በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የህዝብ አመጽ ተነስተው ነበር ወያኔም አስቸኳይ ግዜ አዋጅ በማወጅ እና ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ተቃውሞውን ለማርገብ ሞክሯል፡፡ የእውነት ተቃውሞው ጠፍቷል? ሁኔታውሰው ወዴት እያመራ ነው? በዚህ ግዜ በኢትዮያ የሆነ ነገር ሲነሳ በኤርትራ የማላከክ ሁኔታንስ እንዴት ይመለከቱታል?ሲል በኢትዮጵያ ተነስቶ ስለነበረው ብጥብጥ እና መንግስት ስለ ወሰደው እርምጃ ጋዜጣኛ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቅን ጠየቃቸው።

ኢሳያስ ‘በመጨረሻ የፈነዳው የህዝብ ዓመጽ ከየት መጣ ብለን ማየት አለብን’ አሉ፡፡ የዚህ መንስኤ ወያኔ  ለ25 ዓመታት በኢትዮጵያ ያደገረው ተግባር መሆኑን አመለክቱ። በጉዳዩ ኤርትራ ገብታበታለች ፣ ግብጽ ገብታበታለች የሚባለውም ማንንም ሊያሳስት አይገባም ጠቆሙ። ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብን በሃይማኖት ፣ በብሄር እና በሌሎች ጉዳዮች በመከፋፈል ስልጣኑን ለማራዘም እየጣረ እንደሆነ የጠናገሩት ፕሬዝደንት ኢሳያስ ፤ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ የነደፈውን ፌደራሊዝም የኢትዮጵያን ህዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት የታለመ እንደሆን አስረዱ። የተባለው ፌደራሊዝም  ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብን መምራት አልችልም ከሚል ስጋት በመነሳት የፈጠረው እንደሆን አመለክቱ። አባባልቸው ኢትዮጳያን በጎሳና በዘር የከፋፈሉዋት ለአገዛዝ እንዲመቻቸው ነው ለማለት ነው።

“የኢትዮጵያን ህገ መንግስት ረቂቅ በቅድሚያ ማያት ከቻሉ ቀዳሚሰዎች ሰዎች ውስጥ አንዱ ነበርኩ” የሚሉት ፕሬዝደንቱ ” አንቀጽ 39ን በህገመንስት መቀመጡን ተመልክቼ እንደዚህ ተደርጎ ሀገር ማነጽ ይቻላል ወይ? ሀገር አይበታትንም ወይ? ብዩ በተደጋጋሚ ብናገርም ሰሚ አላገኘሁም” የሚል  አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ እሳቸው ላቀርቡት ማስጠንቀቂያ አዘል ጥያቄ “የእናንተ ዓለም የራሳችሁ ነው ፤ የእኛ ደግሞ የራሳችን ነው ኢትዮጵያን እንደዚህ አድርገን ነው የምንገዛት” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው አስታውሰዋል።

“የትግራይ ህዝብ በወያኔ ተግባር የተነሳ ያልተገባ ጥላቻ እንዲደርስበት ሆኗል ፤ የትግራይ ህዝብ ባልበደለው እና በወያኔ ተግባር ብቻ በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥላቻን እትርፏል ይህም የ25 ዓመት የአገዘዝ ፍሬ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ኢሳያስ ”ብልጭልጭ” የሚሉት ፌደራሊዝም በሕዝቦች መካከል ግጭት መቀስቀሱን አምልክተው “ኢህአዴግም የተፈጠረው ለዚህ አላማ ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም  ”በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ የት አለ?” ሲሉም ጠይቀዋል።

Related stories   አቶ ሃይለማሪያምና ጃዋር መሐመድ መደራደራቸው ተሰማ

አሁን ያለው የመሰለ የከፋፍለህ አገዘዝ በዘመነ ደርግም ይሁን በሃይለ ስላሴ ዘመን ያልታየ መሆኑንን ፤ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ኤርትራ ወይም ግብጽ ሳይሆኑ ወያኔ ራሱ ነው እንደፈጠረው አቶ ኢሳይስ አመልክተዋል። ”በኢትዮያ ያለው ስርዓት የሌቦች ስርአት ነው ኢኮኖሚውም በጥቂት የወያኔ ድርጅቶች የሚመራ ነው” ሲሉም ፕሬዝደንቱ አዲስ ግኝት ባይሆንም  ለማሳጫ ተጠቅመውበታል። በሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተፈጠሩ ችግሮችም የወያኔ ተግባር ውጤት መሆኑንን  ፕሬዝደንቱ  አክለው ገልጸዋል።

አሰቸኳይ ግዜ አዋጁ መፍትሄ ይሆናል ወይ ለሚለውም ፕሬዝደንት ኢሳያስ ሲናገሩ ”በትእግስ እንጠብቅ ፤ ገና እናየዋለን” ነው ያሉት፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ” አስፕሪን ” ወይም ” የህመም ማስታገሻ እንጂ ከህመም መዳኛ ሊሆን አይችልም” ሲሉ ተደምጠዋል። ዜናው የተወሰደው ከሳተናው ሲሆን  መለስተኛ ኤዲቲንግ ተደርጎበታል።

መንግስት የኢሳያስን አስተዳደር በተደጋጋሚ ከሚወነጅልበት የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ሃይሎች የማገዝና ከለላ የመስጥት ጉዳይ፣ እንዲሁም ኤርትራ ምድር ላይ አሉ ስለሚባሉት ተቃዋሚዎች እንዲሁም አሁን ከግብጽ ጋር በመሆን ኡጋንዳን በመያዝ ደቡብ ሱዳን ላይ የተጀመረውን ኦፕሪሽን አስመልክቶ  ዜናው ያለው ነገር የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *