መንግስት በይፋ እንዳስታወቀ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ወገኖች በርሃብ ተጠቅተዋል። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለክታቸው የዓለም ተቋማት ” ሩጫ ከጊዜ ጋር” ሲሉ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። መንግስት ከማከማቻ መጋዘን ቀለብ ወደ ተጠቁት ስፍራዎች እያጋዘ እንደሆነ ቢናገርም ችግሩ አሳሳቢና ችጋር ወገኖችን ወደ መፈጀት ሊያመራ እንደሚችል እየተናገሩ ነው።

ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ሶማሌና ደቡብ ሱዳንም በከፋ ችጋር ተጠቀተዋል። በሶማሌ ሰዎች የሚበላ በማጣት እየሞቱ ነው። ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ የሚመታት ችጋር የፖሊሲና የትኩርት ችግር እነደሆነ በተደጋጋሚ የሚናገሩ ምሁራን ” በሁሉም ስርዓቶች የሚታረስ ምቹ መሬት ሳይጠፋ ለዘመናዊ እርሻ ትኩርት ለመስጠትና በምግብ ምርት ራስን በመስኖ አምርቶ ለመቻል ቁርጠኛነት የጠፋበት ምክንያት ግልጽ አይደልም” እንደውም በተቃራኒው ክፍተኛ ደረጃ የደረሱ የእርሻ ለማቶችንና ሰፋፊ የህብርት ስራ ማህበራትን ማውደምና ማፍረስ ነው የተሻለ አማራጭ ተደርጎ የተወሰደው።

እንደ እንዚህ ክፍሎች ገለጻ ከሁሉም ነገር ይልቅ አገሪቱ ለእርሻ የሚሆን ለም መሬቷን ለሰፋፊና ሜካናይዝድ ለእርሻ ማዋል ላይ ትኩረት ልትሰጥ ይገባል። የአምላክን ስም እየጠሩና መኞትን እየሰበኩ አገሪቱን ከሚገፉ ” ባለህባቶች” ይልቅ በትክክለኛና አገር ወዳድ ወገኖች ዘርፉ እንዲንቀሳቅሰ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ሊያደርግ እንደሚገባ ይመከራሉ። ሰንደቅ ችጋሩን አስመለክቶ የሚከተለውን ዘግቧል።

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅ በከብቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። በዞኑ የበርካታ አርብቶ አደሮች እንስሳት ድርቁን መቋቋም ተስኗቸው የሞቱ መሆኑን የተመለከትን ሲሆን ከአርብቶ አደሮቹ ጋር ባደረግነው ቆይታም በርካታ ከብቶች የሞቱባቸው መሆኑን ገልፀውልናል። በዞኑ ዋና ከተማ ያቢሎ ምዕራባዊ አቅጣጫ ባለው መንገድ ግራ ቀኝ በርካታ ከብቶች ሞተው ተመልክተናል።

አንዳንዶቹ ከብቶች የቆዩ በመሆናቸው አጥንታቸው ብቻ የቀረ ሲሆን ሊሎቹ ደግሞ ከሞቱ ብዙም ቀናት ያላስቆጠሩ በመሆናቸው ቆዳቸው እንኳን ያልበሰበሰ ነው።

Related stories   የበልግ ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

አካባቢው ከፍተኛ ሙቀት ያለው ሲሆን በአካባቢውያሉ ዛፎች ደርቀዋል። ምንም አይነት የሳር አይነትም አይታይም። አርብቶ አደሮቹ ለከብቶቻቸው ውሃና ግጦሽ ፍለጋ ከብቶቻቸውን በመንዳት በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው ቢጓዙም በሄዱባቸው ቦታዎች በሙሉ ምንም የተሻለ ነገር ያላገኙ መሆኑን ይገልፃሉ። በርካታ አርብቶ አደሮችም ግጦሽና ውሃ ለመፈለግ በሚያደርጉት ጉዞ ከብቶቻቸው በርሃብ ተዳክመው በየመንገዱ ቀርተውባቸዋል። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለም ለእነሱም ሆነ ለከብቶቻቸው ከፍተኛ ሥጋት መሆኑን አርብቶ አደሮቹ ገልፀውልናል። በህይወት ያሉ ከብቶችም በከፍተኛ ሁኔታ ከስተው ከመንቀሳሰቅ ይልቅ መተኛትን መርጠው ይታያሉ።

 በመንግስት በኩል የድርቆሽ ሳር መኖ እየቀረበ ቢሆንም በአንድ መልኩ የድርቁ አካባቢ ሰፊ መሆኑ እንደዚሁም የሚቀርበው የድርቆሽ ሳር አይነትም ከከብቶቻቸው ጋር ባለመስማማቱ ችግር የገጠማቸው መሆኑን አርብቶ አደሮቹ ገልፀውልናል። በሌላ መልኩ አርብቶ አደሮቹ ቀሪ ከብቶቻቸውን ለማዳን እንደዚሁም ለቀለብ ሸመታ የሚሆናቸውን ገንዘብ ለማግኘት ከብቶቻቸውን ቢሸጡም በአካባቢው ገበያ ዋጋ ሊያጡላቸው ባለመቻላቸው ሸጠው መጠቀም ያልቻሉ መሆናቸውን አመልክተዋል። ቀደም ሲል ከአምስት እስከ ስድስት ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው የቀንድ ከብት ዋጋ በአሁኑ ሰዓት ከአንድ ሺህ ብር ብዙም የማይዘል እንደሆነ አርብቶ አደሮቹ ይገልፃሉ።

በድርቁ የተጠቁት አርብቶ አደሮች የከብቶቻቸውን ህይወት ለማቆየት የተወሰኑ ከብቶቻቸውን በመሸጥ የፉርሽካ መኖ ከከተማ ቢገዙም አንዳንድ ነጋዴዎች ፉርሽካውን ከጣውላ ፍቅፋቂ ሰጋቱራ ጋር ቀላቅለው በመሸጣቸው በርካታ ከብቶች የሞቱባቸው መሆኑን ገልፀውልናል።

የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የአርብቶ አደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ማርዮ ለድርቁ መከሰት ዋነኛው ምክንያት ከኤሊኖ የአየር ለውጥ ጋር በተያያዘ የክረምት እንደዚሁም በአካባቢው ሀገየ ተብሎ የሚጠራ የዝናብ ወቅት ያለዝናብ በማለፉ ድርቁ የተከሰተ መሆኑን አመልክተዋል። ይህም በመሆኑ ዞኑ በያዛቸው አሰራ ሦስት ወረዳዎች የድርቁ ችግር በስፋት የታየ መሆኑን ገልፀዋል።

Related stories   የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

የከብቶቹንም እልቂት ከውሃና ከመኖ እጥረት ጋር የተያያዘ መሆኑን ምክትል አስተዳዳሪው ጨምረው ገልፀዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም የውሃ እና የግጦሽ ችግር የተከሰተ መሆኑን ያመለከቱት ሀላፊው፤ ችግሩንም ለመቋቋም በኦሮሚያ አርብቶ አደር ኮሚሽን እንደዚሁም በኦሮሚያ አደጋ መከላከል ፅህፈት ቤት በኩል ችግሩን ለመከላከል ጥረት ሲደረግ የቆየና መሆኑንና አሁንም በመደረግ ላይ መሆኑን ገልፀውልናል። በአካባቢው በነበረን ቆያታም ለአርብቶ አደሮቹ የስንዴ እርዳታ ሲታደል ተመልክተናል።

ፎቶ ፋይል

የድርቅ አደጋ ስጋት በጉጅ ዞን

በኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ ስጋት እየጨመረ ነዉ ተባለ። በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በአንድ ቀበሌ ብቻ እስከ 300 ከብት መሞቱም ተገልጿል። በዞን የሚኖሩ አርብቶ አደሮች አደጋዉ እንስሳት ለይ ብቻ ሳይሆን ሰዉም ላይ እያንዣበበ መሆኑን በመግለፅ አፋጣኝ እርዳታ እንዲደረግላቸዉ ጥሪ አቅርበዋል።

ድርቅ በጉጂ ዞን

 የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ  እርዳታዉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል። ኢትዮጵያ ዉስጥ በድርቅ ከተጠቁ አራት ክልሎች፤ የኦሮሚያ ክልል አንዱ ነዉ። በክልሉ በተለይ በጉጂ ዞን በድርቅ ምክንያት የመጣዉ አደጋ በአካባቢዉ አርብቶ አደሮች ዘንድ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል ተብሏል። አርብቶ አደሮቹ እንደሚገልጹት በድርቁ ሳቢያ ዉኃና የግጦሽ ሳር በመጥፋቱ እንስሶቻቸዉ እየሞቱ ነዉ።
በጉጂ ዞን የሻኪሶ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ  የፈለጉ  ግለሰብ  ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ ባለመዝነቡ ዉኃና የግጦሽ ሳር ተመናምኗል። በመሆኑም ከሻኪሶ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኙ የአርብቶ አደሩ መንደሮች ከብቶች መሞት ጀምረዋል።

Related stories   በምናለሽ ተራ ገበያ – ከሰኞ እስከ እሁድ

የዝናቡ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ በሰዉም ይሁን በእንስሳት ሕይወት ላይ ከፍተኛ ስጋት ተደቅኗል ሲሉም አብራርተዋል። አፋጣኝ ርብርብ ካልተደረገም በስፍራዉ ሰብአዊ ቀዉስ ሊከሰት ይችላል ሲሉም ግለሰቡ  ስጋታቸዉን ተናግረዋል።
በጉጂ ዞን የዶዶላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርብቶ አደር ረጋሳ ዱለቻ በበኩላቸዉ እሳቸዉ በሚኖሩበት ቀበሌ በክረምት በቂ ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳ ለእንስሳትም ይሁን ለሰዉ በቂ ዉኃ የለም ብለዋል። በዚህ የተነሳ የቀየዉ ሰዉ ዉኃ ፍለጋ ሙሉ ቀን እንደሚጓዝም ገልጸዋል። ያም ሆኖ ግን የእንስሳቱን ሕይወት መታደግ እንዳልተቻለ አርብቶ አደሩ ተናግረዋል።

አስራ ሁለት ከብቶቻቸዉ በድርቁ ሳቢያ እንደሞቱባቸዉ የሚናገሩት አርብቶ አደር ረጋሳ ዱለቻ በአካባቢያቸዉ በግምት ከ300 መቶ በላይ ከብቶች መሞታቸዉንም ይናገራሉ።  በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንደ ግጦሽ መሬቱ ሁሉ ለሰዉ ምግብነት የሚዉሉ ሌሎች ሰብሎችም ለጉዳት ተዳርገዋል። በመሆኑም  እንስሳቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ላይም  አደጋ እያንዣበበ እንደሆነ ገልጸዋል።

Pastoralisten Somalia (DW/J.Jeffrey)

እንደ አርብቶ አደሩ ገለጻ አሁን ባለዉ ሁኔታ በምግብ እጥረት የሞተ ሰዉ ባይኖርም፤ በቂ ምግብ ባለማግኘት ምክንያት የታመሙ እና የደከሙ ሰዎች መኖራቸዉን ግን አልሸሸጉም። በመሆኑም በሰዉም ይሁን በእንስሳት ላይ ድርቁ የከፋ ጉዳት ሳይመጣ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኑነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘዊዴ በበኩላቸዉ በሀገሪቱ ድርቅ በተከሰተባቸዉ አካባቢዎች ለሰዉም ይሁን ለእንስሳት እርዳታ የማቅረብ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ባልተዳረሰባቸዉ አካባቢዎችም ከስፍራዉ በሚመጣ መረጃ መሠረት ሥራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

Dw radio ፀሐይ  ሽዋዬ ለገሰ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *