ዛጎል ዜና፡- “ጠበቃችን እግዚአብሄር ነው፤ ጠበቃችን ገብርኤል ነው” ሲሉ መልስ ሰጡ። ዳኛው ” ግብርኤል ማን ነው? እዚህ አለ?” ሲሉ ጠየቁ። ታሳሪዎቹ አምላካቸው እንደሆነ መለሱ። ዳኞች ወደ ችሎት ሲገቡ ሁሉም እስረኞች ተነሱ። ከመካከላቸው አንድ ሰው የህሊና ጸሎት እንዲደረግ መዕክት አሳለፈ። ሁሉም ለዳኞቹ እንደተነሱ የህሊና ጸልት ማድረግ ቀጠሉ። ዳኛው በችሎት ፊት እንደማይቻል ቢናገሩ፣ ቢገስጹ፣ ቢቆጡ ሰሚ አልንበረም። ጸሎታቸውን ሲጨርሱ ተቀመጡ። ይህ የሆነውበ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ውስጥ ነበር።

ድምጿ እንዲቀየር ጠይቃ በችሎት የታዘበችውን የመሰከረች አንድ የእስረኛ ቤተሰብ እንዳስረዳቸው ችሎቱ ተተራምሶ ነበር። ታሳሪዎች ታሳሪዎቹ ሸዋሮቢት በነበሩበት ጊዜ መሰቃየታቸውን፣ አሁንም አጅበው ያመጡዋቸው ሲገርፏቸው የነበሩ እንደሆኑ፣ የታሰሩትና የሚሰቃዩት ያለአግባብ መሆኑን፣ ለመግለጻቸውም ባሻገር ተራ በተራ ለመናገር ሲጠየቁ ዳኛው ፈቃድ ከልክለው ስለነብር ሁሉም ብሶታቸውን ሲናገሩና ችሎቱ ሲረበሽ ዳኛው ምልክት ሰጥተው ዱላ የያዙ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ችሎት ገብተዋል።

Related stories   እጃቸውን የሰጡ ከፍተኛ መኮንኖች ተገደው ሚኒሻ ሲያደራጁ እንደነበር ለችሎት አስረዱ

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥላችኋል የተባሉና እነ ያሬድ ሁሴን በሚል የክስ መዝገብ አዲስ ክስ የተመሰረተባቸው 121 እስረኞች ናቸው። ተከሳሾቹ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የተመሰረተባቸው ክስ ረሽም በመሆኑ ዛሬ ሲነበብ ነው የዋለው። ዛሬ ዜናው በተጻፈበት እለት  ቀኑን ሙሉ ክስ የመስማት ሂደት ቢከናወነም፣  ክስ በሚሰማበት ወቅት ተከሳሾቹ ባሰሙት አቤቱታ በችሎቱ መረባበሽ የተነሳ ለመጋቢት 4 ቀን 2009 ተቀጥሯል።

Related stories   በሙስና ወንጀል የተገኘን ንብረት ማሳገድ ፤ ማስመለስ፡ ማስወረስ እና ማካካስ በፀረ ሙስና ህጎች

ከዛሬ አምስት ወር በፊት ቅዳሜ ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም  በቂልንጦ ማረሚያ ቤት ድንገት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 23 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ  ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ከቃጠሎው ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ክስ የተመሰረተው በ38 ተጠርጣሪዎች ላይ ነበር። ዛሬ ይፋ እንደተደረገው  ተከሳሾቹ ከቀረበባቸው የክስ ዝርዝር ውስጥ እስረኞችን እሳት ውስጥ ወርውሮ መጨመር እና በፌሮ ብረት ቀጥቀጦ መግደል የሚሉት ክሶች ይገኙበታል።

Related stories   እነ ጃዋር " በዛሬው ቀጠሮ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ዝግጁ አይደለንም" ሲሉ የመማከሪያ ጊዜ ጠየቁ

በጥቅሉ አስራ አንድ መደበኛ የወንጀል ክሶች የተመሰረተባቸው ሲሆን በአመጽና ንብረት ማውደምም የሚሉ ዝርዘር ክሶችም ተካተዋል። ወደመ የተባለው ንብረትም 15 ሚሊዮን ብር የተገመተ ነው። ተከሳሾሹ የሽብር ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ቃላቸውን ለቪኦኤ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ከሰጡት ጠበቃ አቶ ሰዒድ አብደላ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

ምስል ቂሊንጦ እስር ቤት ሲቃጠል፤ ዜናው የተጠናከረው ከቪኦኤ ዘግባ ነው፤

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *