በ2008ዓ.ም. መገባደጃ ወራት ላይ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የኮሚቴ አባላትን የህወሃት/ኢህአዴግ ኃይሎች በጎንደር ከተማ ለመያዝ ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀስቅሶ የህይወትና የንብረት ዉድመት ማስከተሉ ይታወሳል። በወቅቱ “ንብረታቸው ወድሟል” በሚል ሰፊ ሽፋን አግኝተው የነበሩት የትግራይ ተወላጆች የካሣ ክፍ ሊፈጸምላቸው እንደሆነ  መረጃ ማግኘቱን ጠቅሶ ጎልጉል ዘገበ።

በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ “የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ንብረት እየተለየ ጥቃት ደርሶበታል” በሚል በህወሃት/ኢህአዴግ ጥያቂነትና በራሱ የበላይነት በሚመራው የፌደራሉ አወቃቀር ውሳኔ ሰጪነት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ጎንደር ከተማ ለሚኖሩ ትግራዋያን ነጋዴዎች “የጠፋባቸዉንና የወደመባቸዉን ንብረት” ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማስመዝገብ የካሳ ክፍያና እንደ አስፈላጊነቱ የረዥም ጊዜ የብድር አገልግሎት ሊመቻችላቸዉ እንደሆነ ጎልጉል ታማኝ ያላቸውን የመረጃውን ምንጮች ጠቅሶ አመልከቷል። መረጃውም የተገኘው ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እንደሆነ ተጠቁሟል።

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተወክለዉ የተላኩ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የንብረት ገማች ባለሙያዎች ጎንደር ከተማ ተገኝተዉ “ተዘረፉና ወደሙ” የተባሉ የትግራዋያንን የንግድ ደርጅቶች ወርቅ ቤቶችን፣ ሱቆችን፣ ሆቴሎችንና መኖሪያ ቤቶችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል። ጎልጉል እንዳለው በጎንደር ከተማ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ትግራዋያኖች በተጋነነ መልኩ ያልጠፋቸዉን ንብረቶች (በስቶክ ያልተመዘገቡ) አስመዝግበዋል። በተለይም የሁመራ፣ የተክሌ፣ የመሀሪ ወርቅ ቤት ባለቤቶች በህዛባዊ ተቃዉሞ ጊዜ ወርቅ ቤቶቻቸዉ ተዘግተዉ የነበረ በመሆኑ በርና መስኮታቸዉ ላይ በድንጋይ ድብደባ ጉዳት ከመድረሱ ዉጪ ይህ ነዉ የሚባል ንብረት ባልተዘረፈበት ሁኔታ ከፍተኛ የንብረት እንደወደመባቸውና በሚሊዮኖች ብር የሚያወጣ ወርቅ ተዘርፈናል ሲሉ አስመዝግበዋል። የዜናው ምንጮች እንደሚሉት የአስተዳደር ጽ/ ቤቱ ና የከተማው ህዝብ ሁሉንም በደንብ ስለሜዳው አካሄዱ ሊጤን እንደሚገባ ጠይቀዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

በተመሳሳይ መልኩ የሁመራ ፔንሲዮን፣ ጣና ሆቴል፣ ሮማን ሆቴልና ቋራ ሆቴል ባለቤት የሆኑ ትግራዋያን ወደመብን የሚሉትን ንብረት በሚሊዮኖች ደረጃ አስመዝግበዋል። በአንጻሩ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ አማሮች በህዝባዊ ተቃዉሞዉ ጊዜ የወደመባቸዉ ንብረት በከተማ አስተዳደሩ እንዲመዘገብላቸዉ በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም “ከክልል ትዕዛዝ አላስተላለፈም ” የሚል ምላሽ ሲሰጣቸው  መቆየቱን ጎልጉል ያነጋገራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል።  በተለይም “ከትግራይ ክልል የመጡ ሰርጎ ገቦች “እንደተፈጸመ የሚጠረጠረዉና በርካታ የቪዲዮ ማስረጃ የቀረበበት፣ ፖሊስ፣ አስተዳደሩም ሆነ፣ የፌደራሉ መዋቅር ማስተባበያ ያልሰጠበት የከተማዋ ዋና የገበያ ማዕከል የሆነዉ “ቅዳሜ ገበያ” 446 የባህልና የዘመናዊ አልባሳት መሸጫ ሱቆች፣የጫማና ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችና መደብሮች “በድንገተኛ” የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ የወደመባቸዉ ነጋዴዎች ዛሬም ድረስ አስታዋሽ አላገኙም። ይህ በሆነበት ለትግራዋያን ተወላጆች ብቻ ለይቶ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸዉ የከተማዋን ተወላጆችና ተጎጅዎችን እንዳሳዘናቸዉ ነው ጎልጉል የመረጃ ምንጮቼ  ከጎንደር “ነገሩኝ” ያለው።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ይህንኑ ተከትሎ በጎንደር ከተማም ሆነ በአስተዳደሩ፣ እንዲሁም በሹመኞች ዘንድ ይፋ ባይወጣም ቅሪታ አለ። ጎልጉል በዝርዝር እንዳቀረበው ” ይህ አጋጣሚን ተንተርሶ የሚከናወን የጥቅም ቅርምት ይሚፈጠረው ስሜት አጉል ነው። ዜጎቿን እኩል የማታስተናግድ አገር ውስጥ በጉራማይሌ ሂሳብ መኖር አድሮም ቢሆን የማይሽር ጠባሳ ያመጣል”

በጎንደር የሚኖሩ ባለሃብት የትግራይ ተወላጆች ንብረት ላይ ደረሰ የተባለውን ጉዳት አስመልክቶ መንግስትና አስተዳደሩ በወቅቱ ካሳ እንደሚከፈለ በመገናኝዎች መናገራቸው የታወሳል። ይሁን እንጂ አሁን ጎልጉል የዘገበውን ዜና አስመለክቶ በይፋ የተባለ ነገር የለም። በጎንደር የገበያ ማዕለል ላይ የደረሰውን ውድመት ተከትሎም የማጣራት ሂደቱ ምን እንደደረሰና ንብረታቸውን ያጡ ዜጎች ጉዳይ ብሄር ሳይለይ ምን ውሳኔ እንደተሰጣቸውም የተገልጸ ነገር የለም። የአማራ ክልል ይህንን ከፈተኛ ቅሬታ የፈጠረ ጉዳይ አስመለክቶ አግባብነት ያለውና ሚዛናዊ የሆነ ይወሳኔ ሃሳብ ፈጥኖ ይፋ ሊያደርግ እንደሚገባ የሁሉም ዜጎች እምነት እንደሆነ በተደጋግሚ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ከዚህ ቀደም ሻዕቢያ ከአሰብ የዘረፋቸው ኢትዮጵያዊ ነጋዴዎች ካሳ ሳያገኙ ሲንከራተቱ እንደነበር፣ በተቃራኒው ግን ንብረታቸውን ተወሰደበን ላሉ ኤርትራዊያን ካሳ፣ ብድር፣ አስፈላጊ ጥቅማትቅም እንዲሰጥ አቶ መለስ ማዘዛቸው የሚዘነጋ አይደለም። “ባለ ራዕዩ” መሪ እመራዋለሁ የሚሉትን ሕዝብ ዞር በለ ብለው ለኤርትራ ሲሟገቱና፣ ብዙ አይነት ግብር ሲገብሩ ኖረው ማለፋቸው በዘምናቸው ከሰሩዋቸው ታሪካዊ ጥፋቶች የሚጠቀስላቸው እንደሆነ በወቅቱ መዘገቡ አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *