“Our true nationality is mankind.”H.G.

ዶክተር መረራ እስከ ሞት የሚያደርስ ፍርድ ስለሚጠብቃቸው ዋስትናቸው ውድቅ ሆነ ተባለ

ዛጎል ዜና – የዶክተር መረራ ጉዲና ክስ እስከ ሞት የሚያደርስ ቅጣት የሚያስፈርድ በመሆኑ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ተገለጸ። በዛሬው እለት ባስቻለው ችሎት የዶክተር መረራ ክስ ውድቅ የተደረገው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው።
የመንግስት መገናኛዎች ጠቅላይ አቃቤ ህግን ጠቅሰው እንዳሉት ዶክተር መረራ የተጠረጠሩበት ወንጀል ” ህገመንግስታዊ ስራዓቱን በሃይል የመናድ ሙከራ በመሆኑ፣ በዋስትና ቢወጡ መረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ፣ የሚል እና ከሀገር ይወጣሉ” በማለት ነበር የዋስትና መብታቸው ውድቅ እንዲሆን የጠየቀው።
ሓሙስ እለት የተሰማው ክርክር ለዛሬ አርብ ለብይን ተቀጥሮ ነበር። ዶክተር መረራ የተመሰረተባቸውን ክስ እንደማይቀበሉትና ምንም ዓይነት ወንጀል እንዳልፈጸሙ በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀው አቃቤ ህግ ተቃውሞ በማቅረቡ ነበር ለብይን ተቀጠረ የተባለው።
በዚሁ መሰረት ዛሬ ባስቻለው ችሎት ዶክተር መረራ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ይፋ ሆኗል። ዶክተር መረራ ያለ ተጨባጭ ማስረጃ መታሰራቸውን አበክረው ለፍርድ ቤት ያስረዱ ሲሆን ይህ ዜና እስከታተመበት ድረስ ለተከሰሱበት ክስ መረጃ ስለመቅረቡ የተዘገበ ነገር የለም።
ዶክተር መረራ በኦሮሚያ ሕዝባዊ አመጽ ሲቀጣጠልና አመጹን ተከትሎ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ አገር ቤት ሆነው ድርጊቱን ሲቃወሙ፣ ፖለቲካዊ መፍተሄ ሊፈለግ እንደሚገባ ደጋግመው በግልና በድርጅታቸው ሲወተውቱ እንደነብር፣ ከአገር ውጪም ወጥተው በተመሳሳይ ባገኙት መድረክ ሁሉ የተለመደውን አስተያየት ሲሰጡና ስጋታቸውን ሲገልጹ ነበር። በወቅቱም የተባሉት ነገር አለነበረም።
ብራስልስ በአውሮፓ ህብረት ስብሰባ ላይ ምስክር እንዲሆኑ ተጠርተው ሲመለሱ ከታሰሩ በሁዋላ የተመሰረተባቸው ክስ በኦሮሚያ ክልል ለተነሳውና ራሱ ኢህአዴግ ትክክለኛ ሲል ያመነው አመጽን ተከትሎ ለደረሰው ጉዳት ተጠያቂ አድርጓቸዋል።

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

ዶ/ር መረራ ቀጥለውም ‘…..ለሁላችንም የምትሆንና በእኩልነት የምታስተናግደን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠርና ነፃ የፍትህ ሥርዓት በሀገራችን እንዲሰፍን ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በመታገሌ መከሰሴ አንሶ የአገሪቱ ፓርላማ አባል የነበርኩ ሰው ለተራ ወንጀለኛ የሚፈቀድ የዋስ መብት በመከልከሌ የተሰማኝ ጥልቅ ሀዘን ለራሴ ብቻ ሳይሆን እኛም ሆን ልጆቻችን በሰላም ይኖሩበታል ለምንለው መከረኛ ሀገራችንና አላልፍለት ብሎ ስታመስ ለሚኖር መከረኛ ሕዝባችን ጭምር መሆኑን እንዲታወቅልኝ ነው፡፡” ማለታቸውን ኢትዮ ዲይሊይ ፖስት ገልጿል።
አሁን እየተደረገ ያለው ክስና የክሱ አካሄድ በአገሪቱ ያለውን ፖለቲካ ይባስ ወደ ቂምና ውስብስብ ችግር ከመክተት እንደማያልፍ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

0Shares
0