ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ግብጻውያኑ ሳይከሰሱ ተለቀቁ ፤ የሳልቫኪር የካይሮ ጉብኝት ኢህአዴግን አላስደሰተም፤ አምባሳደሩ ስጋት የለም አሉ፤

ዛጎል ዜና- ኢህአዴግ ” ጸረ ሰላም” ከሚላቸው ወገኖች ጋር የቀጥታ ግንኙነት እንዳላት ስም ጠቅሶ ግብጽን በኮነነ ማግስት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ሶስት የግብጽ ዜጎች ፈታ። አልሃራም የተሰኘው የግብጽ መገናኛ ይፋ እንዳደረገው እስረኞቹ ባለፈው ረቡዕ አገራቸው ገብተዋል።
ግብጽ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ከቶውንም ጣልቃ እንዳልገባች በተደጋጋሚ ብታስታውቅም ከኢትዮያ በኩል ግን የግብጽን ማስተባበያ የመቀበል አዝማሚያ አልታየም ነበር። አህራም እንዳለው “በሽብር ተግባር” ተጠርጥረው የታሰሩት ሶስቱ ግብጻውያን ምንም ዓይነት ክስ አልተመሰረተባቸውም። የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የካይሮ ጉብኝት ኢህአዴግን አላስደሰተም ቢባልም አምባሳደሩ ስጋት እንደሌለ ጠቁመዋል።
በኢሬቻ በአል ወቅት የተቃውሞ ድምጽ ከሚያሰሙ ወገኖች ጋር ከታዩት ግብጻውያን ጋር በተያያዘ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳይ የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ በይፋ ግብጽን አውግዘው ነበር። መረጃም እንዳለ ተናግረው ነበር። በዚሁ መነሻ ግብጻውያኑ ክስ ይመሰረትባቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም አህራም በዜጎቹ ላይ ምንም ዓይነት ክስ እንዳልተመሰረተ ይፋ ማድረጉ፣ ከመንግስት ወገን ምንም ዓይነት መርጃ አለመሰጠቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል።
የግብጽ የውጭ ጉዳይ አዲስ አበባ ተገኝተው በዜጎቻቸው እስር ጉዳይ መነጋገራቸው በይፋ የትገለጸ ሲሆን፣ ሰሞኑንን ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠ/ሚ ሃይለማርያም የእስረኞቹን ጉዳይ ባያነሱም ከግብጽ ጋር ተደጋጋሚ ንግግር መደረጉን፣ በቅርቡ አዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ከሚሆኑት የግብጹ መሪ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዙን ተናገረዋል።
ግብጻውያኑ የተፈቱት ቀደም ባሉት ድርድሮች አግባብ ይሁን በሌላ ይፋ አህራም በግልጽ ያለው ነገር የለም። ከኢህአዴግ በኩል ግብጽ የአባይ ግድብን ለማስተጓጎል ብረት ያነሱ ተቃዋሚዎችን የመርዳት እቅድና ቅድመ ዝግጅት እንዳላት በተዘዋዋሪ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ለፖለቲካዊ ንግግር በይፋ ግብጽ መግባታቸው ለኢህአዴግ ሌላ ራስ ምታት እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ሳልቫኪር በግብጽ ሙሉ ድጋፍ ይደረግላቸዋል የሚለው ስጋት ከኤርትራ ጋር ካለው የቆየ አለመግባባትና በአገር ውስጥ በተለይም በአማራ ክልል ብዙም መረጋጋት አልታየበትም ከሚባለው ችግር ጋር ተዳምሮ ቀውሱን ሊያሰፋው እንደሚችል ይገምታሉ።

Related stories   አውሮፓ ህብረት እየተሽኮረመመ ታዛቢ ሊልክ ነው

ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑት የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ለመንግስት መገናኛዎች የኢትዮጵያን ጥቅም በሚጎዳ በማንኛውም ጉዳይ አገራቸው እንደማትደራደር ” ችግር የለም” በሚል መልኩ  ይፋ አድርገዋል። እንደ መንግስት ሚዲያ ከሆነ የሳልቫኪር የግብጽ ጉብኝት የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር ነው። ሚዲያዎቹ አምባሳደሩን ጠቀሰው በደፈናው  ይህንን ይበሉ እንጂ የሳልቫኪር የካይሮ ጉብኝት ዋና ዓላማ አልዘረዘሩም። አምባሳደሩ ተጨማሪ የሰላም አስከባሪ ሃይል አገራቸው እንደምትፈልግ ግን ጠቁመዋል። የግብጽ ወታደሮች ለዚሁ ተግባር ወደ ደቡብ ሱዳን ስለመምጣታቸው ግን ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ አልሰጡም።

Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

በሌላ በኩል ደግሞ ግብጽ ይህንን የምታደርገው በአባይ ግድብ ላይ ያላትን የበላይነት ለማስጠበቅ እንደ ማስፈራሪያ ከመሆን አያልፍም ሲሉ የሚከራከሩ አሉ። ከሁሉም በላይ ግን ኢህአዴግ ከበረሃ ጀምሮ ከሰሜን ሱዳን ጋር ያለውን ግኑኝነት አጠናከሮ መቀጠሉ፣ ለአልበሽር ሽፋን መሰጠቱ፣ የተለያዩ የመከላከያና የኢኮኖሚ ስምምነት ማደረጉና እሳቸውን እንደ እንቁላል መንከባከቡ በሰሜን በኩል የሚነሳውን ችግር አስቀድሞ ለመመከት ያመች ዘንድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ አመላክች መሆኑንን እንዚሁ ክፍሎች ይጠቁማሉ።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

የግብጽ የተለያዩ ባልስልጣናት እያዳለጣቸው  ምሁራን ፖለቲከኞች በተደጋጋሚ አባይን በተመለከተ አገራቸው ይፋ ጦርነት ከመክፈት ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ግናባታ የሚስተጓጎልበትን አማራጭ መከተል እንዳለባት ሲመክሩ መቆየታቸው፣ አዲሱ ፕሬዚዳንትም ህዝብ ስጋት እንዳይገባው በተለያዩ አጋጣሚዎች ማረጋገጫ መስጠታቸው አይዘነጋም። አባይ ለግብጽ የህይወት መነሻና መደረሻው ቁለፍ ፣ ያለአባይ ውሃ ህይወት ለግብጽ ሞት በመሆኑ የሚቻለው ሁሉ መደረግ አለበት የሚለው አቋም ይፋ ባይሆንም መንግስትን ጨምሮ የመላው ግብጻውያን አቋም እንደሆነ ጥርጥር የለም። በተቃራኒ ኢህአዴግ በአባይ ጉዳይ የፈጠረው የህዝብ መነሳሳትም ሆነ፣ ራሳቸው ዜጎች ለግድቡ ያላቸው ቁርጠኛነት ከግብጻውያን ጋር ሲነጻጸር በተለያዩ ፖለቲካዊና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ምክንያት እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ በመጠቀስ በኢትዮጵያ በሔራዊ መግባባት አስፈላጊ መሆኑን የተለያዩ ጸሃፍት በስፋት አስተያየት የሰጡበት ጉዳይ ነው።
ይህ ዜና እስከተዘገበበት ደረስ የግብጻውያኑ መታሰርና መፈታት አስመልከቶ ከኢትዮጵያ በኩል የተባለ ነገር የለም።