በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ መልኩን እንዳይቀይር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ቢገለጽም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ መገደዳቸውን የሚያረጋግጡ መርጃዎች ይፋ ሆነዋል። የመንግስት ሚዲያዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የተረጂዎች ቁጥር መቀነሱን አመልክተዋል። የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ግን ” አስቸኳይ የውሃና የምግብ አቅርቦት” ሲሉ ይሰማሉ።
በአፋር፣ በደቡብ ፣ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል ከዝናብ እጥረት ጋር በተያያዘ የተከሰተው ድርቅ በአሃዝ ጉዳይና በስያሜው ከተፈጠረው አለመግባባት ውጪ በገሃድ እውቀና የተሰጠው ችግር ነው። ችግሩ በተለይም ህጻናትንና አረጋዊያንን እንዲሁም አርብቶ አደር አካባቢዎችን በእጅጉ እንደጎዳ በተደጋግሚ መርጃዎች አረጋግጠዋል።
ሰሞኑን ለጀርመን ሬዲዮ የአማርኛው ክፍል ቃለ ምልልስ የሰጡ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች እንዳረጋገጡት በኦሮሚያ ጉጂ ዞን ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ይመስላል። የዞኑ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ነጋሽ ኡላላ እንዳሉት 186 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 52 ሺህ ተማሪዎች ለድርቅ ተጋላጭ ሆነዋል። በሁለት ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንዲነሱ በመደረጉ ሁለት ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።
የቦረና ዞን የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጀሌሳ ውቃ በጥቅምት ወር የዘነበው ዝናብ ተስፋ በመስጠቱ ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ 2000 ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገባታቸው እንዲመለሱ ቢደረግም እንደታሰበው አልዘለቀም ይላሉ። አያይዘውም በአሁኑ ሰዓት ከ800 በላይ ተማሪዎች መማር አለመቻላቸውን አመልከተዋል።
“ለተማሪዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታና የውሃ አቅርቦት ግድ ነው” ሲሉም ማሳሰቢያ አዘል መልዕት አስተላልፈዋል። የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሪየት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ችግሩ እንዳለ ይስማማሉ። ቀደም ባሉት ጊዜያት 600 ሚሊዮን ብር ተበጅቶ ተማሪዎችን የመመገብ ስራ መሰራቱን ተናገረዋል። አሁንም ችግሩን የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑንን አመልክተዋል። የተምህርት ሚኒስቴርም ይህንኑ የመለየት ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የድርቅ ተረጂዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ይልቅ ዘንድሮ 44 በመቶ መቀነሱን የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ 1 ሚሊየን የሚሆኑ ተማሪዎችም ከትምህርት ገበታቸው መራቃቸው ተገልጿል። አያይዞም ችግሩን ለመቅረፍ የፌዴራል መንግስት ከክልሎች ጋር በመሆን የህፃናት ምግብ፣ የእንሰሳት መኖ እና የውሃ አቅርቦት እያከናወነ መሆኑን አመልከቷል። አክሎም ፋና ለተጎጂዎች የእርዳታ እህል የማከፋፈል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠቅሶ ገልጿል።
በዳታ ተደግፎ ባይቀርብም በአዲስ አበባና አንዳንድ የአገሪቱ ከተሞች ህጻናት በትምህርት ቤት ውስጥ በረሃብ ምክንያት እንደሚወድቁ፣ በዚህም ሳቢያ መምህራን በራሳቸው ተነሳሽነት ምግብ የመመገብ ስራ መስራት መጀመራቸው በተለያዩ መገናኛዎች መዘገቡ አይዘነጋም። በከተሞች ውስጥ ያለው የስራ አጥነትና ራስን ችሎ ያለመኖር ችግር በርካቶችን የሚፈታተን ችግር እንደሆነም በስፋት የሚደመጥ ጉዳይ ነው።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

አካባቢያቸው በድርቅ የተመታባቸው ነዋሪዎች ልጆቻቸው ትምህርት ቤት ባይገቡም፣ “ቤት” ቀሩ ቢባልም በቤታቸው ውስጥ እንዴት እንደሚኖሩና በማን ሁኔታ እንዳሉ የተባለ ነገር የለም። አርብቶ አደር አካባቢ መሆናቸው ደግሞ ጉዳዩን አስጊ ያደርገዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *