ተረረም – ፐረረም

ጠያቂና መላሽ – የእብዶች ጨዋታ

– ፐረረም ተረረም
ተረረም ፐረረም
-ፐረረም ተረረም
ተረረም – ተረረም – ደስ አይልም ?
አይልም !
-ያስጠላል ?
አያስጠላም !
-ታዲያ ምንድ ነው ?
ተረረም ፐረረም
– ፐረረም ተረረም ዝምታ ወርቅ ነው ?
አይደለም
– ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ?
አይቀርም
– ታድያንድነው ?
ምንም ።
-ምንም የሚባል ነገር የለም ?
አለ
– ታድያ ምንድነው ?
ምንም ።
– ፐረረም ተረረም አዋቂ ነኝ ብለህ ታስባለህ ?
አላስብም ።
– አላዋቂ ነኝ ብለህስ
አላቅም
– ማወቅ ይጠቅማል ?
አይጠቅምም ።
– አለማወቅስ ?
አይጠቅምም
-ታዲያ እውቀት ምንድነው?
ምንም
– ማነው ያለው ?
ማንም !
– ማንም ሊለው ይችላል ?
አይችልም !
– ለምን ?
አዋቂም ሆነ አላዋቂ የለም
– ማነው ደሞ ይሄን ያለው ?
ማንም !
-ፐረረም ተረረም ገኒን ትወዳታለህ ?
እንክት !
– እሷስ ?
ጥልት
– ለምን ይመስልሀል ?
ባቀውማ ወይ አልወዳትም ወይ አትጠላኝም
– ድንቅ ነው !
ጥሩ ብለሀል !
– ፐረረም ተረረም ለመሆኑ እዝጌር አለ ?
ላይኖርም ይችላል !
– እንግዲያውስ የለም
ሊኖርም ይችላል !
– ታዲያ ምን ይሻላል ?
ምንም !
– ካለእግዜር ግን መኖር እንችላለን?
ይመስለኛል
– እንዴት ?
ሞት ከሌለ
– ሞትማ ዘላለማዊ ነው
አይደለም !
– እንዴት ?
ከሞትኩ አላምነውማ
– ምኑን ?
ዘላለማዊነቱን
– ከሞትክማ ምኑን አመንከው ?
እሱን አደል እምልህ !
-ፐረረም- ተረረም
ተረረም – ፐረረም
አፍቅረህ ታውቃለህ ?
ብዙ ጊዜ ።
– ተፈቅረህ ታውቃለህ ?
ትዝ አይለኝም
– ታድያ ለምን ታፈቅራለህ ?
እማፈቅረውን እስካገኝ
– እምታፈቅረውን ካገኘህስ ?
እሞታለሁ !
– እንግዲያውስ ሞትን ነዋ እምታፈቅረው ?
አይደለም
– ታድያ ማንን ነው ?
ሕይወትን !
– ሕይወትን እንዴት ታገኛታለህ ታዲያ ?
በመኖር
– ፐረረም ተረረም – ለምን ትኖራለህ ?
– ፐረረም ተረረም – ለምን ትኖራለህ ?
ለመኖር !
– ኑሮን ታቃታለህ ?
አላውቃትም
– እሷስ ታውቅሀለች ?
አታውቀኝም !
– ታድያ የኑሮ አላማህስ ?
ለትውውቅ ነው ።
– -ፐረረም – ተረረም
ተረረም – ፐረረም
– ሕይወት ውስጥ ምን ምን አለ ?
የሌለ ነገር ሁሉ አለ
– የሌለ ነገር ደሞ ምንድነው ?
የሌለ ነገር ነዋ !
– ለምሳሌ ምን ?
ለምሳሌ ራሱ
– ትቀልዳለህ መሰል ?
እሱም አለ !
ፐረረም -ተረረም
ተረረም – ፐረረም
ገኒ አሁን ምን እየሰራች ይመስልሀል ?
ፀጉር ቤት ሳትሆን አይቀርም
– ለምን አልክ ?
ፀጉሯ ደስ ይለኛል
– ሌላስ ?
አይኗ
– ሌላስ ?
መላ አከላቷ
– ፀባይና ጥፍጥናዋስ ?
የት አውቄያቸው ። እነዚህንም በሩቅ አይቻቸው ነው . ።
-የምትገርም ነህ !
ይባልልኛል ።
ፐረረም – ተረረም
ተረረም -ፐረረም
– ስለ ሰው ምን ታውቃለህ ?
አሻንጉሊት መሆኑን አውቃለሁ ።
-የማን አሻንጉሊት ?
የአንድ ያልታወቀ ሀይል
-ያልታወቀ ስትል ምን ማለትህ ነው ?
ባውቀውማ እነግርህ ነበር ።
– ታዲያ ለምን አልክ ?
ስለማላቀው
– የማታቀውን ታድያ ለምን ትናገራለህ ?
ተናገር ተናገር ካለኝስ ።
-ፐረረም – ተረረም
ተረረም – ፐረረም
-ሀብታም ነህ ደሀ ?
መንገድ ላይ ነኝ
– ወደየትኛው እየሄድክ ነው ?
አላቀውም ። ግን እየሄድኩ ነው ።
-ትደርስ ይሆን ?
አቊዋራጭ ከተገኘ ።
ፐረረም ተረረም
ተረረም ፐረረም
– ከሁሉ ነገር ምን ትጠላለህ ?
ፍረሀትን
– ምን ትፈራለህ?
ባዶነትን
– ምን ትወዳለህ ?
መወደድን

ፐረረም ተረረም
ተረረም ፐረረም
– የምትናገረው ሁሉ ይቃረናል
አዎ ።
– ለምን ይመስልሀል ?
ካፈጣጠሬ ነው ።
– በምንና በምን
በመኖርና ባለመኖር
በውሸትና በውነት
በማወቅና ባለማወቅ
በመውደድና በመጥላት
በዚህና በዚያ
በመምሰልና ባለመምሰል
በብዙና በብዙ
በሌለና በሌላ ይለያያል ።
– ጥሩ ብለሀል !
ጥሩ ብያለሁ ።
ፐረረም ተረረም
ተረረም ፐረረም
– ገኒ ምንህ ነች ?
ገነቴ ነች ።
– -እንደምድረኛው ወይስ እንደላይኛው ?
እንደሁለቱም ።
– እምዴትና እንዴት ?
እምደምድሩ አያታለሁ
እንደላይኛው አልማታለሁ ።
– ትገርማለህ !
ግርም ልበልልህ !
ፐረረም ተረረም
ተረረም ፐረረም
– በአእምሮህ ውስጥ አሁን እየተመላለሰ ያለው ነገር ምንድን ነው ?
አሁን ?
– አዎ አሁን ።
አዋጅ ።
እንዲህ የሚል…
– እኮ እንዴት የሚል ?
ከዚህ በፊት አዳምና ሄዋን የፈጣሪን ስልጣን በመጋፋታቸውና ፣ በለስ በመቅጠፋቸው ምክንያት የእብራይስጥኛ ቊዋንቁዋ በቁጥር እግዚ —-የተፃፈው የእገዳ አዋጅ። የተነሳ መሆኑ ታውቆ ማንኛውም ግለሰብ ያለምንም ሀፍረት እርቃኑን። እንጥልጥሉን እያንጀላጀለና ሽቅብ ቅዷን እየላጨች በአደባባይ መሄድ የሚችል / የምትችል መሆኑን እንዲያውቅ የሚል ።
– ይህ እንዴት በአእምሮህ መጣ ?
ዝም ብሎ መጣ ። እኔ አላመጣሁት ።
– አዋጁ እውን ቢሆንስ ?
እራስህ እየዋ ። ውጤቱን በሀሳብህ እየው ። አሁን ሁሉም ሰው እርቃኑን ቢሄድ ሥር ነቀል ለውጥ ያለ አይመስልህም ?
– በርግጥ ብርድና ቁርጥማን ልትለኝ ይሆናል ። እሱ ይለመዳል ።ግን በሀሳብህ ይታይህ ….
አሁን ውበት እያልን እምናላዝነው ሁሉ ያኔ መልኩን ይለውጣል ። በልብስ ሽፋን ታጅሎ የሚሄድ ግድንግድ ፣ ጠባሳ ፣ ጀላፋ እግር ፣ ዝርፍጥ ሆድና ጨጎጎታም ቆዳ ሁሉ ይጋለጣሉ ። ሰላም ፣ ሰላም ይወጣል ። ያኔ ኩራት ይጠፋል ፤ ውበት ብርቅ ብርቅ ይሆናል ።
– ግሩም ሀሳብ ነው ።
አዎ በተግባር ሊውል የማይችል ሀሳብ ሁሉ ግሩም ነው ።
– በተግባር የማይውል ከሆነ ለምን ታስባለህ ?
እሱ በራሱ ጊዜ ሲመጣስ ።
– ፐረረም ተረረም ገንዘብ ትወዳለህ። ?
እሱ አይወደኝም እንጂ
– ምን ያረግልሀል ?
እርመሰመስበታለሁ ።
– ከወዴት ወዴት ?
ካለሁበት ወደሌለሁበት
– እንዴት እንዴት ?
ያልሆንኩትን በመሆን
– ያልሆንከውን እንዴት ትሆናለህ ?
የሆንኩትን ባለመሆን
– አይገባኝም ።
አመሰግናለሁ
– ደደብ
ስሜ ነው
-እኔ እምልህ
አንተ እምትለኝ
– አወኩ አወኩ ለምን ትላለህ ?
ስላወኩ ነዋ
– አለማወቅህን ግን ታውቃለህ ?
ሶቅራጥስ ስላወቀው ምን ያረግልኛል ።
– ምኑን ?
አለማወቅን
– ታድያ የምትፈልገው ምኑን ነው ?
እውቀትን
-ግራ ታጋባለህ
እኔ ልጋባልህ ።

DD
1983  taken from Senedu Abebe Fb page

ተረረም – ፐረረምጠያቂና መላሽ – የእብዶች ጨዋታ- ፐረረም ተረረምተረረም ፐረረም-ፐረረም ተረረምተረረም – ተረረም – ደስ አይልም ? አይልም !-ያስጠላል ?አያስጠላም…

Публикувахте от Senedu Abebe в Вторник, 7 март 2017 г.

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *