ከአዳማ ” ለፍትህ የምትጮህ ነብስ ” በሚል ርዕስ ጨለማ አስፈሪ ሞረሽ የተባሉ ሰው በፌስ ቡከ ገጻቸው አሳዛኝ፣ አስደንጋጭ እንዲሁም ሰው የሆነ ሁሉ ሊጮህበት የሚገባ ጉዳይ አስፍረዋል። እንደ ሰውየው አባባል ትርፍ አንጀት አለብሽ የተባለች እህታቸው ቀዶ ጥገና ሲደረገላት የተከናወነው የኩላሊት ሌብነት ነው።

adama kidney stolen case.png
ከአምስት ዓመት በሁዋላ ሀመሟ እየጠነከረ ሲመጣ ሌላ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ ስታደርግ ኩላሊቷ መሰረቁ ይነገራታል። ስም፣ አድራሻ፣ የሆስፒታሉ መጠሪያና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ያለተካተቱበት ይህ ዘግናኝ ጉዳይ በትክክል ተፈጽሞ ከሆነ ወገን አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የተጠቂዋን በደል ሊታደግ ይገባል በሚል መረጃውን ተቆርቋሪ ነኝ ያሉ ልከውልናል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆናችሁና ፍርድ ቤት ሚዛንና ብይን ሰለማዛባቱ መረጃ ያላችሁ ዝርዝር ጉዳዩን ብታሳውቁ በልጅቷ ላይ በእርግጥ በደሉ ተፈጽሞ ከሆነ በጎ ፈቃደኛ ተሟጋቾች ማግኘት ይቻላል ሲሉ መልዕቱን የላኩት ክፍሎች ጥሪ አቅርበዋል። በፌስ ቡክ የተሰራጨው መረጃ እንደሚከተለው ይነበባል።
ለፍትህ የምትጮህ ነብስ ከአዳማ
የምንኖረው አዳማ ነው። ከዛሬ 5 አመት በፊት እህቴን ትንሽ ያማትና ሆስፒታል ስትሄድ ትርፍ አንጀት ነው ያመመሽ ተብላ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት ይነገራታል። ከዚያም የቀዶ ጥገናው ሂደት ተጀመሮ በስኬት ተጠናቀቀ።
በወቅቱም ሙሉ የአካል ምርመራ ስታደርግ ሁሉም የአካል ክፍሎቿ ጥሩ ሁኔታ ላይ አንዳሉ ይነገራታል። እየቆየ ግን እህቴን በጣም ያማት ጀመር። ለምርመራ ሌላ ሆስፒታል ወሰድናት። የሚሰማትን ተናገረችና ምርመራ ሲደረግላት አንዱ ኩላሊቷ እንደሌለ ይነገራታል።
አስደንጋጭ ነበር። ለካ በዚያን ወቅት የትርፍ አንጀቷ ቀዶ ጥገና ይሰሩላት የነበሩት ዶክተሮች ተመካክረው አንዱን ኩላሊቷን ሰርቀዋት ኖሯል። ስለዚህ ከሆስፒታሉ ሁሉንም ማስረጃዎቿን አስወጥታ ክስ ጀመረች። ነገር ግን ከዛሬ ነገ ፍርድ እናገኛለን ብለን ብንጠብቅም ክሱ የትም ሊደርስ አልቻለም። ምክንያቱም ዶክተሮቹ ለመርማሪ ፖሊሶች ገንዘብ ሰጥተው ነበርና። ከዚህ በኋላም ፍርድ እናገኛለን ብለን አናምንም። ነገር ግን እንደእህቴ የዚህ ሙያዊ ሙስና ሰለባ የሆኑ ብዙዎች ይኖራሉና መጠንቀቅ ይኖርባቸው ዘንድ ህዝብ እንዲያውቀው መናገሩን መርጠናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *