ቀለማት የሰውነታችን የሀይል ጄኔሬተር ናቸው። ቀለማት በአካላዊ እና ስነአእምሯዊ ጤንነታችን ላይ ከፍተኛ ሚና አላቸው። ይህ እውቀት በዘመኑ የምእራቡ አለም የህክምና ሳይንስ የተረጋገጠ ብቻ ሳይሆን ጥንታውያን ኢትዮጵያውያንም የተረዱት የህክምና እውቀት ነው። ቀለማት ከየትኛውም የህክምና አማራጮች ባልተናነሰ የፈውስ አገልግሎት ይሰጣሉ። ምእራባውያኑ የቀለማት የፈውስ ሀይልን ከብርሃን ጋር የሚያዛምዱት ሲሆን የኛ አያቶች ደግሞ ቀለማቱ ከሚቀመሙባቸው እፅዋት ጋር ያዛምዱታል። ቀለማቱ የፈውስ ሀይል የሚያገኙት ቀለማቱ የተቀመሙባቸውን እፅዋት ሀይል በመውረስ እንደሆነ የዘርፉ ሊቃውንት አስረድተውኛል።
ጥንታውያን አያቶቻችን ለህክምና አገልግሎት ጠልሰሞችን እንደሚጠቀሙ ከዚህ በፊት ተመልክተን ነበር። የጠልሰም የህክምና ጥበብ ከምእራቡ አለም Art Therapy ጋር የሚዛመድ ሲሆን ጠልሰሞቹ የሚሰጡት ፈውስ አንድም ጠልሰሞቹ የሚቀቡት ቀለማት በታማሚው ህቡዕ አእምሮ ላይ በሚፈጥሩት አዎንታዊ ተፅእኖ ነው። በምእራቡ አለምም ቢሆን የ Art therapy አንዱ መገለጫው የቀለማት ስነልቦና colour psychology ነው።
በአገራችን ለተለያዩ አገልግሎቶች ተዘጋጅተው ከሚቀሙቡ ቀለማት አንዱ ጥቁር ቀለም ነው። ለመሆኑ የዚህ የጥቁር ቀለም አዘገጃጀት ወይንም ቀለሙን በተለየ ሀይል የሚሰጡት እፅዋት እነማን ናቸው?
1, የክትክታ ቅጠል
2, የቀንጠፋ ቅጠል
3, የቀርቀሀ ቅጠል
4, የቀርቀሀ ልብስ( ሽልፋፎት)
5, የበግ ቀንድ
6, የበሬ ሸኮና
7, የብራና ፍቅፋቂ
8, የቀረጥ ቅጠል

እነኚህን በአንድ ላይ በማክሰል በማቡካትና በማሸት ተፈላጊውን ጥቁር ቀለም አያቶቻችን ያዘጋጁ ነበር። በተለየ ሁኔታ ለህክምና አገልግሎት የሚውለውን ቀይ ቀለም የሚዘጋጀው እንዴት ነው ?

1,የእንጆሪ ፍሬ
2, ምንጭርሮ እንጨት
3, ሥረ ብዙ
4, የተለያዩ ቀይ አበባዎች
5, ቀይ አፈር
6, የፍሕሦ አበባ እነኚህ በአንድ ላይ ፈጭቶ ነጭ እጣን እና ሙጫ አቅልጦ በሱ እያቀጠኑ በማቡካትና በማለም ተፈላጊውን ቀይ ቀለም ማዘጋጀት ይቻላል።

በነገራችን ላይ khwoja shamsvddin Azeemi የተሰኙ የህክምና ምሁር colour therapy በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ ቀለማት ከስር የተመለከቱትን በሽታዎች መፈውስ እንደሚችሉ ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን ሰጥተዋል :
√ ጭንቀት
√ ድብርት
√ የስኳር በሽታ
√ ስንፈተ ወሲብና ሌሎችም! መፅሐፉን እንዲያነቡ ጋበዝኩ! መፅሐፉን google ላይ ልታወርዱት ትችላላችሁ።

#ራፋቶኤል

#ጠልሰም #Colour_therapy

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *