ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኢህአዴግ – አስመራ ላይ ምን አሰበ? ” ጥልቅ ጥናት እየተደረገ ነው፤ ተግባራዊ የሚያደርገው ሕዝብ ስለሆነ ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል” ሃይለማሪያም ደሳለኝ

– አሰብን የማስመለስ ዘመቻ እንደሚጀመር አቶ ሃይለማሪያም በረከት ስምዖንን ተክተው የምርጫ መኮንን ሆነው ባገለገሉበት ዘመን ኢህአዴግ ቢሮ አካባቢ ይሰማ ነበር ፣ በዚሁ ጊዜ አቶ ሃይለማርያም  ” ተሟግቼ አሰበን አስመልሳለሁ የሚል ካለና ከቻለ እንረዳዋለን” ማለታቸው ይታወሳል

Image result for ethio eritrea war

የዛጎል ዜና – የህወሃትና የሻዕቢያ ፍቅር ካከተመ በሁዋላ በጥቅም ግጭት ለተከሰተው ‘ወረራ’ ምላሽ የተሰጠበት መንገድና የተከፈለው ዋጋ፣ የጠፋው የሰው ህይወት በኢትዮጵያ ታሪክ በአስከፊነቱ ሲዘከር የሚኖር ነው። ይህ ጦርነት በአጭር ጊዜ የበላው ህይወት ብቻ ሳይሆን ያንን ያህል መስዋዕትነት የተከፈለበት ድል እንዲመክን የተደረገበት አግባብም ታሪክና ትውልድ የሚረሱት አይሆንም። ምን አልባትም የሟቹ መለስ ውርስ/ ሌጋሲ እዚህ ላይ ታትሞ የሚቀር ይሆናል።
ጦርነቱ ከምካሄዱ በፊት ሕዝብ ከደጀን የፈጠረው ትብብር፣ ” አትፈለጉም የተባሉ የወታደራዊ ባለሙያዎችና በተለያዩ ደረጃ ያሉ ወታደሮች ለዚህ አገራዊ ጥሪ የሰጡት መልስ ደግሞ በየትኛውም ዘመን የሚያበራ ታሪክ እንደሆነ የሁሉም ” ኢትዮጵያዊ” ስምምነት ነው። ኢህአዴግ ያንን አጋጣሚ ተጠቅሞ አገሪቱን ወደ አንድነት ማምጣት አለመቻሉ ደግሞ እንደ ድርጅት ክስረቱ እንደነበር በወቅቱ በተደጋጋሚ አስትያየት የተሰተበት ጉዳይ ነው።

Related stories   አውሮፓ ህብረት - ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ

Image result for ethio eritrea war
ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በሁዋላ ይኸው አሁን ድረስ የድንበር ጉዳዩ እልባት አጥቶ ቆይቷል። ጦር ሰራዊቱም ጉድጓድ ውስጥ ከከተመ የለጅ እድሜ ሆኗል። ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት ይህ ጉዳይ እልባት የማያገኝበት ምክንያት ምን ይሆን? በሚል በአድባባይም ሆነ በግልጽ ሲጠይቅም ኖሯል። ከዚህም በላይ በግንባር ያለው ሰራዊት የመሰላቸትና በአገሪቱ በተፈጠረው የብሄር እሳቤ እንዳይሸረሸር ስጋት ያላቸውም የበኩላቸውን አስተያየት ከመሰንዘር አልቦዘኑም። በሌላ በኩል ደግሞ ከሰራዊቱ ባላት ውስጥ ከዱ፣ አመለጡ፣ የገቡበት ጠፋ የሚሉ ዜናዎችን መስማትም የተለመደ እየሆነ መጥቷል። አንዳንዴም አገርንና አመለካከትን መለየት እስከሚያቅት ድረስ ብዙ የሚሰሙ ጉዳዮች አሉ። መጠኑ ባይታወቅም ዜናዎቹ ግን እውነትነት እንዳላቸው አመላካች ጉዳዮችም እንዳሉ መካድ አይቻልም።
ሁኔታው በዚህ ሁኔታ ባለበት ወቅት ወደ ሁመራ ሄደው ኩታ የተሸለሙት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከህዝብ ቀረበላቸው ለተባለ ጥያቄ የመለሱት መልስ ውሎ አድሮ አነጋግሪ እንደሚሆን ተገምቷል። የኤርትራ ጉዳይ እስከምቼ በዚህ መልኩ እንደሚቀጥል የተጠየቁት አቶ ሃይለማሪያም ” ጥልቅ ጥናት እያካሄድን ነው” ሲሉ በቪኦኤ ተደምጠዋል። ጥናቱ ምን ይዘት እንዳለው ባያብራሩም ” ተግባራዊ የሚያደርገው ሕዝብ ስለሆነ ሲተናቀቅ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል” የሚል መልስ ሰጥተዋል። አቶ ሃይለማሪያም ቀደም ሲል ኢህአዴግ ኤርትራ ላይ ሲከተል የነበረው ባለ አምስት ነጥብ መርህ እንደሚቀየርም ፍንጭ ሰጥተዋል።
“ሕዝብ ተግባራዊ የሚያገርገው ውሳኔ” ምንድን ነው? የህዝብን ንቀናቄ፣ ምላሽ፣ ትብብር የሚጥይቅና ኤርትራ ላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ከዳር እሰከዳር ሊያነሳሳ የሚችል ” ጥልቅ ጥናት” ምን ሊሆን ይችላል? የሚሉት አንኳር ጉዳዮች ከዜናው መሰማት ጀምሮ የሚነሱ ነጥቦች ሆነዋል።
እንደ አቶ ሃይለማሪያም ገለጻ ” በጥልቅ ” እየተጠና እንደሆነና በቅርብ ለህዝብ ይቀርባል የተባለው የጥናት ውሳኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጦርነት? ባድሜን እንካቹህ ብሎ መገላገል? ውይስ የኢትዮጵያዊያን ንብረት የሆነውንና አቶ መለስ እመራታለሁ የሚሉዋትን አገር ክደው ያስረከቡትን አስብን ማስመለስ? ወይስ አቶ ኢሳያስ በሚፈልጉት መጠን እየገበሩ ለመኖር መስማምት?
ነገሮች ኤርትራ ውስጥ እንደቀድሞው አለመሆናቸውን የወቅቱን ኩነታዎች የሚከታተሉ ይናገራሉ። ዛሬ ኢትዮጵያ በግፍ የተነጠቀችውን አሰብ የባህር በሯን ለማስመለስ ፍጥጫው ከሃያላን ጋር ሊሆን ነው። አሰብ በኮንትራት በመሸጡ ምክንያት ኤርትራን እንደቀድሞው ” ተመጣጣኝ” በሚል ቀረርቶ እየነረቱ መመለስ ከባድ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜው ቢረፍድም ምስራቅ አፍሪካ ላይ እየሆነ ካለው አንጻር ግፍቶ በመሄድ አሰብን ለባለቤቱ ህዝብ የማስመለስ ስራ መጀመር አለበት የሚሉም ይሰማሉ። እንዚህ ክፍሎች አቶ መለስ አገሪቱን ባህር አልባ በማደረጋቸው በአገር ደረጃ የፈጸሙት ክፉ ሌጋሲያቸው በግልጽ በባልደረቦቻቸው ይቅርታ ሊጠየቅበት ይገባል በለው የሚያምኑ መሆናቸውን በተለያዩ ድረ ገጾች የሚወተውቱ ናቸው።
ለሁሉም ግን አገር ቤት ያለው የፖለቲካ ረመጥ ፍትህ ባለብት እርቅና ቀናነት በተሞላበት ድርድር መስመር እንዲይዝ ማድረጉ ከዳግም ሃፍርት እነድሚሰውር በአብዛኞች ዘንድ የሚታመን ነው።

Related stories   በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ- ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙ ታወቀ፣

ምስል 2 የኤርትራ ወታደሮች በምሽግ በር ላይ

ምስል 1 የኢትዮጵያ ወታደሮች ለመለስ ቃል ሲገቡ