“Our true nationality is mankind.”H.G.

በኦሮሚያ – ኢንቨስተሮች ማዕድን ማውጫዎቻቸውን እየተነጠቁ ነው፤ ለክልሉ ስራ አጦች ይከፋፈላል፤

በኦገሪቱ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀው ኢህአዴግ ተከስቶ የነበረውን ተቃውሞ በዘላቂነት ለመፍታት ደፋ ቀና እያለ እንደሆነ እየወተወተ ነው። ራሱን ጥፋተኛ አድርጎ በማቅረብ ” ጥልቅ ተሃድሶ አደርጋለሁ” በሚል የጀመረው እንቀስቃሴ መዋቅርን መልሶ ከማጠናከር ጎን ለጎን የስራ እድል ለስራ አጥ ወጣቶች በሚል ቢሊዮን ብሮች መመደቡን ይፋ አድርጓል። አስተያየት ሰጪዎች ኢህአዴግ  በስራ ሰበብ አሁን እያደረገ ያለው አዳዲስ አባላትን የመመልመል ስራ እንደሆነ ይተቻሉ። አያይዘውም  ኢህአዴግ የነቃ ትውልድን እንደሚመራ በመረዳት አላስፈላጊ ጊዜና ጉልበት ከሚያባክን ሕዝብ በፈለገው የሚተዳደርበትን ስርዓት በመፍጠር አገሪቱንም፣ እራሱንም፣ ሕዝብንም አሸናፊ ቢያደርግ እንደሚሻል ያሳስባሉ።

ይኸው ድርጅታዊ መዋቅርን መልሶ የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ” እየተፋፋመ” ያለው በኦሮሚያ ነው። በኦሮሚያ 6.6 ቢሊዮን ብር ተመድቦ 1.2 ሚሊዮን ስራ አጥ የተባሉ ዜጎችን ስራ የማስያዝ፣ በዛውም ይህንኑ ቁጥር የኦህዴድ አባል በማድረግ የከዳውን አባል የመተካት ስራ ተጀምሯል። ይፍ ከሆኑት ፕሮጀክቶች አንዱ ሪፖርተር የክልሉን ሃላፊ ዋቢ በማድረግ ይፋ ያደረገው የማእድን ኢንቨስትመንቶችን ከባለሃብት በመውሰድ ስራ ለሌላቸው ለማደል መታቀዱን ነው።

ቀደም ባሉ ዓመታት በፌደራሉ ከተማና ስራ ልማት ሚኒስትር ስር በኦሮሚያ ክልል የድንጋይ ካባ ማምረቻና ማቀናበሪያ ፕሮጀክቶች ለበርካታ የተደራጁ ወጣቶች ከብድርና ከማሽኖች ጋር ተከፋፍሎ ነበር። ፕሮጀክቶቹ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ብዙም ርቀት የሌላቸው፣ አንዳንዶቹም ከተማ ውስጥ ነበሩ። እነዚህ በድንጋይ ማምረት፣ በጠጠር ማዘጋጀት፣ እንዲሁም ተመሳሳይነት ያላቸው የግንባታ ግብዓቶችን እንዲያመርቱ ታስበው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ ውጤታማ አልነበሩም። በመስክ በተደረገ ጉብኝት ማሽኖቹና ፕሮጀከቶች ክስራ ውጪ ሆነው ታይተው እንደነበር ይታወሳል።

ፐሮጀከቶቹ ካለው የኮንስትራክሽን አብዮት ጋር በተያያዘ አትራፊ ሊሆኑ ሲገባ ለምን ከሰሩ? ለምን ውጤታማ አልሆኑም? የሚለው ለአሁኑ ፕሮጀክቶች መልካም ግብአት ሊሆን ይችላልና ከተማ ለማትን መጠየቁ አንድ አግባብ ይሆናል። ሌላውና ትለቁ ጉዳይ ግን ይህ ያለገደብና ያለጥናት የሚዛቀው ሃብት አድሮ ችግር እንዳያመጣ ጥንቃቄ አለመደረጉ ነው። ሰፋፊ የመንገድ ፕሮጀክት የሚሰጣቸው ድርጅቶች በየደረሱበት ተራራ እያረሱ ለመንገድ ስራ ጥሬ እቃ ሲያመርቱ ቁጥጥር አለመደረጉ ፣ ይኸው ሳንቲም የማይወጣበት፣ በነጻ የሚታረሰውና ወደ ገደልነት የሚቀየረው ስፍራ የአካባቢውን ውበት፣ ሃብትና፣ መልክዓ ምድር አበላሽቷል። ይህ በነጻ የሚዛቀው ሃብት ከምንገድ ስራ አልፎ ” ኢንቬስተሮች” ለከተማ ቤት ገንቢዎች የሚቸበችቡትና ከፐሮጀክቱ በላይ ጥሩ የትርፍ ምንጭ ነው። ቻይናዎች ሳይቀሩ አፈር፣ ድንጋይ፣ ኮረትና፣ ሰሌክት ነጋዴ ስለመሆናቸው መንገዶች ባለስልጣን በቂ ግንዛቤ አለው።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

ይህንኑ አስመልክቶ በወቅቱ አስተያየት የሰጡ  ያለ አገባብና ያለ ጥናት የሚናደውን ተራራና ውብ የተፈጥሮ ሃብት መቆጣጠር አግባብ ነው። ስራ አጥ ወጣቶች ባግባቡ እንዲጠቀሙና የተፈጠሮ ሃብቱም በወጉ እንዲጠበቅ ከተፈለገ እነዚህ” የውሉ አካል ነው” በሚል በየአጭር ርቀት ኩሬ የሚሰሩትን ተቋራጮች ከዚህ ተግባራቸው በማስቆም ከውስን አቅራቢዎች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዙ ማድረግ አንዱ መፈትሄ እንደሚሆን ነው። ሪፖርተር ከዚህ የሚከተለውን ዜና አስነብቧል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ለኢንቨስተሮች ሰጥቶ የነበረውን የተለያዩ ማዕድናት ማውጫዎች፣ ከሐሙስ የካቲት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ መንጠቅ ጀመረ፡፡ የክልሉ መንግሥት የሚነጥቃቸውን የማዕድን ማውጫዎች ለተደራጁ ሥራ አጥ ወጣቶች ለመስጠት አዲስ ዕቅድ አውጥቷል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በስፋት ሲነሳ የቆየውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ፣ በርካታ አዳዲስ የሥራ መስኮች በመፍጠር ላይ መሆኑን ይናገራል፡፡

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

ከእነዚህ የሥራ መስኮች ውስጥ ከዚህ ቀደም ለባለሀብቶች የተሰጡ የተፈጥሮ ማዕድናት ማውጫዎችን መልሶ በመውሰድ፣ ለተደራጁ ሥራ አጥ ወጣቶች ማከፋፈልና ወደ ሥራ ማስገባት አንደኛው ነው፡፡

በዚህ መሠረት በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ቀይ አሸዋ፣ አሸዋ፣ ድንጋይ (ካባ) ፑሚስና ታንታለም ማውጫ ሥፍራዎችን የሥራ አጥነት መቅረፊያ ለማድረግ ታስቧል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንትና የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓብይ አህመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሥራ አጥነት ባለባቸው ቦታዎች ሁሉ ይህ አሠራር ተግባራዊ ይሆናል፡፡

‹‹አሁን የጀመርነው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ የሚገኙ የማዕድን ማውጫዎችን በመውሰድ ለ300 ሺሕ ወጣቶች ሥራ ለመፍጠር አቅደናል፤›› በማለት የገለጹት አቶ ዓብይ፣ ‹‹በአካባቢው ሲሠሩ ከነበሩ ኢንቨስተሮች ጋር በጋራ ለማካሄድ እየመከርን ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሠረት ወጣቶቹ ያመረቷቸውን ማዕድናት ኢንቨስተሮቹ ይገዛሉ ተብሎ ታቅዷል፡፡

አቶ ዓብይ ጨምረው እንደገለጹት በክልሉ የመሬትና የሰው ሀብት ካፒታል አለ፡፡ የሚጎድለው ማሽንና ትራንስፖርት ነው፡፡ ይህንን ጉድለት ከባለሀብቶች ጋር በመነጋገር ለመፍታትና ለወጣቶቹም ሥልጠና በመስጠት ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከዚህ በፊት ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ስም የተፈጥሮ ማዕድናትን እሴት ሳይጨምሩ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ ክልሉ በአሁኑ ወቅት ይህን አሠራር በማስቀረት ባለሀብቶች እሴት ወደሚጨምሩባቸው ዘርፎች እንዲሄዱ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ቀይ አፈር፣ አሸዋ፣ ድንጋይ፣ ፑሚስና ታንታለም ለማምረት ብዙ ካፒታል አያስፈልግም፡፡ ካፒታል ቢያስፈልግ እንኳ ምርትን በመሸጥ፣ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችን መግዛትም ሆነ መከራየት እንደሚቻል ክልሉ ያካሄደው ጥናት ያመለክታል፡፡

በዚህ መሠረት የኦሮሚያ ክልል እነዚህን የማዕድን ልማት ዘርፎች በክልሉ የተንሰራፋውን ሥራ አጥነት መቅረፊያ መንገድ አድርጎ ፓኬጅ ቀርጿል፡፡

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

እነዚህ ኩባንያዎች የማዕድን ማውጣት ሥራቸው በመስተጓጎል ላይ እንደሚገኝ እየገለጹ ነው፡፡ የደርባ ሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ ከሐሙስ ጀምሮ ማምረት እንዳቆሙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹250 መኪኖች በአካባቢው ያለሥራ ቆመዋል፤›› ያሉት አቶ ኃይሌ፣ ‹‹በእጃችን የሚገኘው አንድ ሳምንት ማምረት የሚያስችል ፑሚስ ብቻ ነው፡፡ ላለፉት ስድስት ቀናት ማምረት ባለመቻላችን የምርት መስተጓጎል እንዳያጋጥመን ሠግተናል፤›› በማለት አክለዋል፡፡

አቶ ኃይሌ እንደሚያስረዱት፣ ደርባ ሚድሮክ የሥራ ፈጠራው መፍትሔ አካል መሆን ይፈልጋል፡፡ ኦሮሚያ ክልል ይህንን አሠራር ተግባራዊ ማድረጉ የሚደገፍ ሆኖ፣ ነገር ግን ይህ ስትራቴጂ ሌሎች የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ባሉባቸው ክልሎች ተግባራዊ የማይደረግ ከሆነ የገበያ ውድድር መዛባት ይፈጥራል፡፡ ‹‹ስትራቴጂው በፌዴራል ደረጃ ሊተገበር የሚገባው ነው፡፡ ካልሆነ ግን የገበያ ዋጋንና ውድድሩንም ፍትሐዊ አያደርገውም፡፡ ጥራት ያለው ማቴሪያል ከማምረት አንፃርም ሊመዘን ይገባዋል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተለይ በዚህ አካባቢ ለሲሚንቶ ማምረቻ ዋነኛ ጥሬ ዕቃ የሆነውን ፑሚስ የሚያመርቱት ግዙፎቹ ኩባንያዎች ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ፣ ዳንጎቴ ሲሚንቶና ሙገር ሲሚንቶ ይገኙበታል፡፡

ሥራውን ከኢንቨስተሮች ጋር በጋራ የመሥራት ዕቅድ እንዳለና የሽግግር ጊዜው ችግር የማይፈጠርበት እንዲሆን ይደረጋል ሲሉ አቶ ዓብይ አስረድተዋል፡፡ ጥራት ያለው ምርት ከማምረት አንፃርም ወጣቶቹ ከኢንቨስተሮቹ ጋር በጋራ የሚሠሩበትና ሥልጠና የሚያገኙበት ዕድልም ስለሚኖር፣ ችግሩ ይፈታል ሲሉ አቶ ዓብይ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የተንሰራፋውን ሥራ አጥነት ለመቅረፍ በዚህ በጀት ዓመት የ6.6 ቢሊዮን ብር በጀት በመመደብ፣ 1.2 ሚሊዮን ሥራ አጥ ወጣቶችን ሥራ ለማስያዝ ዕቅድ አውጥቷል፡፡

ውድነህ ዘነበ’s blog   ሪፖርተር አማርኛ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0