ዝክረ አድዋ
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለአደዋ ጦርነት ለኢትዮጵያ የሕዝብ ያስተላለፉት የክተት ሰራዊት ጥሪ፦
“እግዚአብሄር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፤ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት
ገዛሁ፡፡ ከእንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለእኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ
አያውቅም፤ ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት
እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል፡፡ እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን
ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡
የአገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም፡፡ አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት
ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘንህ እርዳኝ፡፡ ወስልተህ
የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፡፡ አልተወህም ፡፡ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም ፡፡ ዘመቻዬ በትቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ››( አጤ ምኒልክ ጳወሎስ ኞኞ)

‹‹ግፍ የማይወደውን አምላክ ጨምሬ በመጣችሁበት መንገድ እቀበላችኋለውሁ ፡፡ ባገሬ በኢትዬጵያ ምድር የሮማን ባንዲራ አላስተክልም ›› አፄ ምኒልክ

Related stories   በኢትዮጵያ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያላቸው ማዕከላት ሊገነቡ ነው

‹‹እኔ ሴት ነኝ፤ ጦርነትም አልወድም ፡፡ ግን እንዲህ አይነቱን ውል ከምቀበል ጦርነት እመርጣለሁ፡፡ እኛ ለራሳችን እንበቃለን የእናንተን የበላይ ጠባቂነት አንፈልግም ፡፡ እናንተን አንፈራችሁም›› እቴጌ ጣይቱ የውጫሌ ውል አንቀጽ17 እንደማይቀበሉት ከተናገሩት

የእቴጌ ጣይቱ ትዕዛዝ
‹‹እናንተ ከጉድባ ገብተን ካልተዋጋን እያላችሁ ስትመኙ ነበር ፡፡ነገር ግን ለብዙ ሰራዊት ጥቂት ስፍራ አይበቃውምና ከኢጣሊያው ነፍጥ ይልቅ እናንተ እርስ በርሳችሁ ትተላለቃላችሁ ከውሀው ተኝታችሁ ፡፡ ውሃ እንዳይቀዳ ጠብቁ ››

Related stories   የቀድሞው የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ኮ/ል ኢብራሂም ሸምሰዲን?

Ethio daily post

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *