– የኢንቨስትመንት ጥያቄ ቀነሰ፣ ለ800 ሺህ ወጣቶች ስራ ይፈጠራል በሚል ቃል ተገባ

ዛጎል ዜና፡- ግብር የማይከፍሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራችውን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ። አቶ ገዱ ግብር አይከፍሉም ያሉዋቸውን አካባቢዎች፣ ወረዳዎች ወይም ቀበሌዎች ለይተው ስለመናገራቸው የተባለ ነገር የለም።
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን የተናገሩት የካቲት 13 ቀን 2009 ዓ ም አቶ ደመቀ የጎንደር ነዋሪዎችን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባነጋገሩበት ወቅት ነው። ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን በደፈናው ያቀረበው ፋና እንደዘገበው አቶ ገዱ ” ባለፉት ስድስት ወራት በጎንደር የኢንቨስትመንት ጥያቄ ቀንሷል፤ ስለ ጎንደር የሚነሱ አሉባልታዎችን ወደጎን በመተው የከተማዋን ገፅታ መቀየር ይኖርብናል” ማለታቸውን እና ” አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠበቅባቸውን ግብር እየከፈሉ አለመሆኑን ርዕሰ መስተዳደሩ ተናገረዋል” ብሏል።gedu-2
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በሁዋላ አገሪቱ ወደ ቀድሞ ሰላሟ መመልሱንና፣ ያለፈው እንዳይደገም ህዝብ በሃላፊነት እንዲሰራ አቶ ደመቀ መጠየቃቸውን የፋና ዘገባ ያስረዳል። የተለያዩ መገናኛዎች በአገሪቱ ሰሜን ክፍል ግጭቶች የሚካሄዱባቸው ቦታዎች አሉ። በእነዚህ ቦታዎች ” እምቢ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ” የሚሉ ዜናዎች በተደጋጋሚ ለወራት የተሰራጩና እየተሰራጩ ናቸው። በእነዚሁ ስፍራዎች ግብር መክፍል ያቆሙ ስለመኖራቸውን ተወስቷል። በዜናዎች ላይ መንግስት በገሃድ ማስተባበያም ሆነ ጦርነት ስለመኖሩ በቀጥታ መረጃ አልሰጠም። ነገር ግን “ሻዕቢያ የላካቸው” የተባሉ ተማርከው የሚያሳይ ምስልና ሪፖርት ማስተላለፉ አይዘነጋም።
አቶ ገዱ ግብር የማይከፍሉ የህብረተስብ ክፍሎች መኖራቸውን በግልጽ እንዳስታወቁ ያመለክተው የፋና ዘገባ ” ግብር አየከፍሉም” የተባሉት ዜጎች በምን መነሻና ምክንያት ግብር መክፈል እንዳቆሙ አላብራራም። በጎንደር ራሳቸውን በጎበዝ አለቃ አደራጅተው በረት በማንሳት ዱር ቤቴ ያሉ ወገኖች መኖራቸው በተደጋጋሚ የተገልጸ መሆኑ ይታወቃል። እነዚህ ክፍሎች ራሱን የቻለ አደረጃጀት እንዳላቸው ከመገለጹ ውጪ ምን ያህል ወታደራዊ አቅምና ጡንቻ እንዳላቸው በይፍ አይታወቅም። የትግሉ ባለቤትንት ላይም ከፈተኛ አለመግባባት መደመጥ ከጀመረ ወራት ተቆጥሯል። አቶ ገዱ ” ስለ ጎንደር የሚነሱ አሉባልታዎችን ወደጎን በመተው የከተማዋን ገፅታ መቀየር ይኖርብናል” ማለታቸው ይህንን ለማስተባበል ይሁን ሌላ የፋና ዜና ዝርዝር ማብራሪያ አላተመም።
ጎንደር ሰላም ካልሆነ ሁላችንም ነው የምንታመመው፤….ጎንደር ሲታመም አገርም ትታመማለች፣ ጎንደርን ሰላም ማደረግ አለብን” በማለት ለጎንደር የንግዱ ህብረተሰብ መልዕክት ማስተላለፋቸውን መዘገባችን አየዘነጋም።
ፎቶ
The market town Amba Giorgis, in the North Gondar region, where farmers have been clashing with the military in nearby areas recently [William Davison/አልጃዚራ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *