“…ፈረንጆች የካሳሬ ቦርጂያን ፎቶ እግዜር ነው ብለው ሰጥተውን በየመኝታ ቤታችን ሰቅለን እንፀልያለን። ከሄንሪ ብላንክ አፄ ቴዎድሮስን ደም የጠማው ግስላ አድርጎ መጽሐፍ ጽፎልን ወደ አማርኛ ተርጉመን የኢትዮጵያ ታሪክ ብለን እናስተምራለን። አፄ ምኒልክ ጡት ቆርጠዋል የሚል የሐሰት ታሪክ ተፈጥሮ የጡት ሐውልት ተሠርቷል…” ከክርክሩ የተወሰደ

የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶለሳ መጽሐፍ ከታሪኩ ኩነት፣ ከጭብጡ እስከ አጠቃላይ አወቃቀሩ እያነጋገረ ነው። መጽሐፉን በጨዋነት ከመተቸት ይልቅ ማናናቅ የመረጡም አሉ። መጽሃፉንና የመጽሃፉን ባለቤት፣ እንዲሁም አደማጭና ተመልካችን ያሳዘነ ቃለ ምልልስ ተደርጓል። ይህ ቃለ ምልልስ ጠያቂው ብቻውን ያወራበት፣ ተጠያቂ እድል በመነፈጋቸው ብቻ ሳይሆን ክብረ ነክ የሆኑ ጉዳዮችና ዘለፋ ሲሰነዘርባቸው ችለው ቃለ ምልልሱን በጨዋነት ጨርሰው አመስግነው መሰናበታቸው ያስገረማቸው ብዙ ያሉበት ሲሆን ትዕንቱ ያስደሰታቸውም አልታጡም።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ ልዩ ትኩረት ሰጥተውት አስተያየት ያካተቱበትና ለተሰጣቸው ምላሽ ዳግም የበኩላቸውን አስተያየት በመልስ መልክ ያቀረቡበት መጽሐፍ በማህበራዊ ገጾች ላይ ራሱን ችሎ እንደ አጀንዳ ተትክሏል። አቶ ጉዋንጉል ተሻገር “እስኪ እንወያይ” ሲሉ ፕሮፌሰር ጌታቸውን ሸንቆጥ አድርገው የጀመሩትን አስተያየት የተለያዩ የፌስ ቡክ ባልደረቦቻቸው ሃሳብ ሰጥተውበታል። እንዲህ ያለው የማህበራዊ ድር ወግ ይበል የሚያሰኝ ነውና እንዳለ አትመነዋል። አቶ ጉዋንጉል አስተያየቶቹ እንዳሉ እንዲታተሙ ስለፈቀዱ እናመሰግናቸዋለን። በሳቸው የመነሻ ሃሳብ ተጀምሯል፤ ዝግጀት ክፍሉ
————————————————————————–

Guangul Teshager
ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ በፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ መጽሐፍ ላይ የሚሰጡት አስተያየት በጣም ወረደብኝ። ተሳስቼ ይሆን?! እስቲ ጎበዝ አግዙኝ! ጽሑፋቸgwanguleው በጣም ወረደብኝ። እውነት ለመናገር ደነገጥኩኝ። ሌላ ሰው ስማቸውን እንደ ብዕር ስም ተጠቅሞበት ይሆን ወይ ብዬም ጠረጠርኩ። ከዚህ ቀደም አንዱ መፅሀፋቸውን ሲያሳትሙ የፕሮፌሰር መስፍን አስተያየት ካልወጣ አናትምም ተብለው አውጥተው ማሳተማቸውን ሰምቼ ደንግጬ ነበር። መቸም ፈረንካዋ እንዳታመልጣቸው ሳይሆን ዕውቀት ለማስተላለፍ ባላቸው ብርቱ ፍላጎት ነው ብዬ በበጎ (Positively) ተርጉሜ አልፌው ነበር።አሁን ይህ ሲፈጠር ምንድን ነው ይህንን ዓይነት ነገር ፣ ግራ የሚያጋባ ነገር ተደጋጋመ ብዬ እየጠየኩ ነው። መቸም ለኢትዮጵያ ያላቸው ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ፕሮፍ ፍቅሬን በወረዳ ቋንቋ በመዝለፋቸው ፀረ ኢትዮጵያ ካምፕ ውስጥ ነው ዘው ብለው እቅፋቸው ውስጥ የወደቁት። ሂሳቸው አፍራሽ ነው። ገንቢ አይደለም። በጣም ያስደነግጣል። ምሁራዊ (አካዳሚክ) ውይይት ማድረግ አልቻሉም። ተበሳጭተዋል፣ ደንግጠዋል። እንግዲህ የፕሮፌሰር ፍቅሬ መጽሐፍ ላለፋት 50-70 ዓመት ፕሮፌሽናል ሆነ አማተር ሂስቶርያን ከጻፈው ወጣ ያለ ነው። እንደውም ፍፁም ይለያል። እኛ ይሄን ሁሉ ዓመታት ሙሉ ዕድሜያችን የጻፍነውና ያስተማርነው ገደል ሊገባ ነው ብሎ በድንጋጤ ከመወራጨት ፓነል ውይይት ወይም ትልቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈራንስ አዘጋጅቶ ጥልቅ ምሁራዊ ውይይት ማድረግ ሲቻል እንደ 69 -70 ዓ.ም የኢሕአፓው አደፍርስ እና እሳቱ ተሰማ ይባሉ የነበሩ ስም አጥፊዎች ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን፣ ሜትር አርቲስት እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን የመሰሉ ታላላቅ ከባንዲራችን ቀጥሎ የሚከበሩ ሰዎችን ለማዋረድ ይሞነጫጭሩት የነበረው ዓይነት እጅግ የወረደ አንጃ ግራንጃ ርካሽ ስድብ መጻፍ ያስገምታል። ራስን ያዋርዳል። ኧረ ግራ ያጋባል። እስኪ እንወያይበት።
Assefa Chabo
Assefa Chabo I have got the essence,if any,of the book from few of the first review.My friend and I said Dr.Getachew has no need to respond.Unfortunately he did and that was his right. As for me I closed the Subject and Moved on.
Guangul Teshager J AssefaChabo
በጥሞና ምንጭህን አሳውቅና እኛም ለመጻፍ እንጠቀምብት ማለት ያባት ነው። ለየት ያለ ነገር ነው።
Kassim Adam
መቸም ጓንጉል አንተም እንደምታቀው ይህ በጣም አስቸጋሪ ዳርቻ ነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በምእራባውያኑ falklore የማያመልኩ ሰው ቢሆኑ ኖሮ ምክንያት አላቸው ማለት በተቻለ ነበር ።It isn’t always Science that keeps the fabric of society intact . We depend heavily on tradition . እንዳልከውም ሁሉ የወረደ ወቀሳ ነው።
Yussuf Yassin ይቅርታ ወንደም Guangul Teshager J የፕሮፌሰር ጌታቸው “የወረደ አንጃ ግራንጃ ርካሽ ስድብ” ላልከው አንድ ምሳሌ ብትሰጠን መልካም ነበር።
Guangul Teshager J YussufYassin
አንድ ሰው 20 ዓመት ፈጀብኝ ብሎ ያውጣውን ጥናት ተረት ነው ፣ ሚዝ ነው ከማለት የከፋ ስድብ ምን አለ??”
Guangul Teshager J AmbawAdane
ቴዎድሮስ የሚባለው የኢ ቢ ኤስ ሰውዬ አንድ ጆንያ ጥያቄ ሰብስቦ ይዞ ነበር ሰዓቱ ሳያልቅብት አወረደው ጠያቂም መላሽም ሆኖ አለቀ። የፕሮፍ ጌታቸው ኃይሌ አንዱ ቅሌት ይህንን ሰውዬ ማድነቃቸው ነው። ሰው ሲወርድ፣ እንደው አንዴ ቁልቁለቱን ከያዘው፤ መቆሚያ የለውም ለካ….ያሳዝናል!!!
