ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ 46 ሰዎችን ገደለ፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው አልታወቁም፣ የዝቋላ ገዳም ደን ነደደ

“ቤቴ እዚያ ጋር ነበር፡፡ መደርመሱ ሲከሰት እናቴ እና ሶስት እህቶቼ በውስጡ ነበሩ፡፡ የሁሉንም ዕጣፈንታ አላወቅኩም ”

በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የቆሻሻ ክምር በድንገት ተደርምሶ ቁጥራቸው 46 የሚሆኑ ነዋሪዎች ህይወታቸው ማለፉ ተዘገበ። 32 ሴቶቻን 14 ወንዶች ህይወታቸው ማለፉን ከንቲባ ድሪባ ኩማ በቢሯቸው በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል። የመንግስት ሚዲያዎች በስእል አስደግፈው እንደዘገቡት ተጎጂዎች መውደቂያ የሌላቸው መሆኑንና በአደጋው ሙሉ በሙሉ ንብረታቸው መውደሙን ተናግረዋል።

የአለርት ሆስፒታል ሙሉ የርብርብ ስራ በመስራት አካላቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን እየረዳ እንደሚገኝ ስራ ስኪያጁ አስታውቀዋል። የአዲስ አበባ አስተዳደር የሟቾች ቁጥር እንደሚጨምር የገለጸ ሲሆን የአስከሬን ፍለጋና የነብስ አድን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አረጋግጧል። የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው መካክለ አንድ እናት በአለርት ሆስፒትታል ሆነው ” ከወገቤ በታች ሰውነቴ አይንቀሳቀስም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ፖሊስ የአደጋውን መንስዔ በይፋ አላስታወቀም። የአደጋው መጥንም አልተገለጸም። አደጋው ወገኖችን ያሳዘነ ድንገተኛ ዱብዳ እንደሆነ የተለያዩ ሚዲያዎች ገለጸዋል። በተለይ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ጥልቅ ሃዘናቸውን ሲያስተላልፉና ለጉዳተኞች መጽናናትን ሲመኙ ውለዋል። የአዲስ  አበባ ከንቲባም አደጋው ዘግናኝ መሆኑንን ጠቅሰው የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ከአደጋው ለተረፉት የሰብአዊ ድጋፍ መደረጉን ከመግለጽ በዘለለ አስተዳደራቸው ለወደፊቱ ምን ሊያደርግ እንዳሰብ አለተናገሩም።  ዝግጅት ክፍላችን በአደጋው ለተጎዱና ህይወታቸውን ላጡ ሁሉ የተሰማውን ትልቅ ሃዘን ይገልጽላ

“ቤቴ እዚያ ጋር ነበር፡፡ መደርመሱ ሲከሰት እናቴ እና ሶስት እህቶቼ በውስጡ ነበሩ፡፡ የሁሉንም ዕጣፈንታ አላወቅኩም ”

የጀርመን ሬዲዮ አማርኛ ክፍል

Related stories   የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

ለአዲስ አበባ ከተማ የቆሻሻ መጣያ በሆነው በዚሁ ስፍራ ይኖሩ በነበሩ ሰዎች ላይ የመደርመስ አደጋው የደረሰው ትናንት ቅዳሜ ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዳግማዊት ሞገስ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የቆሻሻ መጣያ ስፍራው ሰፊ ስፍራን የሚሸፍን በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር አሁን ካለውም ሊጨምር ይችላል፡፡

Äthiopien Erdrutsch (picture-alliance/AP Photo/E. Meseret)የአካባቢው ነዋሪዎች በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም መሞት አሊያም መትረፋቸው አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

Related stories   የበልግ ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

በአደጋው በርካታ ቤቶች በቆሻሻው ክምር መዋጣቸውን አሶሴትድ ፕሬስ ከስፍራው ዘግቧል፡፡ የዜና አገልግሎቱ ያነጋገራቸው አሰፋ ተክለሃይማኖት የተባሉ ነዋሪ ወደ 150 የሚጠጉ ነዋሪዎች አደጋው በደረሰበት ቦታ ነበሩ ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ 37 ሰዎችን ከአደጋው ማትረፍ መቻሉን እና ተጎጂዎቹ የህክምና እርዳታ እያገኙ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የአሶሴትድ ፕሬስ ዘጋቢ ከቆሻሻው ክምር ስር የወጣ የአራት ሰዎች አካላት በአምቡላንስ ሲወሰድ ተመልክቷል፡፡ ስድስት ኤክስካቫተሮች ከቆሻሻ ክምሩ ውስጥ ተጨማሪ ሰዎች ለማግኘት ሲቆፍሩ ነበር፡፡ ተበጁ አስረስ የተባለች የአካባቢው ነዋሪ ቆፋሮው ወደሚካሄድበት ቦታ እያመላከተች “ቤቴ እዚያ ጋር ነበር፡፡ መደርመሱ ሲከሰት እናቴ እና ሶስት እህቶቼ በውስጡ ነበሩ፡፡ የሁሉንም ዕጣፈንታ አላወቅኩም”ብላለች።
አደጋው በደረሰበት ቦታ አዛውንቶች ሲያለቅሱ የታዩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በአካባቢው ቆመው የቤተሰቦቻቸውን እና ወዳጆቻቸውን መጨረሻ ለማወቅ በጭንቀት ሲጠብቁ ተስተውለዋል፡፡ በአካባቢው የነበረው የቆሻሻ መጣያ አዲስ አበባ ከተማን ለ50 ዓመታት ያገለገለ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ግን አገልግሎቱ ቆሞ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቦታው እንደገና ቆሻሻ መጣል መጀመሩ ለአደጋው መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ የአካባቢው ነዋሪ ለአሶሴትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡

Related stories   የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ

በሌላ ዜና የዝቋላ ደን ላይ የተነሳው ቃጠሎ አየር ሃይል፣ ኦሮሚያ ፖሊስና የአካባቢው ህብረተሰብ ባደረጉት ርብርብ መጥፋቱ ተጠቁሟል። ደኑ ሰፊ ሽፋን የነበረውና ጥቅትቅ የተፈጠሮ ደን የሞሉበት ነው። እሳቱ አንዴ የጠፋ እየመሰለ እንደገና ይነሳ ነብረ። ደኑ ይህን መሰል አደጋ ሲያጋጥመው ተደጋጋሚ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። ደኑ በአካባቢው ነዋሪዎችም ውድመት የሚደርስበትና ተንከባካቢ ያጣ መሆኑ ተወሰቷል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0
Read previous post:
” ድፍን ኦህዴድን አታውግዙ፣ ተጠቃሚው ሌላ አካል ነውና”

"ዳኞቹ  ምን ተሰምቷቸው ይሁን?" ይላል ሶስት እነድሆኑ ጠቅሰው መልዕክት የላኩት ክፍሎች። " አጭር እና የልብ...

Close