ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

አስገራሚ ተፈጥሮዎች

በመጀመሪያዎቹ ብትገረሙም እነዚህ ሁለቱም ያስገርማሉ። የሰው ተፈጥሮ እጅግ ድንቅ ነው።
3) በዓለም ትልቁን የሴት ብልት (የመራቢያ አካል) በመያዝ ባለ ሪኮርድ የሆነችው አንና ስዋን የተባለች እና ከ1846-1888 የኖረች ስኮትላንዳዊት ናት። የአንና ብልት 48.26 ሴንቲሜትር (ግማሽ ሜትር የሚጠጋ) ይሰፋ ነበር። አንና በሰውነትዋም ግዙፍ ስለነበረች ስኮቲሽ ጂያንት ትባል ነበር።
4) በአንና ትገረሙ ይሆናል። ጆናህ ፋልኮን የተባለ (ዛሬም ያለ) አሜሪካዊ አክተር ብልቱ 34.29 ሳንቲ ሜትር ይረዝማል።
5) ይሄ ሪክርድ የሚባል ነገር መቼም የማያሰማን የለም። ሊዛ ስፕራክስ የተባለች አሜሪካዊት ደግሞ በአንድ ቀን ብቻ ከ919 ወንዶች ጋር ግብረ-ስጋ ግንኙነት በማድረግ ሪኮርዱን ይዛለች። ብዙዎች ለመስበር ይጥራሉ፤ እስካሁን አልተሳካላቸውም።

ዛሬ ከሳይንሱ ትንሽ ወጣ ያሉ አስገራሚ መረጃዎችን እንስጣችሁ

በዓለም ላይ እጅግ ብዙ አስገራሚ ነገሮች አሉ፣ እናያለን፣ እንሰማለን። እነዚህን ግን የማንጠብቃቸው ናቸው፥
1) ብዙ ግዜ አንዲት እናት አስር ወይም አስራ ምናምን ወለደች ሲባል እንገረማለን። ከ1707-1782 የኖረችው ቫሌንቲና ቫሲሌቫ የተባለች ራሺያዊት ግን 69 ልጆች በመውለድ ሪኮርዱን እስካሁን ይዛለች። 16 ጊዜ መንታ፣ ሰባት ግዜ ሶስት፣ አራት ግዜ አራት ህጻናትን በመውለድ። ከርስዋ ቀጥላ ዛሬም ያለችው ሊዮንቲና አልቢና የተባለች የቺሊ ሴት 64 ልጆች በመውለድ ትከተላለች። መንታ ሳትወልድ 18 የወለደችው ደግሞ ሊቪያ ኢዮንሴ የተባለች ሮማኒያዊት ናት።
2) ከወንዶች ደግሞ ሙላይ ኢስማኤል ኢብን ሻሪፍ የሚባል ከ1634-1727 የኖረ የሞሮኮ ንጉስ 867 የአብራኩ ክፋይ የሆኑ ልጆች ነበሩት።

አፍላቶክሲን የደቀነው ጣጣ
አፍላቶክሲን (Aflatoxin) የተባለው ንጥረ ነገር ከመጠን በላይ በምግቦች ውስጥ መገኘት ለካንሰር እና መሰል በሽታዎች እንደሚያጋልጥ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። መረጃዎች እንድሚያሳዩን በአፈር ውስጥ እንዲሁም በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰቱ ፈንገሶች (molds like Aspergillus flavus and Aspergillus parasiticus) አፍላቶክሲንን ይፈጥራሉ። በአግባቡ እና ደረጃውን ባልጠበቀ መልኩ በሚከማቹ የምግብ ሰብሎችና ፍራፍሬዎች ላይ እነዚህ ፈንገሶች ሲፈጠሩም በምግቡ ውስጥ አፍላቶክሲን ይገኛል። የዋዜማ ራዲዮ ጫፍ ባስያዘን መሰረት ይህን መረጃ እንስጣችሁ። ሼር ብታደርጉት ብዙዎችን መጥቀም የሚችል መረጃ ነው።
1) ከሁለት አመት በፊት በኢትዮጵያ የተደረገ አንድ ጥናት በወተት ውስጥ ከፍ ያለ አፍላቶክሲን መጠን እንደሚገኝ መጠቆሙን ተከትሎ ጉዳዩ በሃገር ውስጥ በሚታተሙ ጋዜጦች ለንባብ በቅቶ ነበር። እዚህ ፌስቡክ ላይ ሳይቀር ከፍተኛ መነጋገርያ ሆኖ ሰንብቶ ነበር። ተከትሎም በወተት እና የወተት ተዋጾዎች ላይ ከፍተኛ የገበያ ቀውስ ተፈጥሮ ነበር። ነገር ግን በሚመለከታቸው አካላት የተወሰደ እርምጃ ስለመኖሩ ማስረጃ አልተገኘም። የአፍላቶክሲን ጣጣ ግን በዚያው ወቅት ተወስኖ አልቀረም። በሌሎች ወሳኝ የምግብ አይነቶች ውስጥም ስለመገኘቱ መረጃዎች እየወጡ ነው።
2) ከወተት ቀጥሎ የተጠቀሰው በርበሬ ነው። የእንግሊዝ ሃገር የምግብ ደረጃዎች ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ የተላከ በረበሬ ውስጥ አፍላቶክሲን መገኘቱን በሚያወጣቸው ወርሃዊ ሪፖርቶች ላይ ጠቁሟል። በቅርቡም ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ ሃገር ተልኮ የነበረ ሁለት ኮንቴይነር ሙሉ በርበሬ በአፍላቶክሲን ስለተጠረጠረ እንዲጣል መደረጉ ተዘግቧል። በርበሬን በተመለከተ ኢትዮጵያ ውስጥ ምርምር እንደሚደረግበት የሚያሳይ መረጃ ማግኘት አልቻልንም። ከበርበሬ ከፍተኛ ጥቅም አንጻር ሲታይ ግን ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ ይመስላል።
3) ሌላው በአፍላቶክሲን እንደተበከለ እየተገለጸ ያለው ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ ነው። በኢትዮጵያ በለውዝ ምርት ላይ በተደረጉ ተደጋጋሚ ጥናቶች ከፍ ያለ የአፍላቶክሲን ንጥረ ነገር በውስጣቸው ተገኝቷል። የዓለም የጤና ድርጅት እና የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ደረጃ መሰረት በአንድ ኪሎግራም ለውዝ ውስጥ እስከ 15 ማይክሮግራም አፍላቶክሲን ቢኖር ጉዳቱ ያን ያህል እንዳልሆነ ይገልጻል። የኢትዮጵያው ግን ከዚህ በእጅጉ የበዛ ነው።
4) ከለውዝ ቀጥሎ የተጠቀሰው ማሽላ ነው። በኢትዮጵያዉያን ተመራማሪዎች የተከናወነ እና ባለፈው ሰኔ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው አፍላቶክሲን ከማሽላ ማሳም ገብቷል። ተመራማሪዎቹ በምስራቅ ኢትዮጵያ ከወሰዷቸው ናሙናዎች ውስጥ በሁሉም ውስጥ አፍላቶክሲን ተገኝቷል። የንጥረ ነገሩ መጠን ከማሳ ላይ በተሰበሰቡት ናሙናዎች አነስ ብሎ ታይቷል። ነገር ግን በጎተራ ከተከማቸ ማሽላ የተወሰደ ናሙና ላይ መጠኑ የበዛ አፍላቶክሲን ተገኝቷል።
ማጠቃለያ፥
ከላይ እንደጠቆምነው አፍላቶክሲን መርዛማ እና ገዳይ የሆነውን ካንሰር ያመጣል። በነዚህ የምግብ አይነቶች ውስጥ መገኘቱ ምን ይጠቁመን ይሆን? ሌሎች የምግብ አይነቶችስ? ካንሰር ቀጣዩ የኢትዮጵያ ፈተና ሊሆን ይችል ይሆን? መንግስት ጉዳዩን ስራዬ ብሎ ይዞት መጠኑ እንዲበዛ ያደረጉትን ምክንያቶች ለይቶ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት እርምጃ ይወስድ ይሆን?

ተወሰደ – EthioScienceInformer