Yussuf Yassin

የጥናቱ ትክክለኛነት ጸሓፊው ጥናቱን ለማጠናቀቅ በፈጀው ጊዜ የሚለካና የሚወሰን ከሆነማ ምኑን መከራከር አስፈለገን። ተረት ወይም ሜትን ከታሪክ የሚለው የጥናት መስክነታቸውና በአጠናን ዘዴዎቻቹው ያለው ልዩነት መስሎኝ ነው። የሁለቱ ፕሮፌሰሮቻችንም ሆነ የእኛ የክርከር ማጠኝጠኛው ይህ መስሎኝ ነው።
Guangul Teshager J YussufYassin
ፈረንጅ የቀባጠረውን መገልበጥ እና ጥናት ይለያያል። ከበሬታ በተሞላበት ሁኔታ ሕፀፅ ማውጣት እና ዘለፋ ይለያያል።
Yussuf Yassin

ፈረንጅ ከቀባጠረውን (የጠነዙ ገለፃዎች?) የአማራና የኦሮሞ ምንጅላቶች የዘር ፍሬ (እውነተኛው የዘር ምንጭ) በወንዙ ውስጥ ዋኝቶ ተገናኘበት የተባለው አኳሃን ነው ይብልጥኑ ታማኒው? ሚትና (ጥረቃ?) ታሪክ ላይይለያይ ወስኗል ማለት ነዋ!። ይሁና!!
Betty Mullugeta Guangul Teshager J
እኔ የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን መፅሀፍ ባላነበውም ከተለያዩ ፅሁፎች እንዳነበብኩት ከሆነ ግን የአማራንና የኦሮሞን ወንድማማችነትና አንድነት የሚዘክር አይነት ፅሁፍ መሠለኝ :: በኔ ግምት የአማራና የኦሮሞ ህዝብ መሠረታቸው አንድ ነው ማለቱ የሚያስኬድ ባይመስለኝም ነገር ግን ከማንም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች እንደ ሁለቱ የተዋለደና የተቀላቀለ ያለ ባይመስለኝም ነገር ግን ታሪክን ሳይሆን ውሸትን መሠረት አድርጎ በሚጮሁ ጥቂት የኦነግ አቀንቃኞች እንደነ ዶክተር መሐመድ ሀሰን በመሳሰሉ ምሁሮች የተመረዘው የኦሮሞ ወጣት ላይ ያለውን ሁኔታ ስንመለከት የኦሮሞ ተወላጆች ልክ ከሌላ ፕላኔት የመጡ ያህል አርቀዋቸው ማየቱ የተለመደ ሆኗልና በርካታው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ በፅኑ የሚያምኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የዶክተር ፍቅሬን ሀሳብ እንከንየለሽ አድርጎ ቢያየው አይደንቀኝም :: እኔ ፕሮፌሰር ጌታቸው የፃፉትና ከላይ ፖስት ያደረኩላችሁ የተባለውን ሀሳብ የሚያፈርስ fact እየጠቀሱ ሀሳቡን ሲቃወሙ አይቻለሁ ነገር ግን እኔም እናንተም እርሳቸው ከጠቃቀሷቸው የፕሮፌሰር ፍቅሬን ዘለፋዎች ያሏቸውን አየን እንጂ ሙሉውን ፅሁፉን እርሳቸው ባለመግለፃቸው በርግጥ ምን እንዳላቸው አናውቅም :: እርሳቸው የፃፉትን መልስ አያችሁ ነገር ግን ሁለቱ የተፃፃፉትን ግን በግልፅ አላየንምና የአንድ ጎንን ብቻ አይተህ ውሳኔ ላይ መድረሱና የርሳቸውን የወረደ ምናምን ማለቱ ምን አይነት ፍርደ ገምድልነትን አየሁብህ:: እኔ ግን የፕሮፌሰር ጌታቸውን ፅሁፍ አንተ በተረዳኸው ሁኔታ አልተረዳሁትም :: ፕሮፌሰር ፍቅሬ የፃፈው ፅሁፍ ላይ አበይት ስህተቶች ያሏቸውን ተችተዋል ; ሲተቹ ደግሞ ብዙ መረጃንም አጣቅሰዋል ስለዚህ ፅሁፉን ወረደ የሚያስብለውንም ሁኔታ ፈፅሞ አልገባኝም:: ያነበብኩት የምሁር ትችትን ነው :: እኔም አንተም ያነበብነው የፖሮፌሰር ጌታቸው ፅሁፍ ላይ በወረደ ቋንቋ ሽማግሌውን የዘለፈው እያለ እርሱን እንደ victim እርሳቸውን ደግሞ የወረደ የሚለውን እጅግ የወረደ ስም መስጠትህ ዘግንኖኛል:: እኔ ያነበብኩትና አንተ ያነበብከው የተለያየ ፅሁፍ እስኪመስለኝ ድረስ ፕሮፌሰር ጌታቸው ላይ የተጠቀምከው ከባድ ቃላት ይገርማል ::
Ambaw Adane Relatively speaking, the majority of the oromo youth (at least those active in the social media) gave the book a warm welcome regardless of the truthfulness of the thesis. On the contrary, the self-claiming ethiopianists like tedros tsegaye of reyoot and most others active in the social media from the same camp took offense in the book. It is time to check their claim of ethiopianism.
Guangul Teshager J Betty Mulugeta
አንድ ሰው 20 ዓመት የጻፈውን መጽሐፍ እውነታነቱን ቢጠራጠሩ መብታቸው ነው። ውሸት ነው፣ተረት ነው ብለው ማመናቸውም ችግር የለውም። እግዜርም የለም ብለው በአደባባይ የሚሟገቱ አሉ። ይህ ሁሉ ችግር የለውም። ለምን ተጠራጠሩት አይደለም ጥያቄው። እርሳቸው ያላዩት፣ የማያውቁት ነገር ሁሉ የለም፣ ውሸት ነው ቢሉ Subjective idealist ናቸው የበርክሌይ ተከታይ ናቸው ተብሎ ይታለፋል። ፈረንጅ የፃፈልንን ታሪክ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አድርገው ከዚህ ውጭ ያለው ተረት ነው፣ ሚዝ ነው ኪንደርጋርተን ለሕጻናት መማርያነትም አያገለግልም፣ በ…….ጊዜ የደነቆረ ወዘተ እያሉ ሰው መዝለፍ ነውር ነው። በጣም የወረደ ነው። እኔ ከእርሳቸው የጠበኩት በኢትዮጵያ ጥናት ላይ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ እንዲቀርብ እና ምሁራዊ ውይይት እንዲደርግበት ያደርጋሉ፣ ፍቅሬን ጠርተው ይወያያሉ የሚል እንጂ እንደዚህ ዓይነት ፀያፍ አተካራ ውስጥ ይገባሉ፣ ለፀረ ኢትዮጵያ ውሾች ጥይት ያቀብላሉ ብዬ አስቤም አላውቅም። አስደንግጠውኛል። excessively defensive ሆነዋል። ኦሮሚያ የምትባል ሐገር እንፈጥራለን የሚሉ ደደቦች አሁን በየቀኑ ጌታቸው ኃይሌን እየጠቀሱ ፍቅሬ ቶሎሳን ያጥላላሉ። ይህንን ያሰቡበት አይመስልም። ፀረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ኢትዮጵያውያንን ተጠቅመው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ልምድ አላቸው። ሻዕብያ ኢህአፓ፣ ኦነግን እና የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴን እስከ ጥግ ተጠቅሟል።
ፕሮፍ ለወደፊቱ ቢጠነቀቁ መልካም ነው። ከዚህ በኋላም ንትርኩ ስድድቡ ቆሞ በዓለም አቀፍ መድረክ የፍቅሬ ቶሎሣ መጽሐፍ ቢቀርብ መልካም ነው። አዲስ ነገር ሲመጣ በቅንነት የቀረበ እስከሆነ ድረስ ክፍት አንጎል ሊኖረን ይገባል።
ደህና ሁኝ!
Kassim Adam
እዚህ ላይ እኔን አስተያየት ሰጥቻለሁ ቤቲየ ። Scholars in academia produce shrouded myth and mystery based on a popular culture . Stars , planets , Galaxy’s and all known objects in the history of known universe posses mythological names . Today newly discovered objects are given a scientific name . However, Leo is still Leo , Venus is still Venus , and Ishtar is still Ishtar regardless of a relationship between an imagined thought and reality .
አፈ ታሪክ እና ልብ ወለድ ድርሰት ይለያያሉ ። ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶለሳ ኢትዮጵያዊ አፈታሪክን በፃፉ ሰአት የዚህ ፅሁፋቸውን አውራ ባህል ምንጭ እንደሚጠየቁ አሳምረው ያውቃሉ ። ለዚህም ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ባልሰጡ ጊዜ ፅሁፋቸው ልብ ወለድ ድርሰት ሆኖ ሊወሰድ ይችላል። ገዳም ውስጥ ተገኝ የተባለውም ብራና አይነተኛ ሚናው እዛ ላይ ነው። እኔ እና አንች እና እንደ ጓንጉል አይነት ሰዎች ካለፈው አራት እና አምስት ትውልድ ትውልድ ምሁራን ጋር ያለን መስረታዊ ችግር ይሄ ነው ። የፈረንጆችን አፈታሪክ እና ሳይንስ በጅምላ እየተቀበልን የራሳችንን ተረት ተረት ላይ እንሳለቃለን ።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ሲተቹ ፣ ትችታቸው እራሱ ይተቻል ። ነገር ግን እኔ እና አንች መተቸት ስንጀምር በዚህ ፅሁፍ ላይ እምነት አላሳደርንም ማለት ነው። ሁሉም አይነት ፅሁፎች scientific or otherwise focus on a targeted audience . እንዳልሽውም የአንድነት ሀይሎችን አስደስቷል ።
Aba Biya Warabadi
Prof Getachew Haile has a great hate for the Oromo people. He has been eve writing false about The Oromo He is suffering from Oromo fobia.
Aba Biya Warabadi
Prf Getachew does not want the fraternity amongst Oromosand Amharas not the Oromos call themselves. He doing great service to the tplf. Who knows he is on the tplf pay roll.
Fekade Shewakena Guangul Teshager
ከጸረ ኢትዮጵያዊነትና ጸረ ኢትዮጵያ ከሆኑ ሀይሎች ጋር ይህ ምን ያገናኘዋል? ችግሩ መጽሀፉ ቅጥ ያጣ ሚቶሎጂ እንደመረጃ ተወስዶ ታሪክ ነው የሚባል ነገር የተጻፈበት መሆኑ ነው። ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ደስ እንዳይላቸው ተብሎ ውሸት ማሽሞንሞን አለብን? ፕሮፈሰር ጌታቸው ናቸው መጽሃፉን ባግባቡ ስለተቹ ስድብ የወረደባቸው። እሳቸውን ጥፋተኛ ለማደረግ መሞከር ስህተት ነው። እንደመጽሀፉ አሳሳችነት ያውም ራርተውለታል። የውሸት ታሪክ መጻፍ እኮ ወንጀል ነው። ስለተጻፈ ብቻ ታሪክ ነው ልንለው አይገባም። ይህን ውሸት በማየት ሰዎች ሊሳሳቱ ይችላሉ። ይህም ሲሆን የወንጀል ያህል ነው። ሰው ከባህር ወጣ ብሎ ነገር የታሪክ መረጃ ቀርቶ ለሕጻን ማጫወቻም አይሆንም
Betty Mullugeta
እውነት ሁሌም ቢሆን ያማል :: ገና ለገና እነኦነጎች እንደ source ይጠቀሙታል ተብሎ እውነትን ማጣመም የዘመናችን መገለጫ ቢሆንም እርሳቸው ያንን አልመረጡም :: እኒህ በኢትዮጵያ ጉዳይ ዘመናቸውን ሁሉ ሲተጉ የነበሩን አዛውንት እንኳን ኦነጎችን ትተህ የኦነግ sympathizers እንኳን በሚሠሯቸው ምርጥ ስራዎች ሁሌም ሲተቿቸውና ሲሠድቧቸው እንሰማለን :: በዊልቼር ዘመናቸውን እንዲገፉ ያደረጋቸውን የደርግ መንግስት እኮ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋምና ሀሣባቸው በነፃነት የሚገልፁ ሰው በመሆናቸው ነበር ቤታቸውን ከበው በጥይት እሩምታ ይህ የደረሰባቸው :: ግን ይህንን ግፈኛ መንግስት የአማራ መንግስት ነበር እያሉ የሚያቅራሩትን እነ ዶክተር መሐመድ ሀሰንን እርሳቸው ህያው ምስክር ሆነው ይህ ከእውነት የራቀ የዘመኑ fabrication መሆኑን ሲያስረዱ የአማራ ትምክህተኛ እያሉ ሌሎቹንም ጨምሮ ሲዘልፏቸው እንሰማለን :: እስቲ እርሳቸው በፃፉት ጽሁፍ ላይ ፀሀፊው የሰጠውን ምላሽ እዩ :: እርሳቸው የፀሀፊውን ሀሳብ በመረጃ ፉርሽ አደረጉት :: መመስገን ባለበት ቦታም ላይ ሳያመሠግኑም አላለፉም :: መቼም እርሳቸው ያውም የተማሪያቸውን ተማሪ ፕሮፌሰር ፍቅሬን ቀንተዉበት ይህንን አሉ አትሉም :: እርሳቸው ዋቢ ያደረጓቸው ታሪኮች ፈረንጅ የፃፏቸው ናቸው የሚለውም ንግግራችሁም ብዙም ሚዛን አይደፋም ::

Ermias Wubshet
Ermias Wubshet እንደሚመስለኝ በቅርቡ ለገበያ የቀረቡት የሳቸው መፅሐፍት ገበያ አላገኙም የፕሮፌሰር ፍቅሬ በአገርቤትም ሆነ በሌላው ዓለም ለጉድ እየተሸጠ ነው፡፡ተሠሚነታቸውን ተጠቅመው ከገበያ ለማሶጣት የመረጡት መንገድ ነው ብል ከዕውነቱ የምርቅ አይመስለኝም፡፡
Guangul Teshager J FekadeShewakena
እኔ የፕሮፌሰር ፍቅሬ መጽሐፍ አንብባዋለሁ። ፍቅሬንም በግንባር አግኝቸው አውርተናል። በመጽሐፉ ዙርያ ተወያይተናል። በኢትዮጵያ ታሪክ ዙርያ ብዙ አስገራሚ ነገሮች አሉ። የልብነ ድንግልን ጦር አምጣ ብሎ መሬት በጅራፍ መግረፍ፣ አፄ ዮሐንስን የሸዋ ሰዎች ባህታዊ መስለው በቤታቸው ጀርባ ጃኖ ለብሰው ወደ ጦርነት እንዲሄዱ እንዴት እንዳበረቷቷቸው፣ ስለ አፄ ቴዎድሮስ፣ ስለ ምኒልክ፣ብዙ ተፅፏል። ፈረንጆች የካሳሬ ቦርጂያን ፎቶ እግዜር ነው ብለው ሰጥተውን በየመኝታ ቤታችን ሰቅለን እንፀልያለን። ከሄንሪ ብላንክ አፄ ቴዎድሮስን ደም የጠማው ግስላ አድርጎ መጽሐፍ ጽፎልን ወደ አማርኛ ተርጉመን የኢትዮጵያ ታሪክ ብለን እናስተምራለን። አፄ ምኒልክ ጡት ቆርጠዋል የሚል የሐሰት ታሪክ ተፈጥሮ የጡት ሐውልት ተሠርቷል። ፕሮፌሰር ፍቅሬ ጋር አዲስ አበባ አግኝቼው ተወያይተናል። መጽሐፋን ሲያስመርቅ በሙዝየም ተገኝቼ ተከታትያለሁ። በጣም ደስ የሚል ተፈጥሮ ያለው የእውነት ሰው ነው። እርሱ ባለው መረጃ ጽፏል። ፈረንጅ ከጻፈልን ታሪክ ይለያል። የራሱ ምንጭ አለው። ጌታቸው ኃይሌ እግዜር ጭቃ አድቦልቡሎ እፍ አለበት ሰው ሆነ ብለው እንደሚያምኑ አልጠራጠርም። እግዜር በ 6 ቀን ስማይና ምድርን አቆመ። ጋላክሲውን፣ ጨለማውን፣ ብርህኑን፣ ፓስፊክን፣ አባይን ኮከቡን ፣ ፕላኔቱን ወዘተ እንደው ሁን ብያለሁ፤ ሁን እፍ፣ እያለ ጠፍጥፎ ሰራው ብለው እንደሚያምኑ አልጠራጠርም።
እንግዲህ የተገኘውን መረጃ ይህንን ደገፎ እንዳለ አቀረበው። በላቦራቶሪ ቀምሜ፣ ቀላቅዬ ፣ቴስታ አድርጌ አረጋገጥኩ አላለም።ሊልም አይችልም።
አሁንም የተሻለ የሚሆነው በኢትዮጵያ የጥናት መድረክ እንዲቀርብ ማድረግ እንጂ አንድ ሰው ሀያ ዓመት ደከምኩበት የሚለውን ነገር ማርካኪስ፣ ግሪን ፊልድ፣ ወይም እስፔንሰር ካልተጠቀስ ተረት ነው ብሎ መዝለፍ ነውር ነው። እኔ ፕሮፍ ጌታቸውን የምጠብቃቸው ፍቅሬን ጠርተው ቁጭ አድርገው ተወያይተው ለመተራረም መሞከር እንጂ እስካሁን ካለው ጋር ይጋጫል ሰለዚህ ተረት ነው አያስኬድም ብሎ በጋዜጣ ለልጆች ተረት መማርያ እንኳን በቂ አይደለም ብሎ የሰው ድካም አጣጥሎ መጻፍ እብሪት ነው። ምሁራዊ አይደለም። ስለ ኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን ብዙ ታዝበናል። እግዜር ይባርካቸውና “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ” በሚለው መጽሐፋቸው ፕሮፌሰር መስፍን ብዙ ነገር አስተምረውናል።
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን ፈልገህ አናግረው። በመጨረሻ ማለት የምፈልገው ግን ይህ መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ተጽፏል። ወደ አማርኛ በእውቁ ምናልባትም ብቸኛ ምርጥ ተርጓሚ አቶ አብርሀም ጎዝጉዜ ተተርጉሞ ሲቀርብ ትርምስ ተፈጠረ። ለምን????!!!!!!
ጊዜ ወስደህ አስተያየትህን ስላካፈልከኝ እግዜር ያክብርልኝ።
ቸር ይግጠመን ጌታዬ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *