በአንድ ካምፓኒ ሰራተኛ ‘ኤ’ ወደ ቅርብ ኃላፊው በመሄድ የእለት ሥራ እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡የቀርብ ኃላፊውም ሰራተኛውን ወደ ወንዝ ወሰደና “በል ይሄን ወንዝ ተሻግረህ ማዶ ልይህ” አለው፡፡ ሰራተኛ ‘ኤ’ ሥራውን በሚገባ ካጠናቀቀ በኋላ ሥራውን መጨረሱን ለኃላፊው ሪፖርት ባደረገ ጊዜ ኃላፊው በፈገግታ ሁኖ “ጥሩ ሥራ ሠርተሀል” ሲል መለሰለት፡፡

በማግስቱ ‘ቢ’ የተባለ ሰራተኛ ለዛው የሥራ ኃለፊ የእለቱን ሥራ እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡ ኃላፊው ለሰራተኛ ‘ኤ’ የሰጠውን ተመሳሳይ ሥራ እንዲሰራ ሰጠው፡፡ሰራተኛ ‘ቢ’ ስራውን ለመከወን ወደ ወንዙ ጫፍ ሲደርስ ሰራተኛ ‘ሲ’ ወንዙን ለመሻግር ጥረት ሲያደርግ ተመለከተውና ተመሳሳይ ሥራ እንደተሰጣቸው ተገነዘበ፡፡ በዚህ ጊዜ ሰራተኛ ‘ቢ’የ’ራሱን መሻገር ብቻ ሳይሆን ሰራተኛ ‘ሲ’ እንዲሻገር እርዳታ አደረገለት፡፡ ሰራተኛ ‘ቢ’ የሥራውን ውጤት ለኃላፊው ሪፖርት ባደረገ ጊዜ ኃላፊው እንደተለመደው ፈገግታ እያሳየው “በጣም ጥሩ ሥራ” ሲል የሙገሳ መልስ ሰጠው፡፡ በቀጣዩ ቀን ሰራተኛ ‘ኪው’ ለዛው የሥራ ኃላፊ የዕለቱን ሥራ ይሰጠው ዘንድ ጠየቀ፡፡ የበፊቶቹ የሠሩትን ተመሳሳይ ሥራ እንዲሰራ ተነገረው፡፡ ሰራተኛ ‘ኪው’ ሥራውን ከመሥራቱ በፊት ቅድመ ዝግጅት አደረገ፡፡ በቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴውም ሰራተኛ ‘ኤ’፣’ቢ’ና ‘ሲ’ ሥራውን ቀደም ብለው እንደሰሩት ተገነዘበ፡፡ እነሱን በማናግርም ሥራውን በምን አኳኋን እንደሰሩት መረጃ ወሰደ፡፡ መረጃውን ካገኘ በኋላ ቁጭ ብሎ ወንዙን ለመሻገር የሚያስችሉ የአሰራር ደንቦችን ለየ፡፡ አያይዞም ወንዙን በመሻገር ሂደት በተግባር የሚከሰቱ ስህተቶችን ለይቶ በማስቀመጥ በቀላል ጥረት ወንዙን መሻገር የሚያስችሉ ስልቶችን ጨምሮ በመጠቆም እንዲሁም አተገባበሩን የሚገልጽ ሰነድ በማዘጋጀት ለኃላፊው ዝርዝር ሪፖርቱን ከማሰልጠኛ ሰነዱ ጋር አቀረበ፡፡ የቅርብ ኃላፊው በጣም ተሰድቶ “እጅግ በጣም ጥሩ ሥራ ሰርተሀል” አለው፡፡ በማግስቱ ሰራተኛ ‘ኦ’ የእለቱን ሥራ እንዲሰጠው ያንኑ የሥራ ኃለፊ በጠየቀ ጊዜ እንደበፊቶቹ ሰራተኞች ተመሳሳይ ሥራ ተሰጠው፡፡ ሰራተኛ ‘ኦ’ ቀዳሚው ሥራው ያደረገው ሰራተኛ ‘ኪው’ ያዘጋጀውን ሰነድ ያሰራር ማኑዋል ማጥናት ነበር፡፡ ከጥናቱ የተረዳውም ካምፓኒው ይሄን ሥራ ለመስራት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እያወጣ እንደሆነ ተረዳ፡፡ በመሆኑም ወንዙን ከመሻገሩ በፊት ፋታ ወስዶ ማሰብ ጀመረ፡፡ ድልድይ መስራት አዋጭ እንደሆነ ስላመነበት የድልድዩን ዲዛይን በመስራት ወደ ኃላፊው ይዞ በመቅረብ ከዚህ በኋላ ይሄን ተግባር ለአንድም ሰራተኛ መመደብ አይጠበቅብህም ሲል አሰረዳው፡፡ ኃለፊውም “ላቅ ያለ ስራ ስለሰራህ ኮርቸብሃለሁ” በማለት የተሰማውን ደስታ ገለጸለት፡፡

Related stories   በምናለሽ ተራ ገበያ – ከሰኞ እስከ እሁድ

ከዚህ ታሪክ በመነሳት በሰራተኛ ‘ኤ’፣ ‘ቢ’ ፣ ‘ኪው’ና ‘ኦ’ ምን ልዩነት አለ ብለን ስንጠይቅ ባብዛኛው የምናገኘው ምላሽ በመስሪያ ቤትም ሆነ በቤታችን የኛ ሥራ ብለን ከልለን ባስቀመጥነው የመታጠር(የመወሰን) ሁኔታ እንዳለ ያችን ከተወጣንም ከእኛ ተጨማሪ ምንም እንደማይጠበቅ ቆጥረን ኃላፊነትን በመወጣት ስሜት ደስተኞች እንደምንሆን ነው፡፡
እራሳችንን ከሰራተኛ ‘ቢ’ ጋር ብናወዳድረው ሌሎቹ ችግራቸው አንዲፈታ ማገዝ መቻል የእራስንም ክህሎት እንደሚያሻሽል እንገነዘባለን፡፡ “ለማስተማር ተማር ለመማር አስተምር” እንደሚባው ማለት ነው፡፡ ሰራተኛ ‘ኪው’ ከታዘዘው አንድ እርማጃ ከፍ ብሎ በመሄድ የስልጠና ሰነዶችን በማዘጋጀቱ ለሌሎች ሠራተኞች የዕውቀት መሠረት ጣለ፡፡ በዚህም በቡድኑ ውስጥ ክህሎትን ለማሸጋገር ከፍተኛ ሚና ተጫወተ፡፡

Related stories   የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

የላቀ ሥራ የሰራው ሰራተኛ ‘ኦ’ ደግሞ የስራውን አተገባበር አላስፈላጊነት በማሳየት ዘላቂ መፍትሄ አስቀመጠለት፡፡ ስለሆነም ሰራተኛ ቢ፣ኪውና ኦ እንደ አንድ ግለሰብ የሚጠበቅባቸው(ከታዘዙት) የላቀ አበርክቶ እንዳደረጉ ያስገነዝበናል፡፡ ለአንድ ሰራተኛ ወሳኝ የሆነውን የእራስ ተነሳሽነት የሚባለውን ባህሪ አዳብረዋል፡፡ በሁሉም ስፍራ፤ በማንኛውም ሁኔታ የእራስ ተነሳሽነት ያለው ለስኬት አንደሚበቃ እሙን ነው፡፡ ይሄን ባህሪ ለመላበስ ደግሞ ከተለመደው አስተሳሰብ መውጣትን ይጠይቃል፡፡
ምንጭ፡ Employee

Related stories   የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ

(#ምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ) 19-09-2007 ዓ.ም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *