“Our true nationality is mankind.”H.G.

ገዱ “ሰላም”አሉ፤ የጎንደር መታመም የአገሪቱ መታመም ነው!! እንግሊዝ ፖሊስን ጠቀሳ የጉዞ ማሳሰቢያ ሰጠች

“ጎንደር ሰላም ካልሆነ ሁላችንም ነው የምንታመመው፤ ጎንደርን ሰላም ማደረግ አለብን” ሲሉ የአማራ ክልል የበላይ መሪ ገዱ አንዳርጋቸው የተማጽኖ ድምጽ አሰሙ። አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ስድስት ጊዜ “ሰላም” በማለት የተናገሩት አቶ ገዱ ይህንን ሲናገሩ ድምጻቸውና አካላቸው የተሰብሳቢዎችን ቀልብ ሊስብ በሚችል መልኩ እጅግ መለሳለስ የታየበት ነው።

ዛጎል ዜና- የጎንደር ሰላም ማጣት የአማራ ክልል ህመም እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ደጉ፣” አንድ ትልቅ አካባቢ” ሲሉ የጠቀሱት  ጎንደር ሲታመም አገርም እንደምትታመም አመላክተዋል። አገር ስትታመም ዜጎች በተናጥልም ሆነ በጋራ ሰላም ስለሚያጣ ጎንደርን አብሮ ሰላም ማደረግና ” ወደ ቀድሞ” ሰላም መመለስ የሁሉም ነገር ቅድሚያ እንደሆነ የሚያሰገነዝብ ተማጽኖ አሰምተዋል።

2017-01-17 (4).png

ፎቶ – የጎንደር የንግድ ማህበረሰብ አባላት

ሙሉ የዜናው ክፍል ሳይካተት በቀረበው ቪዲዮ ለመረዳት እንደተቻለው ገዱ ያነጋገሩት የጎንደር ነጋዴዎችን ነበር። በዚሁ አጭር ቪዲዮ አንድ ትልቅ አባት ቆመው የወልቃይት ጉዳይ በትግራይ ክልል እንጂ በአማራ ወይንም በብአዴን አማካይነት መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም መባሉን አንስተው ላቀረቡት ጥያቄ አቶ ገዱ የመለሱት ህገ መንግስቱን ጠቅሰው ነው። ይሁን እንጂ አንድን ህዝብ ማፈን እንደማይቻል አመልከተዋል። አያይዘውም ፍላጎትን በውክልና ማስፈጸም እንደማይቻል ጠቁመዋል። ” ውክልና ” ሲሉ ግን እነማንና የትኞቹን ክፍሎች እንደሆነ አልዘረዘሩም። የወልቃይት ጉዳይ የሚከታተሉት የኮሚቴው አባላት በተደጋጋሚ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው አካሄድ መሰረት መሄዳቸውን፣ ህጋዊ አክሄድ ተከትለው ሳለ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን በተለያዩ የአገርና የውጪ ሚዲያዎች መናገራቸው ይታወሳል። አቶ ገዱም ይህንን ታሳቢ አድርገው መልስ ሰለመስጠታቸው  የታወቀ ነገር ባይኖርም ጉዳዩን እንደሚያውቁት ግን አያጠራጥርም የሚል አስተያየት በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች ከተሰራጩት ውስጥ የሚጠቀሰ ነው።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

በጎንደር ከፋኝ፣ የአማራ ነጻነት ሃይሎች፣ አርበኞች ግንቦት 7 ብረት አንስተው ፍልሚያ መጀመራቸውንና አሁንም ይህንኑ ፍልሚያ አጠናክረው እንደቀጠሉ ነው የሚነገረው። ተቀማጭነታቸው በውጪ አገር የሆኑ የደርጅቶቹና ሌሎች ሚዲያዎች በተደጋጋሚ እንደሚሉት በአንዳንድ ቦታዎች ድል እየቀናቸው መሆኑንን ነው። በመንግስት በኩል  ጦርነት ስለመኖሩ በይፋ ባይገለጽም” የተማረኩ” በሚል ዜናዎችን መመልከት የተለመደ ነው።

ሚዛን ላይ ሆኖ የሚቀርብ የገለልተኛ ወገን ማርጋገጫ ባይኖርም “ታላላቅ” የሚባሉት የአውሮፓ አገሮችና አሜሪካ ዜጎቻቸው ወደ ጎንደርና ባህር ዳር  እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው፣ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ ማራዘማቸው ችገሩ ስለመኖሩ አመላካች እንደሆነ ሁሉም ወገኖች ይስማማሉ። በቅርቡ በባህር ዳርና በጎንደር ለደረሱት ፍንዳታዎች ሃላፊነት የሚወስድ አካል ባይኖርም ክልሉ በደፋረሱን አመላክች ይሆናሉ።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ከሁሉም በላይ ግን ያልተመለሰውና ለሁሉም ግጭት መነሻ የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይና እሱን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ የተከሰተው ቁሳዊና ሰብአዊ ቀውስ ሰፊ የህብረተስብ ክፍሎችን ጓዳ የነካ፣ ልብ የሰበረና፣ በቀላሉ የማይሽር ጠባሳ መቋጠሩን አካባቢውን የሚያውቁ በስፋት የሚሉት ጉዳይ ነው። አቶ ገዱም በዚሁ መነሻ ይመስላል የሰላም ተማጽኖ ያሰሙት።፡

2017-01-17 (4).png

Latest update: Summary – there is tension in the Gondar and Bahir Dar areas of Amhara region after two separate explosions in January 2017, both at hotels that aren’t popular with foreign tourists; police have warned that further attacks may take place during or around the upcoming Timkat Festival (19 January)

ይህ በእንዲህ እያለ የእንግሊዝ መንግስት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል። ጃንዋሪ 17- 2017 11:58 ሰዓት ባሰራጨው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በአማራ ክልል ጎንደረና በህር ዳር በተከታታይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ ተከትሎ ውጥረት መንገሱን አመልክቷል። በዚሁ መነሻ ፖሊስ ከትምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ በበዓሉ ቀን ወይም በበአሉ መቃረቢያ ተመሳሳይ ጥቃት ሊኖር እንደሚችል  ማስጠንቀቁን የጉዞ ማስጥንቀቂያ የማንቂያ መልዕክቱ ይፋ አድርጓል።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

 

 

 

 

 

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0