“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከፍተኛ አመራሩን “የወሬ ቋት” የሚለው የስኳር ፕሮጀክት ሪፖርተና አዙሪቱ!!

የአንደኛው እና የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በኢንዱስትሪው ልማት ዘርፍ ብዛት ያለው የሰው ኃይል በመያዝ ትኩረት ከተሰጣቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል የስኳር ፋብሪካ ኢንዱስትሪ ግንባታዎች ዘርፍ አንዱ ነው። በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ከታቀዱት አስር የስኳር ፋብሪካ ግንባታዎች መካከል የከሠም ስኳር ልማት ፕሮጀክት አንዱ ነው።

ከከሰም ስኳር ፋብሪካ ጋር በተያያዘ በሰንደቅ ጋዜጣ ቁጥር 597 “ከሠም ስኳር ፋብሪካ የሒሳብ ቋት የለውም፤ ሠራተኞች ቅሬታ አላቸው” በሚል ዘገባ አቅርበን ነበር። ይህ ዘገባ ከቀረበ በኋላ የስኳር ኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ከሠም ስኳር ፋብሪካ በአካል ተገኝተው የከሠም ስኳር ፋብሪካ ምርታማነት መቀነስ በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

በመጀመሪያ ከኮርፖሬሽኑ የቴክኒካል ግምገማ ለማድረግ የተንቀሳቀሱት የቡድን አባለት አቶ ታፈሰ  ሰብሳቢ፣ አቶ መርጋ  አባል፣ አቶ መርሻ  አባል እና አቶ ጌታቸዉ አባል ናቸው። ይህ ቡድን ከተለያዩ ሥራ ዘርፎች ግብረ መልሶች ሰብስቦ ለተቋሙ አቅርቧል።

ከተሰበሰበው ግብረ መልስ በኋላ  የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዋዩ ሮባ እና  የኮርፖሬሽኑ ስትራቴጂክ ድጋፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በዛብህ ገ/የስ ከሠም ፋብሪካ በመገኘት ከቡድን መሪዎች በላይ የሆኑትን አመራሮችን ሰብስበው አወያይተዋል።

 ለከሰም ምርታማነት መቀነስ ከተወያዮቹ የቀረቡ ምክንያቶች

ከፍተኛ አመራሩ እርስ በርስ የማይተማመን መሆኑ፤ ከፍተኛ አመራሩ የወሬ ቋት መሆኑ፤ ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር ያለ መሆኑ፤ ግልፅነት የጎደለዉ የደረጃ እድገት፣ ቅጥር፣ ዝዉዉር መኖሩ፤ ግልፅነት የጎደለዉ ሹም ሽረት መኖሩ፤ የኪራይ ሰብሳቢነት ዝንባሌዎች መኖራቸው፤ የሪፖርት አፈፃፀም ግምገማ ተደርጎ የማያዉቅ መሆኑ፤ የከፍተኛ አመራሩ የቡድን ስሜት የሌለ መሆኑ፤ አብሮ የማይሰራ ማኔጅመንት መኖሩ፤ ከፍተኛ አመራሩ አድርባይ መሆኑ፤ ፋብሪካዉ ተነጥሎ ብቻዉን ያለ መሆኑ፤ በእዉቀት እየተመራ እንዳልሆነ በሰፊዉ መነሳቱ፤ ፍትሃዊ የሆነ የዲሲፕሊን እርምጃ አለመኖር፤ የኃላፊዎች የስነምግባር ብሉሽነት፤ የከፍተኛ አመራሩ አቅም ማነስ፤ የአሰራር ስርዓት አለመኖር፤ የማሽነሪ አደጋ መብዛት፤ የመንገዱ ርቀት፤የባለቤትነት ስሜት ማጣት፤ የአገልጋይ መንፈስ የሌለ መሆኑ ተነስቷል።

እንዲሁም፤ ንብረት ቆጠራ ይፋ ሳይደረግ ሂሳብ መዝጋት እንደማይቻል፤ የ2007 ዓ/ም ያልተወራረድ የግዥ ሰነድ ያለ መሆኑ፤ የጥብቅነት አሰራር አሁንም ያለ መሆኑን እና ከአንድ ዓመት በላይ የሰሩ አመራሮች ያሉ መሆናቸው፤ ያለዉክልና ቡድን እንዲመሩ ማድረግ፤ እንደ ሃገር ከሰም ላይም  ያለ መሆኑ፤ ድጋፍ እና ክትትል እኩል ያለ ማየት እንዲሁም ማግለል፤ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ በቁርኝት ያለመስራት፤ ከወረዳ አመራሮች በቁርኝት ያለመስራት ከተነሱት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

Related stories   መንግስት ከግብርናው ዘርፍ ስኬት ቆንጥሮ በዳታ የተደገፈ መረጃ ይፋ አደረገ - አቡካዶ ቀጣዩ ወርቅ !

በተለይ ሁሉም አመራሮች በሚባል ደረጃ የጠባቂነት መንፈስ መኖሩ፤ መተጋገል የሌለ መሆኑ፤ የፈፃሚ ሠራተኞች የማበረታቻ ስርዓት ያለመኖር፤ ፍትሃዊ ያልሆነ የዲሲፒሊን እርምጃ፤ ቅሬታ በአግባቡ የማይፈታ መሆኑ፤ የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ የሌለ መሆኑ፤ ችግር ፈቺ ማኔጅመንት የሌለ መሆኑ፤ የሰዉ ኃይል ፍልሰት እና የመኖርያ ቤት ችግር እንዳለ ቀርበዋል።

ከዘርፉ የተገኙ ግብአቶች፤ የአሚባራ አገዳ እንክብካቤና አመራር፣ ቆረጣና ለቀማ፣ አጫጫንና ትራንስፖርት እና የማሳ ውስጥ መንገዶች ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ከቴክኒክ ድጋፍ ባሻገር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ክትትል ቢደረግ፤ በየቦታው በብልሽት የሚቆሙ ጋሪዎችን ተከታትሎ አገዳውን ከጥፋት ማዳን ቢቻል፤ የተገለበጡ ጋሪዎች በቀላሉ በማንሳት ወደ ስራ ማስገባት ሲቻል ችላ መባል የለበትም፤ የስምሪት አመራሩ ያሉት ጠንካራ ጎኖች እንደተጠበቀ ሆኖ ጠባቂነትና ችላ ባይነት የሚታይባቸው አካበባቢዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠይቃል፣

ከሲቨል ምህንድስና የተገኙ፤ ሠራተኛውና ፋብሪካው ያለበት ሳይት በአቀማመጡ ለጎርፍ ተጋላጭ ስለሆነ ስጋት በሚፈጥሩ ቦታዎች ላይ ዳይክ ቢሰራ፤ የመኖሪያ ቤቶች፣ የሽንት ቤት፣ መጠጥ ውሃና መንገድ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ ተጠናክረው ቢቀጥሉ፤ ከፋብሪካ ውሃ አቅርቦት ጋር የሚነሳው የሶሻል ጉዳዮች አማራጭ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ቢደረግ፤ ቀጣይ የክረምት ወቅት የሚመጣ ስለሆነ በቀበና ወንዝ ላይ የሳይፈን ግንባታው በራስ አቅም ከወዲሁ ትኩረት ተሰጥቶት ቢሰራ፤ በቡድኑ በመዋቅሩ መሰረት በርካታ ባለሙያዎች የተመደቡለት ቢሆን የስምሪትና የስራ ድርሻ ለይቶ ከመስጠት አንፃር የሚታይ ክፍተት፤ ቀጣይ የክረምት ወቅት ከመምጣቱ በፊት ድልድዩ በፍጥነት ተጠናቆ ወደ ስራ የማይገባ ከሆነ ለተጨማሪ ድካም ስለሚዳርግ ትኩረት ቢሰጠው፤ ከኮንትራከተሮች ጋር ያለው ግንኙት ተጠናክሮ የግንባታ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቢደረግ፤ በማሽነሪ እጥረት ምክንያት ያልተጠረጉ ሰከንደሪ ካናሎችና ኩሬዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰሩ ቢደረግ።

Related stories   መንግስት ከግብርናው ዘርፍ ስኬት ቆንጥሮ በዳታ የተደገፈ መረጃ ይፋ አደረገ - አቡካዶ ቀጣዩ ወርቅ !

በፋብሪካ ዘርፍ የተገኙ፤ በኬን አንሎዲንግ ቦታ የሚታየው የአገዳ ብክነት ትኩረት ቢሰጠው፤ ያላለቁ የፕሮጄክት ስራዎችን የኮሚሽኒንግ ስራ ትኩረት ቢሰጠው፤ ከማቴሪያል ጥራት ጋር ተያይዞ አሁን የሚታዩ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ የሚሄዱበት አግባብ ቢፈጠር፤ የፊለተር ኬክ ክምችት ፈጣን መፍትሄ ቢሰጠው፤ የቴክኒክ ስልጠናዎች ችግር ከውል ስምምነቱ ጀምሮ መታየቱ ትኩረት የሚሰጠው፤ የዕቅድ ክንውንና ዕቅድ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የታለመው ሁሉ ቢደረግ፤ የመከላከያ አልባሳት ጉዳይ ትኩረት ቢሰጠው፤ ከእርሻ ኦፕሬሽን ስራ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን፣ ከአገዳው ጋር ባዕድ ነገር መምጣጡ፣ የሚስተካከልበት መንግድ ቢታሰብበት።

ከፋይናንስ ዘርፍ የተገኙ፤ ንብረት ሲመጣ ሙሉ ሰነድ ይዞ የሚመጣበትን ሁኔታ ክትትል በማድረግ ማስተካከል ቢቻል፤ በንብረት ቆጠራ ስራ ላይ የገጠመ የንብረቶች ስያሜ መለያየት ችግርን ለመፍታት የተጀመረው ጥረት እንዲጠናከር ቢደረግ፤ የመንግስትን ግዴታ ለመወጣት ከግብይት መምጣት ያለበት ሰነድ ጊዜ ባይሰጠው፤ የማቴሪያል ዝውውር ከበቂ ሰነድ ጋር የተደጋገፈ ቢሆን፤ ያልተፈቱ የአሚባራ እርሻ ጉዳዮች እልባት እንዲያገኙ ከሚመለከተው ክፍል ጋር ቢሰራ፤ ገንዘብ ወጪ አድርገው ያልተወራረደላቸው ሠራተኞች ለሰራተኞቹም ሆነ ለድርጅቱ ስለማይጠቅም ትኩረት ቢሰጠው፤ የቻርት ኦፍ አካውንት እንደ ኮርፖሬሽን ወጥ አለመሆን ቢስተካከል፤ በዕቅድ የታገዘ የፒቲ ካሽ ማኔጅመንት ስራ ቢጠናከር፣ እንዲሁም ከአዋሽ ወጪ መደረጉ ታስቦ አማራጭ መፍትሄ ቢወሰድ፤ የካይዘን እንቅስቃሴ ቢጠናከር የሚሉ ይገኙባቸዋል። እንዲሁም የ2004፣ 2005፣ 2006 እአ 2007 ሂሳብ በመዝጋት በአማካሪ ኦዲተር ለማስመርመር እየተደረገ መሆኑ ተገልፆ፤ የ2008 ለመዝጋት ያላቸውን ዝግጁነት አንስተዋል።

ከዕቅድ ዘርፍ የተገኙ፤ የአፈፃፀም ሪፖርት ቢዘጋጅም ለሰራተኛው አልቀረበም፤ ስራዎችን ወደ ሲስተም አምጥቶ ለመስራት ክፍተት አለ፤ አፈፃፀምን ከዕቅድ ጋር አለማያያዝ፤ ዶክመንቶች አያያዝ ላይ በተለይም ፋይናንሻል ሰነዶች ላይ ክፍተት አለ። በተለይም ከሴክሽን ወደ ዘርፍ መምጣት አለበት የተጣራም መሆን ይቀረዋል (የተቆረጡ ማሳዎች ማሽነሪ ሀወር)፤ ዕቅድን ከወረቀት ላይ ማትረፍ ባሻገር አለመስራት፤ የኔትወርክ ስትራክቸር የለም፣ ለሌሎች ፋብሪካዎች የሚደረገው ድጋፍ የለም፤ ኢንተግሬትድ ሲስተም የለም፤ ሲስተም ይኑር፣ መተሳሰር ይኑር የሚሉ ይገኙበታል።

Related stories   መንግስት ከግብርናው ዘርፍ ስኬት ቆንጥሮ በዳታ የተደገፈ መረጃ ይፋ አደረገ - አቡካዶ ቀጣዩ ወርቅ !

በውይይቱ ማጠቃለያ ነጥቦች የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዋዩ ሮባ ያላቸውን የግምገማ ውጤት ሲያስቀምጡ እንደተናገሩት፤ የፋብሪካዉ ከፍተኛ አመራሮች ስትራቴጂክ ሆኖ ያለመምራት፤ የማኔጅመንቱ የቡድን ስሜት ያለመኖር፤ ለተፈጠረው ክፍተት የከሰም ስኳር ፋብርካ ማኔጅመንት እና የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አማራሮች ሃላፊነት መሆኑን፤ ከፍተኛ አመራሩ አድርባይ የማይታገል እንደነበረ፤ ከፍተኛ አመራሩ ጠባቂነት መንፈስ ያለዉ መሆኑ፤ የክትትል እና ቁጥጥር ግምገማ አለመኖር (ይህም ሲባል የአንድ ወር፣ የሶስት ወር እና የስድስት ወር ግምገማ አለመኖር)፤ የአካባቢ ማህበረሰብ አለማሳተፍ ፤ የከፍተኛ አመራሩ ቡድንተኝነት መኖሩ፤ ቡድን መሪዎች መታገል ላይ ክፍተት ያላቸዉ መሆኑ፤ ከፍተኛ አመራሩ ባለፉት ስምነት ወራት ያልነበረ መሆኑ፤ አሰራሮች ተከብረውሮ እየተሠራ እንዳልነበረ በግልፅ በመድረኩ ላይ አስቀምጠዋል።

እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ስትራቴጂክ ድጋፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ የአቶ በዛብህ በሰጡት የማጠቃለያ ነጥቦች እንዳስቀመጡት፤ የተበተነ የመካከለኛ አመራር መኖሩ፤ ከፍተኛ አመራሩ ችግር ፈቺ አለመሆኑ፤ ከፍተኛ አመራሩ ዉሳኔ ሰጭ አመራር አለመሆኑ፤ አድርባይ ማኔጅመንት መኖሩን፤ ለዉድቀቱ የመጀመርያ የከፍተኛ አመራር አብሮ አለመስራት፤ ተጠያቂነት አለመኖር፤ ችግር ፈቺ ማኔጅመንት ያለመኖር፤ ከአካባቢ ማህበረሰብ ጋር አብሮ ያለመስራት መሆናቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይ ከግምገማው ውጤት ቀጣይ አቅጣጫዎች መነሻ የትኩረት አቅጣጫዎች ሰፍረዋል፤ በየደረጃዉ የአመራር መድረክ ማዘጋጀት፤ ለከፍተኛ አመራሩ የቡድን ስሜት በመፍጠር መስራት፤ በአንድ ወር ዉስጥ ምርት ላይ ለዉጥ ማምጣት፤ ማህበረሰቡን አሳታፊ ማድረግ፣ አብሮ መስራት፤ የበታች አመራሮች እና ፈፃሚዎች መደገፍ፣ መከታተል፣ ማብቃት፤ ከፍተኛ አመራሩ ስትራቴጂክ ሆኖ መምራት ይኖርበታል። ከፍተኛ አመራሩ ችግር ፈቺ መሆን፤ የአሚባራ ሂሳብ በአንድ ወር ዉስጥ መዝጋት፣ ማስተካከል፤ ባጠቃላይ ያለዉ የሂሳብ አያይዝ ክፍተት ማስተካከል፣ ማረም፤ጥንስስ ቡድንተኝነት ማስወገድ፤ ህግና ደንብ ማክበር፣ ማስከበር፤ ጥራት ያለዉ ደረጃ እድገት፣ ቅጥር ማካሄድ፤ ከአድርባይነት ነፃ መሆን እና መተጋገል እንዳለባቸው፤ በማሽነሪ አያያዝ ላይ ለዉጥ ማምጣት፤ ዉሳኔ ሰጭ ማኔጅመንት አመራሮች መፍጠር፤ በተነሱት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ መወያየት እና መፍትሔ ማስቀመጥ ናቸው።

ሰንደቅ ጋዜጣ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0