በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ ይባብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አባወራ ቤቶች ሕገ ወጥ ግንባታ ናችሁ በሚል እንደፈረሱ ተጎጂዎች ተናገሩ። በዚህ ምክንያት በተፈጠረ ግጭት ብዙ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች እንደተደበደቡና አንድ ሰውም በደረሰበት ጉዳት ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል።

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ማርቃ ወረዳ ለከተማ ማስፋፋያ በሚል ከ180 በላይ የሚሆኑ የአባወራ ቤቶች በኃይል እንደፈረሱም የጉዳቱ ሰለባዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል። በሁለቱም ክልሎች ከዚህ ጋር ተያይዞ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል የአማራ ክልል ቃል አቀባይ በበኩላቸው ሕገወጥ የተባሉ ቤቶች መፍረሳቸውን ገልፀው ተፍፅሟል የተባለው ድብደባ ስለመድረሱ ግን መረጃ እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *