“Our true nationality is mankind.”H.G.

“… መከላከያ ሰራዊታችን ጠንክሮ ባይጠብቅ ኖሮ ከዚህም በባሰ መልኩ ጥቃት ይፈጽሙ ነበር” መንግስት

በጋምቤላ የሙርሲ ጎሳዎሽ  ላደረሱት ተደጋጋሚ ጥቃት ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዛዲግ አብርሃ  መከላከያ ሰራዊት ጠንክሮ ባይጠብቅ ኖሮ ከዚህም የሚብስ ጥቃት ሊፈጸም ይችል እንደነበር ተናገሩ። ሚኒስትሩ የማያዳግም ርምጃም እንደሚወሰድ ገልጸዋል። የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ እንደሚገለጹት በቂ ጥበቃ አይደረግም። ጥቃቱ ከመከናወኑ በፊት የመንግስት አካላት መረጃ እንደነበራቸው በተደጋጋሚ እየገለጹ ነው።

አቶ ዛዲግ ርምጃ ይወሰዳል ከማለታቸው በቀር መቼና እንዴት፣ እንዲሁም ምን ያህል በደል እስኪፈጸም እንደሚጠብቁ አልተገለጸም። የመከላካያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈርጌሳ በአካባቢው የመሰረተ ልማት ግንባታ በማከናወን ችግሩን እስከመጨረሻ ለመቅረፍ፣ እንዲሁም የድልድይና የምንገድ ግንባታ እየተካሄደ መሆኑንን ለፋና ተናግረዋል። ድልድይና መንገድ የሚገነባው ሙርሲዎችን ለመምታት ይሁን ለሌላ የተባለ ነገር የለም። በተደጋጋሚ  ህጻናት በአስከፊ ሁኔታ እየታፈኑና ህዝብ እየሞተ ባለበት ወቅት ሁለቱም ሚኒስትሮች የሰጡት ምላሽ ከደረሰው አደጋ በላይ ስሜት የሚጎዳ እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠ ነው። የሰንደቅ ዜና ከዚህ የሚከተለው ነው።

ከደቡብ ሱዳን አማፂ ቡድኖች አንዱ የሆነው የሙርሌ ጎሳ በስምንት ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በርካታ የጋምቤላ ክልል ህጻናትን አፍኖ ሲወስድ ሰዎችንም ገድሏል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ድንገተኛ ወረራ አድርጎ የነበረውና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጋምቤላ ተወላጆችን ገድሎ፣ ቤታቸውን አቃጥሎ እና ንብረታቸውን ዘርፎ የተመለሰው የሙርሌ ጎሳ መጋቢት 1 እና 2 ቀን 2009 ዓም በድጋሚ ወረራ በማድረግ ተመሳሳዩን ድርጊት ፈጽሞ መሰወሩን ከጋምቤላ የሰንደቅ ጋዜጣ ምንጮች ገልጸዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ ብለው መረጃውን ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹ አንድ የክልሉ የስራ ኃላፊ “የክለላችን የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ እና የፖሊስ ኮሚሽነሩ የመስክ ጉብኝት እያካሄዱ ነው። እኔም በግሌ አንድ ቀበሌ የጎበኘሁ ሲሆን በጎበኘሁት ቀበሌ 14 ሰዎች ሞተዋል፣ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ቁጥራቸው የማይታወቅ ዜጎች ደግሞ ታፍነው ተወስደዋል። ከዚህ በተጨማሪም ንብረቶቻቸው ተዘርፈው ተወስደዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ጋምቤላ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡኩኝ ኡኬሎ ደውለን ጠይቀናቸው ነበር። ሆኖም አቶ ኡኩኝ ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ገልጸው “ቆይታችሁ ደውሉ” ባሉን መሰረት ደጋግመን ብንደውልም ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ድረስ ከስብሰባ ባለመውጣታቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

የክልሉ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኡመድ ኡቶ በበኩላቸው ጉዳቱ መከሰቱን አምነው “ሆኖም ግን የተጣራ መረጃ ስለሌለ ይህን ያህል ጉዳት፣ ይህን ያህል ሞትና እንዴት እንደተፈጸመ መግለጽ አልችልም” ሲሉ መልሰዋል። የደረሰውን ጉዳት እና እየተደረገ ያለውን የመንግስት እርምጃ በተመለከተ ምን መልክ እንዳለው የጠየቅናቸው አቶ ኡመድ “ከዚህ ውጭ ልነግርህ የምችለው መረጃ የለም” ብለዋል።

የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው “መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓም ከምሽቱ 8 ሰዓት በአንድ ቀበሌ ጥቃት ፈጽመው ብዙ ቤቶችን አቃጥለው፣ 12 ሰዎችን ገድለዋል ወደ 22 የሚሆኑ ሀጻናትን ደግሞ አፍነው ወስደዋል” በማለት ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጠዋል። “የፌዴራል መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ምን እያደረገ ነው?” ለሚለው ጥያቄ አቶ ዛዲግ ሲመልሱ “ድርጊቱን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ከክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ ጋር በመሆን የሁለቱን አገራት ድንበሮች ዘግቶ እየጠበቀ ይገኛል። ተከታትሎም የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል” ብለዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

የሙርሌ ጎሳ አባላት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ጥቃት ሊከፍቱ የቻሉት በምን ምክንያት ነው? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ “የመከላከያ ሰራዊት አገርን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ይጠብቃል። ካለፈው ጊዜ ጥቃት በኋላ ድንበሮቻችን አካባቢ የተጠናከረ ጥበቃ መከላከያ ሰራዊታችን ሲያደርግ ቆይቷል። ሙርሌዎች በባህላቸው ህጻናትን አፍኖ የመወሰድ ባህል ሰላላቸው መከላከያ ሰራዊታችን ጠንክሮ ባይጠብቅ ኖሮ ከዚህም በባሰ መልኩ ጥቃት ይፈጽሙ ነበር” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ከዚህ በኋላ ግን መከላከያ ሰራዊታችን የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ያደርጋል። ዘላቂው መፍትሔ የደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ማቆም ነው። ነገር ግን የእርስ በእርስ ጦርነቱ እስኪቆም ድረስ ዜጎቻችን መሞት የለባቸውም። ለዚህም መንግስት ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥረት በማድረግ ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት በማጠናከር ሙርሌዎችን ከድርጊታቸው እንዲያቆሙ የዲፕሎማሲ ስራ ይሰራል” ሲሉ ተናግረዋል።¾

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0