌለበትም እንኳን ድልድይ ለመገንባት ቃል ይገባሉ፡፡
ኒክታ ክሩስቼቭ
– እውነት በአብላጫ ድምፅ አይወሰንም፡፡
ዱግ ግዊን
– ኮንሰርቫቲቭ፤ምንም ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ መደረግ እንደሌለበት የሚያምን ሰው ነው፡፡
አልፍሬድ ኢ.ዊጋም
– አንዳንድ ሰዎች ለመርሃቸው ሲሉ ፓርቲያቸውን ይለውጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ ለፓርቲያቸው ሲሉ መርሃቸውን ይለውጣሉ፡፡
ዊንስተን ቸርቺል
– ፖለቲካ ጨዋታ ሳይሆን ከባድ ሥራ ነው፡፡
ዊንስተን ቸርቺል
– ለአሜሪካ ነፃነት ትልቁ አደጋ ህገ መንግስቱን ችላ የሚል መንግስት ነው፡፡
ቶማስ ጀፈርሰን
– ሁሉም ሰዎች ሲፈጠሩ ተመሳሳይ ናቸው – ከሪፐብሊካኖችና ዲሞክራቶች በስተቀር፡፡
ግሮቾ ማርክስ
-የማታ ማታ የምናስታውሰው የጠላቶቻችንን ንግግር ሳይሆን የወዳጆቻችንን ዝምታ ነው፡፡
ማርቲን ሉተርኪንግ
– በፖለቲካ፣ ምላሽ ያልተሰጠው ውሸት፣ በ24 ሰዓት ውስጥ እውነት ይሆናል፡፡
ዊሊ ብራውን
– በፖለቲካ ውስጥ አለመሳተፍ ከሚያስከትላቸው ቅጣቶች አንዱ ካንተ ባነሱ ሰዎች መተዳደርን ነው፡፡
ፕሌቶ
– በዝግታ እራመዳለሁ፤ ነገር ግን ፈፅሞ ወደ ኋላ አልራመድም፡፡
አብርሃም ሊንከን
– ልጆቼ ሂሳብና ፍልስፍና የማጥናት ነፃነት እንዲያገኙ፣ እኔ ፖለቲካና ጦርነት ማጥናት ይኖርብኛል፡፡
ጆን አዳምስ

Related stories   እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።

ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተወሰደ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *