የየካቲት ወር በሀገራችን ኢትዮጵያ ላቅ ያለ ታሪካዊ ቦታን የያዘ ነው። እራቅ ብለን የካቲት 12 ሺህ 9 መቶ 29 ሲታወስ አካፋና ዶማ፣ ፋስና መጥረቢያ ለሰው ልጅ መጨፍጨፊያ ውለዋል። አዛውንት እናትና አባቶች ሕጻናትን ጨምሮ በመኖሪያቸው በእሳት ጋይተዋል። ዋይታና ጩኸቶች፣ የሰቆቃ ድምጾች እሪታና ጣር እያሰሙ ንጹሐን ዜጎች በየመንገዱ፣ በየጉራንጉሩ፣ በየመንደሩ ተዘርግተዋል። በአዲስ አበባ በትንሹ ወደ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን በግራዚያኒ ተጨፍጭፈዋል። እነሆ የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን በየዓመቱ ሲዘከር፣ ሲታወስ 80 ዓመት ሞላው። እኛም “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” ክብር ለሰማዕታት ወገኖቻችን፣ ኢትዮጵያ በእናንተ ደምና አጥንት ተጠብቃለች እያልን ሰንደቃችንን ዝቅ አድርገን እንዘክራቸዋለን።ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ                                    %e1%8b%a8%e1%8a%ab%e1%89%b2%e1%89%b5-1929-%e1%8a%a5%e1%8a%93-1966

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *