እናንት ዳኞች የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለይግባኝ ተቀብያለሁ፡፡ ይግባኝ ብዬ ጉዳዬን የሚመለከትልኝየኢትዮጵያ ሕዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈለግሁ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እንደማይሆን አውቃለውናበይግባኝ የአፄ ኃ/ስላሴን ፊት ማየት አልፈቅድም፡፡ በእግዚያብሔር ስም ተሰይማችሁ ከተቀመጣችሁበት የፍርድ ወንበር ላይ ከመቀመጣችሁ በፊት በእኔ ላይየምትሰጡትን የዛሬውን ፍርድ ታውቁት እንደነበር ሳስብና ፍርድ እስከዚህ መርከሱን ስታዘብ ሀዘኔ ይበዛል፡፡

እኔ የተነሳሁት ከትክክለኛ ሕግና ከህሊናችሁ ውጭ ለመፍረድ እንዳትገደዱ ለማድረግ ነበር፡፡ በአጭሩበእኔ ላይ ለመፍረድ የቸኮላችሁትን ያህል አስር እና አስራ አምሰት ዓመት በቀጠሮ የምታጎላሉትን ሕዝብጉዳይ እንደዚህ አፋጥናችሁ ብትመለከቱትና ብትሸኙት ኖሮ የእኔ መነሳት ባላስፈለገም ነበር፡፡

 መንግስቱ ንዋይ

ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት፣ ነፃነትና ርምጃ የተነሳሁ ወዳጅ ነኝ እንጂ ለማፋጀት የተነሳሁ ወንበዴአይደለሁም፡፡ ይህንን ማድረግ ፈልጌ ቢሆን ኖሮ ማንም የማይወዳደረው ሰራዊትና መሣሪያ ሳላጣ ዛሬ እዚህከእናንተ ፊት ለመቆም ባልበቃሁ ነበር፡፡

እኔ ከኃ/ስላሴ ድንክ ውሾች ያነሰ ደመወዝ የሚያገኙ ሁለት የተራቡ ወታደሮችን አጣልቼ ለማደባደብና አገርለማፍረስ አለመምጣቴን የሚያረጋግጥልኝ እናንተ በትዕዛዝ ያገኛችሁትን ፍርድ ለመቀበል እዚህ መቆሜነው፡፡

ከእኔ በፊት በግፍ የፈሰሰው ንፁህ የኢትዮጵያዊያን ደም ብዙ ነው፡፡ በየአፄ /ስላሴ ዘመነ መንግስት ግፍሽልማት በመሆኑ እኔ ለመሞት የመጀመሪያው ሰው አልሆንም፡፡ ሥልጣን አላፊ ነው፡፡ እናንተ ዛሬከጨበጣችሁት የበለጠ ስልጣን ነበረኝ፡፡ ሀብትም አላጣሁም፡፡ ነገር ግን ሕዝብ የሚበደልበትልጣንናድሃ የማይካፈለው ኃብት ስላልፈለግሁ ሁሉንም ንቄ ተነሳሁ፡፡ አሁንም እሞታለሁ፡፡ ሰው ሞትን ይሸሻል፡፡እኔ ግን በደስታ ወደሞት እሄዳለሁ፡፡

ለኢትዮጵያ ኽዝብ ታላቅነት ቀድመውኝ መስዋዕት የሆኑትን አብረውኝ ተነስተው የነበሩትን ጀግኖችወንድሞቼን ለመገናኝት ናፍቄአለሁ፡፡ የጀመርኩት ሥራ ቀላል አይደለም፡፡ አልተሸነፍኩም፡፡ ወገኔ የሆነውድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀመርኩለትን ሥራ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ፈፅሞ ራሱን በራሱ እንደሚጠቅምአልጠራጠርም፡፡

ከሁሉ በበለጠ የሚያስደስተኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልሰራለት ካሰብኳቸው ስራዎች አንዱ የኢትዮጵያ ወታደርዋጋና ክብር ከፍ ማድረግ ሲሆን ይህ ሃሳቤ ህይወቴ ከማለፉ በፊት ሲፈፀም ማየቴ ነው፡፡

ዛሬ መኖራችሁን በማየቴ ነገ መሞታችሁን ረስታችሁ አሜን ብላችሁ ቀናችሁን በማስተላለፍ በመገደዳችሁበእኔ ላይ ሳትፈርዱ በራሳችሁ ላይ የፈረዳችሁ መሆናችሁን አላስተዋላችሁም፡፡

እኔ የተነሳሁት ከትክክለኛ ሕግና ከህሊናችሁ ውጭ ለመፍረድ እንዳትገደዱ ለማድረግ ነበር፡፡ በአጭሩ በእኔላይ ለመፍረድ የቸኮላችሁትን ያህል አስር እና አስራ አምሰት ዓመት በቀጠሮ የምታጎላሉትን ሕዝብ ጉዳይእንደዚህ አፋጥናችሁ ብትመለከቱትና ብትሸኙት ኖሮ የእኔ መነሳት ባላስፈለገም ነበር፡፡

ከእናንተ ከዳኞቹና የሞት ፍርድ እንድትበይኑብኝ ካዘዛችሁ ሰው ይልቅ እኔ ፍርድ ተቀባይ የዛሬ ወንጀለኛ የነገባለታሪክ ነኝ፡፡

የኔ ከጓደኞቸ መካከል ለጊዜው በህይወት መቆየትና ለእናንተ ፍርድ መብቃት የመመዘኑን ፍርድ ለመጭውትውልድ የሚያሳይ ይሆናል፡፡

! ! ! ለእናንተና ለገዢአችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃሳቤ በዝርዝር ገብቶት በአንድነት በሚነሳበት ጊዜየሚወርድባችሁ መዓት አሰቃቂ ይሆናል፡፡ በተለይ የአፄ /ስላሴ የግፍ መንግስት ባላደራዎች ሆነው ድሀውንየኢትዮጵያ ህዝብ ሲገሸልጡት ከነበሩት መኮንን /ወልድና /ወልድ እንግዳወርቅን ከመሳሰሉት በመንፈስየታሰሩ በስጋ የኮሰሱ መዠገሮች መካከል ጥቂቶቹን ገለል ማድረጌን ሳስታውስና የተረፉትም ፍፃሜያቸውንበሚበድሉት በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ ላይ መውደቅ ሲሰማኝ ደስ ይለኛል፡፡

መንግስቱ ንዋይ : መጋቢት 19 1953 . 

አWRITTEN BY 

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *